Friday, 22 January 2021 00:00

በጥምቀታችን እንድመቅበት በተሰጠን እንወቅበት 

Written by  ዲ/ን አሻግሬ አምጤ

Overview

ኢትዮጵያውያን በፍቅር አብረው እንዳይኖሩ የሚያደርጋቸውን ስስ ብልት እየፈለጉ ሲያጋጩ የነበሩ አሁንም በጥፋታቸው የቀጠሉ አካላት በመንግሥት መዋቅርም፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥ መኖራቸው አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው እውነታ ነው። ከመገለጫዎች አንዱም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአደባባይ በዓላት እንዳይከበሩ ምክንያት እየፈለጉ ማስተጓጎል፣ የሚደርስባቸውን መከራም ጆሮ ዳባልበስ ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን አድሎ የሚታይበት እኩይ ድርጊት እንዲታረም እና ወጥነት ያለው ሥርዓት እንዲሰፍን ስትጠይቅ ቆይታለች። የቅድመ አደጋ ስጋት ክትትልና መከላከል ሥርዓት እንዲዘረጋ እስከ መወሰን የደረሰችውም ለዚህ ነበር። ቅዱስ ፓትርያርኩ በጥቅምቱ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተከፈተበት ወቅት “ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ክርስቲያኖች ራሳችንን እናዘጋጅ!” በማለት የተናገሩትም በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው መከራ እየተባባሰ በመቀጠሉ ነው።  ባለፈው ዓመት ማለትም በ፳፻፲፪ ዓ.ም ዩኒስኮ በዓለም ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ እንዲሆን ያደረገው የጥምቀት በዓል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የሚገልጥ ቢሆንም የኢትዮጵያውያን ሁሉ መለያችን መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። የቤተ ክርስቲያን የሆነው ነገር ሁሉ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መሆኑን ከተረዳን መጠበቅ የሚኖርብንም ሁላችን መሆናችንን መገንዘብ ይኖርብናል። ተባብረን መጠበቅ የሚገባን የኦርቶዶክሳውያንን መገለጫ ብቻ ነው እያልን አለመሆናችንም መታወቅ ይኖርበታል። በሃይማኖት ብንለያይም ያለችን አንድ አገር በመሆኗ ያላትን ሁሉ የመጠበቅ ኃላፊነትም ግዴታም ያለብን ኢትየጵያውያን በሙሉ ነን። የምንጠብቀው የራሳችን ሃይማኖት መገለጫ የሆነውን ብቻ ከሆነ የሌላው ሲወድም የማይገደን ከሆነ አገራችንን የልዩ ልዩ ባህል ባለቤት መሆኗን እየተቃወምን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል።

 

ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በፍቅር አብረው እየኖሩ የሃይማኖት በዓላቸውን በጋራ ሲያከብሩ መኖራቸው የሚታወቅ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገራችንን ታሪክ የማይረዱ አንዳንድ አክራሪዎች ከራሳችን ውጭ የሆነውን ሁሉ ማየት አንፈልግም ቢሉም እውነታው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተከሠቶ በስጋት እንድንኖር እያደረገን እንዳለው አልነበረም። ሙስሊሞች የክርስቲያኖችን፣ ክርስቲያኖችም የሙስሊሞችን በዓላት በጋራ አክብረው አብረው በልተው ጠጥተው ደስታቸውን ሲገልጡ መኖራቸው ይታወቃል። በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ተከባብረው ሲኖሩ እንጂ ተገፋፍተው የጎሪጥ ሲተያዩ አልኖሩም። ተባብረው በፍቅር ባይኖሩ አንድ ሆነው አገራቸውን ጠብቀው ማቆየት ባይቻላቸውም ነበር። መተባበሩም ከሙስሊሞች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር ጭምር መሆን ይገባዋል። ኦርቶዶክሳውያንን ለማቃጠል የተለኮሰ እሳት ሌሎችንም ሲያቃጥል እያየን በመሆኑ መተባበር ግዴታችን ነው።

