ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

የቆዩ እትሞች

በ PDF መልኩ በቀላሉ ያውርዱ

ስምዐ ጽድቅ ሐምሌ ፩-፲፭/፳፻፲፬ ዓ.ም

Details
Written by: Gedion Aklilu
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 27 July 2022
Hits: 3414
ስምዐ ጽድቅ ሐምሌ ፩-፲፭/፳፻፲፬ ዓ.ም
Download attachments:
  • simasidek.pdf

የተቸገሩትን በመርዳት ቤተ ክርስቲያን ቦታዋ የት ነው?

Details
Written by: ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 970

እውነተኛ የፍቅርና የርኅራኄን ሥራ ያደረገና ያሳየ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የክርስቶስ የርኅራኄ ሥራ የሚመነጨው የባሕርይ ከሆነ ፍጹም ፍቅሩ ነው፡፡ ይህ ፍቅሩ ፍጥረትን ሁሉ ሳይለይ በማያቋርጥ መግቦቱ ያኖረዋል፡፡ ሰዎች ደግሞ ከየትኛውም ፍጡር በተለየ የፍቅሩ ብቻ ሳይሆን የክብሩ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ፈቅዷል፡፡ ስለዚህም ለክፉዎችም ለደጎችም በማያቋርጥ መግቦቱ ይደርስላቸዋል፡፡ ሳይለይ ሳያዳላ መውደድን አሳይቷል፤ አስተምሯል፡፡ የዚህ የፍቅር ትምህርቱ ተቀባይ፣ ወራሽ፣ ሰባኪ፣ አድራጊ ሆና በምድር ላይ የተገለጸችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማለት ክርስቶስን መስለው የሚኖሩ ወገኖች ኅብረት ናት፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በርኅራኄ ሥራ ክርስቶስን መስላ መገኘት ግዴታዋ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  በችግር በመከራ ውስጥ ላሉ ወገኖች የርኅራኄ ሥራዎችን የመሥራት ታሪክ ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ ከተቋቋመ በኋላ እንኳን በተለያዩ የርኅራኄ ሥራዎች ቀዳሚ ሚና ነበራት፡፡ በተለይም በተደጋጋሚ በሀገራችን ይከሰት በነበረው የድርቅ አደጋ የሚጎዱ ወገኖችን በመጎብኘት ግንባር ቀደም ሚና ስትጫወት ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ለነበረው የ፲፱፻፸ዎቹ ድርቅና ተያያዥ ችግሮች ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ማእከላትን በማቋቋም ለሰዎች በመድረስ በኩል ከፍተኛ ሚና እንዲኖራት ምስጉን አመራር ሰጥተዋል፡፡ በብዙ ማእከላት ቤተ ክርስቲያን  ርዳታ ትሰጥ ነበር፡፡ 

በተጨማሪም በዚያው ዘመን በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያትም ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይና ዘላቂ ማቋቋሚያ ድጋፎችን እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ወገኖች የሕፃናት ማሳደጊያዎችን በመላው ሀገሪቱ በመክፈት የርኅራኄ ሥራዎችን አስፋፍተው ነበር፡፡ በወቅቱ የነበረው የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳር  ከምእመናን በሚሰበሰብ ገንዘብና ቁሳቁስ፣ ከዓለም አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም ለጋሾች የሚመጡ ድጋፎችን በታማኝነት ያሰራጭ ነበር፡፡

በዚህም በወቅቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳር ጥሩ አመራር ይሰጥ እንደነበር፣ ታማኝ አገልጋዮች፣ ጠንካራ ተቋማት፣ የሰመረ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ግንኙነት እንደነበረም ያሳያል፡፡ 

ጊዜያት አልፈው በአሁን ዘመን ያለውን ሁኔታ ስንገመግም ደግሞ ኢትዮጵያ በብዙ ችግሮች የተተበተበችበት ጊዜ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሀገራችንን ዘርፈ ብዙ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች እየተፈታተኗት ነው፡፡ ጦርነት፣ በአየር መዛባት የሚመጡ ጉዳቶች፣ አንበጣ፣ የብሔር ግጭቶች፣ የበሽታ መስፋፋት፣ የኑሮ ውድነት፣ የውጪ ወረራ ወዘተ እየተፈታተኗት ነው፡፡ ከዚህም አልፎ በሃይማኖት ምክንያት ራሳቸው የቤተ ክርስቲያንም ቤተሰቦች መከራ ውስጥ እየገቡ መሆናቸውን ለመረዳት ያለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በክርስቲያኖች ላይ የደረሰው ስደት፣ ሞት እና የንብረት መውደም በቂ ማሳያ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለአደጋዎች ምላሽ የመስጠት የቀደመው ክርስቲያናዊ ዝግጁነት፣ ባህል፣ የተቋም ጥንካሬ፣ የአመራር ቅንነት አላት ወይ የሚል ጥያቄ ማንሣት የግድ ነው፡፡ በአሁን ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳር  ኢትዮጵያ ከገጠማት ፈተና አንጻር የሚጠበቅባትን ያህል ምላሽ እየሰጠች መሆኑን በጥርጥር መልክ የሚታዘቡ በርካቶች ናቸው፡፡ 

