Tuesday, 08 September 2020 00:00

ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል ጥቃት ለተፈጸመባቸው ምእመናን የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች 

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ሞት ሽፋን በማድርግ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ጽንፈኛ ሙስሊሞች በፈጸሙት ጥቃት ሳቢያ ንብረታቸው በቃጠሎ ለወደመባቸውና ለተፈናቀሉ ምእመናን ማቋቋሚያ የሚውል የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቤተክርስቲያን እንደምታደርግ ነሐሴ 28 ቀን 2012 ዓ/ም በሰጠችው መግለጫ አስታወቀች፡፡    ቤተክርስቲያን የምታደርገው የገንዘብ ድጋፍ ለእያንዳንዱ ተጎጂ ምእመን ከቅዱስ ዮሐንስ በዓል በፊት የሚከፋፈል ሲሆን የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያጣራ ኃላፊነት የተሰጠው ዐቢይ ኮሚቴም በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናንንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ይኖሩበት በነበረበት አካባቢ በቋሚነት በማቋቋም የጽንፈኞቹን ኦርቶዶክሳውያንን የማፈናቀልና የማጥፋ ሴራ ለማክሸፍ እንደሚሰራ አስገንዝቧል፡፡    በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በምእመናንና በንብረታቸው ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ እንዲሁም ምእመናንን መልሶ በማቋቋሙና ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ዙሪያ ዐቢይ ኮሚቴው  ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር  እንደተወያዩ ታውቋል፡፡                
Read 618 times