ዛሬም እንደጥንቱ አገራዊ አንድነታችንንና ሃይማኖታዊ ትብብራችንን የሚገልጥ ተግባር በሐረሪ ክርላዊ መንግሥት መፈጸሙን የክልሉ ኮሚንኬሽን ቢሮ ገልጧል። ጉዳዩንም “በሐረር የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ የእስልምና እምነት ተከታዮች እና የሰላም ቤተሰቦች በአንድነት ታቦታት የሚያልፉባቸውን መንገዶች ማጽዳታቸውን” የክልሉ ኮሚንኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል። በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር እየተሠራ መሆኑንም ጨምሮ ነግሮናል ። እንዲህ ዓይነቱ በጎ ጅምር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ባለፈው ዓመት የተፈጸመውን አሰቃቂ ተግባር አስታውሰን በዚህ ዓመት የሆነውን ስንሰማ ወደ ቀደመው የመከባበርና የመተሳሰብ ባህላችን እየተመለስን መሆኑን እንድንረዳ ያደርገናል። 

የክልሉ መንግሥት ክርስቲያኖች በዓላቸውን እንዲያከብሩ ጥበቃ ከማድረግ አልፎ ታቦታቱ የሚያልፉባቸው መስመሮች እንዲጸዱ የክልሉን ሙስሊም ወገኖቻችንን ማስተባበሩ የኢትዮጵያዊው እሴታችን መገለጫ ተግባር በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል። ለኢትዮጵያውያን የሚያምርብንም እንዲህ ዓይነቱ መደጋገፍ እንጂ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት መጠላለፉ አይደለም። በአገራችን የክርስቲያኖች እና የሙስሊሞች ትብብር የዓለምን ሕዝብ ሲያስገርመው እንደኖረው ሁሉ ወደ ፊትም መቀጠል የሚኖርበት የተሳሳተው እየታረመ፣ የተዛነፈው እየተስተካከለ፣ የተጣመመው እየተቃና ነው። ትልሿን ነገር እያጎሉ የልዩነት አጥር ከመሥራት እና በለው ፣ፍለጠው ከማለት ይልቅ በሚያስተሳስረን ጉዳይ አብረን እየሠራን በልዩነታችን ተከባብረን መኖር ሁላችንንም ይጠቅመናል።

እንዲህ ዓይነቱ በጎ ተግባር በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥትና በአንዳንድ የኦሮምያ አካባቢዎችም ቢደገም አገራችን ሰላም ውላ ታድራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአደባባይ በዓላት ከሆኑት አንዱ የሆነው መስቀል ተከብሮ በማያውቅባቸው በዓረብ አገራት በሰላም ሲከበር በአንዳንድ የኦሮምያ አካባቢዎች ሳይከበር መቅረቱን የምናስታውሰው ነው። በያዝነው ፳፻፲፫ ዓ.ም በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ቢሸፍቱና አዳማ ክርስቲያኖች መስቀልን እንዳያከብሩ በመከልከላቸው ክርስቲያኖች ብቻ ሳንሆን ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በልቅሶ፣ በመከራ፣ በኀዘን አሳልፈነዋል። በዚህም ከክርስቲያኖች በላይ የጎዳው ከልካዮችን መሆኑን መረዳት ይገባል። በአገራችን የዐደባባይ በዓላት  እስከ ዘመናችን ድረስ በደስታና በምስጋና ሲከበሩ ጠብቀው ማቆየት ባልተቻላቸውም ነበር። መተባበሩም ከሙስሊሞች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር ጭምር መሆን ይገባዋል። ኦርቶዶክሳውያንን ለማቃጠል የተለኮሰ እሳት ሌሎችንም ሲያቃጥል እያየን በመሆኑ መተባበር ግዴታችን ነው።