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳ በሀገር ውስጥ ለሚታዩት የተለያዩ ቀውሶች  በተለያየ ጊዜ ዘር ሃይማኖት ሳትለይ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት የርዳታ እጇን ስትዘረጋ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ካለፉት ዘመናት የተሻለ ሥራ ተሠርቷል ለማለት ይከብዳል፡፡ እንደ ግዙፍነቷ ወቅታዊውን የኢትዮጵያን ሁኔታ ያገናዘበ ምላሽ የሚሰጥ ተቋም ማደራጀቱን የሚያሳይ ርምጃ ብዙም አይታይም፡፡ የርኅራኄ ሥራን የሚያስፋፋ ለወቅቱ ዘርፈ ብዙ ችግር ምላሽ የሚሰጥ በጎ አድራጎት ተቋም መሥርቶ በመላው ሀገሪቱ ማእከላዊነት ባለው መንገድ አድልዎ በሌለበት አግባብ ችግረኞችን የማገልገል ነገር በበቂ አይታይም፡፡ በሀገራችን ያለውንና የሚመጣውን መከራ ገምግሞ፣ ተንትኖ የሚያውቅ፤ በመላው ዓለም ካሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ አጥቢያዎች ርዳታ ማሰባሰብ የሚችል፣ የመጣውን ርዳታ በታማኝነት የሚያከፋፍል ተቋም ዛሬ ይዛለች ወይ? የሚለው ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡

በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን የርኅራኄ ሥራ መሥራት ያለባት ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለመላው የሀገሪቱ ችግር ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉ ነው፡፡ ጠላት ወዳጅ ሳትል ድጋፏን ለሚፈልግ ሁሉ ነው፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ችግር ላይ ላሉ ለራሷ ቤተሰቦችም በበቂ ሁኔታ ርዳታ ለመስጠት ያላት አቅም በቂ መሆኑ ላይ ጥያቄ ይነሣል፡፡ የኮቪድ ፲፱ ወረርሺኝ ባስከተለው ተጽእኖ ምክንያት አብያተ ክርስቲያናት ለአገልጋይ ካህናት ደሞዝ ለመክፈል እስከመቸገር ደርሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የዘር ጥላቻ፣ የሃይማኖት አክራሪነት ምክንያት አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ነው፡፡ ክርስቲያኖች እየተገደሉ ነው፡፡ ብዙዎች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ በቅድሚያ ፈጣን ምላሽ የሚፈልጉት ከቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ችግሮች ከተከሰቱ በኋላ ለጉዳተኞቹ ድጋፍ አሰባስባ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ጊዜ ለማይሰጡ ለርኅራኄ ሥራም የተዘጋጀች ሆና በመገኘት በፍጥነት  ምላሽ እንድትሰጥ ይጠበቅባታል፡፡ 

ዛሬ ከቤተ ክርስቲያን የሚጠበቀው ከአገልጋዮቿም ባለፈ ችግር ላይ ላሉት ሁሉ ፈጥና የምትደርስ ተቋም ሆና መገኘት እንድትችል ነው፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ቢያንስ ፶ ሚሊዮን ሕዝበ ክርስቲያንን ያቀፈች ናት፡፡ ከእነዚህ ምእመናን በትጋት ድጋፍ ማሰባሰብ ቢቻል ለበርካቶች ፈጥና ደራሽ መሆን የሚያስችላት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ባዕለ ጸጋ ምእመናን ያሏት ናት፤ በርካታ በውጪ ሀገር የሚኖሩ ምእመናን ቤተሰብም አሏት ከእነሱ በርካታ ርዳታ ማሰባሰብ ትችላለች፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ቤተሰቦቿ ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ ሐሳብ ማሰባሰብ ትችላለች፡፡ በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያን  አስተዳደር አቅሙን አሳድጎ ከሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናትና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አባላት ጋር አብሮ በመሥራትና ድጋፍ በመጠየቅ ከፍተኛ ርዳታ ማሰባሰብና ማሰራጨት ይችላል፡፡ ቤተ ከርስቲያን በምትሰጠው ርዳታ መጠን፣ ዓይነት፣ አሰጣጥ ሁሉ ከሌሎች ርዳታ ሰጪዎች ሁሉ ከፍ ብላ መገኘት አለባት፡፡ ከግብዝነት የጸዳ፣ አድልዎ የሌለበት፣ ተንኮል ያላዘለ የርዳታ አሰጣጥ  ማሳየት ይጠበቅባታል፡፡ በዚህ ደረጃ አቅምን ማሳየት መቻሉን የሚጠራጠሩ ሁሉ ነገሩን በትዝብት ማየታቸው አልቀረም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ዓላማና ጥረት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጎላ እየሆነ ነው፡፡ ይህ ለምን ሆነ? ሰይጣን አዘገየን ወይስ ምን?

