ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!

  • ወር: መስከረም
  • ጸሐፊ: በአዘጋጁ
  • ዓመተ ምሕረት: 2012
  • ቁጥር: 27
  • ጽሑፍ ዘርፍ: የማኅበሩ መልእክት

Overview

አንጀትሽ አልችል ብሎ ሆድሽ ሲባባ ፊትሽ ጠቊሮ ዓይንሽ የደም ዕንባ ሲያነባ እናት ዓለም እማማ አንቺ የክርስቲያኖች መለያ አርማ አንቺ ስንዱ እመቤት ባለማዕረግ የዕውቀት ምንጭ የጥበባት አፍላግ   እምነት ማንነትሽ በነጭ እንዲታደስ   መርዙ ከገበታሽ በማር እንዲለወስ   ሠገነትሽ በደም ዕንባ ሲታጠር   ኑፋቄ ከደጅሽ በዝቶ ሲቆጠር   የዓለምን ብልጽግና ግሳንግሱን   ንቀን ተጸይፈን ሹመት ሽልማቱን   ወርቅ ብር ቢመነዘር አያወጣምና ዋጋ   ስለ እናት ፍቅር እጃችን ለሰንሰለት ተዘረጋ   ሞት በአጋፋሪ ቢደገስልን    ጦርነትም በዝቶ ሲያታክተን   እንደ መብረቅ ብልጭልጭታ እንደ ነጐድጓድ ቢያስፈራ   ክርስቲያኖች ከፊት ቆመናል ስለማይበግረን መከራ   እናቴ የነፃነትሽ ትርጉም የማንነትሽ መለያ   ለሃይማኖት ሟች ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!