ዛሬም እንደጥንቱ አገራዊ አንድነታችንንና ሃይማኖታዊ ትብብራችንን የሚገልጥ ተግባር በሐረሪ ክርላዊ መንግሥት መፈጸሙን የክልሉ ኮሚንኬሽን ቢሮ ገልጧል። ጉዳዩንም “በሐረር የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ የእስልምና እምነት ተከታዮች እና የሰላም ቤተሰቦች በአንድነት ታቦታት የሚያልፉባቸውን መንገዶች ማጽዳታቸውን” የክልሉ ኮሚንኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል። በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር እየተሠራ መሆኑንም ጨምሮ ነግሮናል ። እንዲህ ዓይነቱ በጎ ጅምር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ባለፈው ዓመት የተፈጸመውን አሰቃቂ ተግባር አስታውሰን በዚህ ዓመት ሊተገበር የታሰበውን ስንሰማ ወደ ቀደመው የመከባበርና የመተሳሰብ ባህላችን እየተመለስን መሆኑን እንድንረዳ ያደርገናል። 

የክልሉ መንግሥት ክርስቲያኖች በዓላቸውን እንዲያከብሩ ጥበቃ ከማድረግ አልፎ ታቦታቱ የሚያልፉባቸው መስመሮች እንዲጸዱ የክልሉን ሙስሊም ወገኖቻችንን ማስተባበሩ የኢትዮጵያዊው እሴታችን መገለጫ ተግባር በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል። ለኢትዮጵያውያን የሚያምርብንም እንዲህ ዓይነቱ መደጋገፍ እንጂ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት መጠላለፉ አይደለም። በአገራችን የክርስቲያኖች እና የሙስሊሞች ትብብር የዓለምን ሕዝብ ሲያስገርመው እንደኖረው ሁሉ ወደ ፊትም መቀጠል የሚኖርበት የተሳሳተው እየታረመ፣ የተዛነፈው እየተስተካከለ፣ የተጣመመው እየተቃና ሲሄድ ብቻ ነው። ትንሿን ነገር እያጎሉ የልዩነት አጥር ከመሥራት እና በለው ፍለጠው በማለት ይልቅ በሚያስተባብረን ጉዳይ አብረን እየሠራን ልዩነታችንን አክብረን መኖር ሁላችንንም ይጠቅመናል።

እንዲህ ዓይነቱ በጎ ተግባር በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥትና በአንዳንድ የኦሮምያ አካባቢዎችም ቢደገም አገራችን ሰላም ውላ ታድራለች። በአገራችን የዐደባባይ በዓላት  እስከ ዘመናችን ድረስ በደስታና በምስጋና ሲከበሩ መኖራቸውን ታሪክ ይነግረናል። እኛም ደርሰን አይተናል። ዜጎችን ሁሉ ያለ አድልኦ አስተዳድራለሁ የሚል  መንግሥት ባለበት አገር ክርስቲያኖች የዓደባባይ በዓላትን እንዳያከብሩ ተከልክለው በኀዘን እንዲያሳልፉ  ሲደረግ የቆየውን ሊያስተካክል የሚችል በጎ ጅምር በመሆኑ በሌሎች አካባቢዎችም መደገም ይኖርበታል።

 እስከ አሁን ሲፈጸም የነበረ እኩይ ድርጊት እንዳይደገም መሥራትና የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት የፈጸመውን አርአያ ማድረግ ለሰላምና መረጋጋት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል። አንድንድ አካላት ሌሎችን ለማሳነስና ለማዋረድ የሚፈጽሙት ተግባርና የሚናገሩት ቃል ሊያጠቋቸው ከፈለጓቸው ወገኖች የበለጠ ራሳቸውን ሊያሳንሳቸው እንደሚችል የሚከተለውን ታሪክ አንብበን እንረዳ።  ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ዮሐንስና ንጉሥ ምኒልክ በሥልጣን እየተሻኮቱ ብዙ ጊዜ ለጦርነት መጋበዛቸውን የምናውቀው ነው። በመሆኑም ሊቃውንቱ እንዴት የአንድ አገር ሕዝብ እርስ በርሱ ሲጫረስ ዝም ብለን እናያለን ብለው ለማስታረቅ ተነሡ። አለቃ ምላት፣ አለቃ ሥነ ጊዮስጊስ፣ መምህር አካለ ወልድ ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ካሸማገሉ ሊቃውንት የሚጠቀሱ ነበሩ። 