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ይሄንን ለማድረግ የአስተምህሮ ግዴታ እያለበት፣ የታሪክና የልምድ መሠረት እያለው፣ ብዙ እምቅ አቅም ይዞ ሳለ  በዚህ በመከራ ጊዜ የሕዝብ ባለውለታ ሆና ቤተ ክርስቲያን ጎልታ መታየት እንድትችል ካላደረገ በእጅጉ ትዝብት ላይ መውደቅ ይገጥመዋል፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን አመራር ንቁ እንዲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ያላት ተቋም እንዲጠናከር፣ እንዲሰፋ አድርጎ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ካሉ ተቋማት ሁሉ ግዙፍና ሰፊ ሆና እንደመታየቷ ከእርሷ የሚጠበቀው ተግባርም ግዙፍና ሰፊ መሆን አለበት፡፡ ቢሆን ለሌሎችም መትረፍ ያ ቢያቅት እንኳ ለራሷ ችግረኛ ቤተሰቦች እንኳን በበቂ መድረስ ይገባታል፡፡

ዛሬ ሌላው የሃይማኖት ድርጅት በርዳታ ስም መንጋውን ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሚያስኮበልልበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን ከአገልጋይ ካህናቷ ጀምሮ ለተከታይ ምእመንዋ መድረስ ካልቻለች የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳር ከትዝብት ባለፈም ተሰሚነትን የሚያሳጣ፣ ለሃይማኖታዊ አገልግሎትም እንቅፋት የሚሆን ድክመት ሆኖ ይታይባታል፡፡ 

ከላይ ለማንሳት እንደሞከርነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ በሀገር ውስጥ ለተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ክስተቶች በቻለችው መጠን ስትረዳ ፣ ተጎጆዎችን ስትታደግ እንደቆየች ቢታወቅም በቂ ነው ግን ማለት አይቻልም፡፡ በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ድርጅት ፣የተለያዩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምእመናንን እና ባለድርሻ አካላትን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ በማደራጀት የተለያዩ ርዳታ ስታደርግ ብትቆይም ፶% በላይ ምእመን ላላት ትልቅ ተቋም ግን እጅግ አናሳ ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ እስከ ታች ያለው የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳር ይንቃ፣ ይብቃ፣ ለሀገር ለወገን ይድረስ፤ የችግረኞችን ዕንባ ያብስ፤  ክርስቶሳዊ መልኩን ከዚህ በበለጠ ሊያሣይ ይገባል እንላለን፡፡

 

የመስቀል በዓል ታሪክ ለልጆች

Details
Written by: ምኒልክ ብርሃኑ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1679

ልጆች! እንደምን ከረማችኹ! …… እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችኹ! …… በዐዲሱ ዓመት ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት እየተዘጋጃችኹ ነው? ጎበዞች! ፳፻፲፬ መልካም የትምህርት ዘመን እንዲኾንላችሁ እንመኛለን፡፡ 

ልጆችዬ! በመስከረም ወር ዳመራ በመለኮስ፣ ችቦ በማብራት የምናከብረው ታላቅ በዓል አለ! የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል በዓል ነው፡፡ በዛሬ ቆይታችን ስለመስቀል በዓል ታሪክ፣ ስለደመራና በኢትዮጵያ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የት እንደሚገኝ እንማራለን፡፡ አብራችኹን ቆዩ!

በድሮ ጊዜ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተው ብቻቸውን በጨለማ ይኖሩ ነበር፡፡ ከዛም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፤ በመስቀል ላይም ተሰቀሎ ሁላችንንም አዳነን፡፡ የሰው ልጆችንም ወደ ብርሃን አመጣቸው:: 

ታዲያ ልጆች! ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ብዙ ሰዎችን ከበሽታ ያድናል፣ ከሕመማቸው ይፈውሳል፣ ከሞት ያስነሣል፡፡ ከዕለታት ባንድ ቀን በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች መጡና የክርስቶስ መስቀል ለምን ይፈውሳል፤ ሰዎችንስ ለምን ያድናል ብለው በክፋት ተነሣሡ፡፡ ሕዝቡም ከበሽታው እንዳይድን ብለው በምቀኝነት ለመደበቅ ወሰኑ፡፡