በአንድ ወቅት ዐፄ ዮሐንስን ለመማለድ ትግራይ ሔደው ከነበሩ ሊቃውንት አንዱ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ ከንጉሡ ዘንድ ቀርበው በነረበት ሰዓት በንጉሥ ምኒልክ  የተበሳጩት ዐፄ ዮሐንስ ደብዳቤ ሊልኩባቸው ፈልገው ጸሐፊያቸውን “ይድረስ ከመርድዕ አዝማች ምኒልክ ብለህ ጻፍ” ይላሉ። በዚህ ጊዜ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ “ጃንሆይ እንደዚህ ብለው አይጻፉ” ይላሉ። ንጉሠ ነገሥቱም “እኮ ለምን” በማለት መልሰው ይጠይቃሉ። አለቃ ሥነ ጊዮርጊስም “ምኒልክ መርድዕ አዝማች ከተባሉ እርስዎ ንጉሠ ነገሥት መባልዎ ቀርቶ ዝቅ ብለው ንጉሥ መባልዎ አይደለምን?  ምኒልክ ንጕሥ በመሆናቸው እርስዎ ንጕሠ ነገሥት ተባሉ” ሲሏቸው ንጉሡም የሊቅ ቃል አክባሪ ስለነበሩ“ይህ ነገር እውነት ነው፤ በል ይድረስ ከንጉሥ ምኒልክ ብለህ ጻፍ”  ብለው አሳባቸውን አስተካከሉ። ሁለቱም ቅን መሪዎች ስለነበሩ የሊቃውንቱን አሳብ ተቀብለው ታረቁ።

 

የዘመናችን ባለ ሥናጣናትም ሌሎችን ለማንኳሰስ ብለው የሚጠቀሙበት ተግባር የራሳቸውን ክብር ዝቅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሌላቸው መሆኑን ስለሚያሳይባቸው ስሕተታቸውን ለማረም እንጂ በስሕተት ላይ ስሕተት ለመጨመር መትጋት አይፈልጉም።  ከእግዚአብሔር ጋር በመገዳደር ‘ሰባሁ እረዱኝ’ ማለት መሆኑን ብቻ ሳይሆን ሥልጣናቸውን እንደሚያሳጣም መገንዘብ ኖርባቸዋል። 

ከግጭትም የከሰረ እንጂ ያተረፈ ባለመኖሩ የሚፈጸመው ሁሉ ሚዛን የጠበቀ ይሆን ዘንድ  እናሳስባለን። ለሁላችን የሚበጀውን ከመፈጸም ይልቅ እናንተ እየሞታችሁ ቻሉት እኛን ግን ምንም አይንካን ከሚል አሳብ በመውጣት ሁሉን በእኩል ሚዛን ማየት መለመድ የሚገባው ተግባር ነው። 

የሆሣዕና ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ከ፵ ዓመታት በላይ  አምልኮ ሲፈጽሙበት የኖረውን የጥምቀትና የመስቀል በዓል ማክበሪያ ይዞታቸውን በከተማ አስተዳደሩ መነጠቃቸውን በተደጋጋሚ ስንሰማና ስንዘግብ መቆየታችን ይታወቃል። ሆሣዕናዎችም ሐረሪዎችን አብነት ቢያደርጉ የሥልጣን ዘመናቸው ጭምር ይረዝማል እንጅ አያጥርም። ሰላም ሲሰፍን፣ አካባቢውን በመገንዘብ ጭር ሲል አልወድም ማለት ከግጭት የሚያተርፉ አካላት ሥልጣን ላይ ለመቆየት መፈለጋቸውን እንደሚያሳይ መረዳት ይገባል። ግጭት ተቀስቅሶ አገር እንዲበጠበጥ የሚሠሩ አካላት ሁል ጊዜ ተረጋግቶ የሚኖረውን ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ትልቅ ሥራ የሠሩ ይመስላቸዋል። እንዲህ አይነት ሰዎች መደበቂያቸው ሃይማኖት ወይም ጎሳ ነው። ዓላማቸው ባይሳካ እንኳ ሕዝብ ጎራ ለይቶ ደም ሲፋሰስ በሰው ኀዘን ይደሰታሉ ይህ ግን ለአገራችን አይበጃትም። 

 

Read 766 times