ቅዱስ መስቀሉ በጉድጓድ እንደቀበሩት፤ 

ልጆች! እነዚያ ክፉ ሰዎች መስቀሉን ለመደበቅ ብለው ትልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ፡፡ በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥም ቀበሩት፡፡ የቀበሩት ቦታ ማንም ሰው እንዳያውቀው ቆሻሻ ደፉበት። ቆሻሻውም ተጠራቅሞ ተጠራቅሞ ትልቅ ተራራ ኾነ። በዚህም ምክንያት የመስቀሉ ቦታ ሳይታወቅ ብዙ ዓመታት አለፈ፡፡

 

የተቀበረውን መስቀል ንግሥት ዕሌኒ እንደፈለገችው፤

ልጆች! ከብዙ ጊዜ በኋላ ንግሥት ዕሌኒ የምትባል ታላቅ ንግሥት ነገሠች፡፡ ታዲያ ይቺ ንግሥት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከተቀበረበት ጉድጓድ ለማውጣት ተነሣች፡፡ ወደተቀበረበት አገር መጣችና የአካባቢውን ሰዎች ጠየቀች፡፡ ነገር ግን የሚነግራት ሰው አጣች፡፡ ከዛም ኪራኮስ የሚባል ሽማግሌ አግኝታ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ያውቅ ዘንድ ጠየቀችው፡፡ እርሱም “ለብዙ ዓመታት ቆሻሻ ሲደፋበት ስለቆየ ቦታው እንደሌሎቹ ትልቅ ተራራ ኾኗል፡፡ ስለዚኽ ትክክለኛው ቦታ የቱ እንደኾነ አላውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ዘዴ አለ፡፡ ዘዴውን የምትጠቀሙ ከኾነ እነግርሻለው” አላት፡፡

ልጆች! ኪራኮስ መስቀሉን እንድታገኘው የሚነግራት ዘዴ ምን ይኾን? ዘዴውስ መስቀሉን እንድታገኘው ይረዳታል? አብረን እንከታተል እሺ….

ንግሥት ዕሌኒ ዳመራ እንደደመረች፤

ንግሥት ዕሌኒ ኪራኮስ የሚነግራትን ዘዴ ለማወቅ በጣም ጓጓችና “ምንድን ነው ዘዴው ንገረኝ” አለችው፡፡ እርሱም “እንጨት አሰባስበሽ፣ ደመራ ደምረሽ፣ ዕጣን አድርጊበትና በእሳት አያይዢው፤ ከዛም የዕጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ሲመለስ የትኛው ተራራ እንደኾነ ይጠቁምሻል” ብሎ ዘዴውን ነገራት፡፡ ልጆች ይኽ ዘዴ ይሠራ ይኾን? ደመራ በመደመር ከዛም ጭሱ ወደ ላይ ወጥቶ እንደገና ተመልሶ ቦታውን ይነግራት ይኾን? ጭስ ደግሞ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች አይሔድም፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምንም የሚሳነው ነገር የለምና ንግሥት ዕሌኒ እንዲሳካላት ሕዝቡን ሰብስባ ጸሎት አደረገች፡፡ 

ጸሎቱን ከጨረሱ በኋላ እንጨት አሰባስባ ደመራ አስተከለች፡፡ ደመራው ላይ ዕጣን ጨመረችበት በእሳት ለኮሰችው፡፡ የአካባቢውም ሕዝብ ተሰብስበው የሚኾነውን ይከታተሉ ጀመር፡፡ ልጆችዬ! ታዲያ በዚኽ ጊዜ አንድ አስደናቂ ነገር ተከሠተ፡፡ የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ወጣና እንደገናም ወደ ታች ተመልሶ ወረደ፡፡ ከዛም አንድ ተራራ ላይ አረፈና ለተራራው ሰገደ፡፡ ሕዝቡ በሚያየው ነገር በጣም ተደነቀ፡፡ ዕሌኒም በጣም ደስ አላት፡፡ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ሁሉም በአንድነት ኾነው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ 

 

መስቀሉ በክብር ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳስገቡት፤

ልጆች አያችሁ አይደል የእግዚአብሔርን ሥራ! ለብዙ ዓመታ ተደብቆ የቆየው ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በደመራና በዕጣን ጢስ ተገኘ፡፡ በዚኽ መሠረት ንግሥት ዕሌኒ ብዙ ሰዎችን አሰባስባ ተራራውን ማስቆፈር ጀመረች፡፡ ቁፋሮ የተጀመረበት ዕለት መስከረም ፲፮ ቀን ነበር፡፡ ለሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉ ከጉድጓዱ፡፡ እርሷም ደስ አላት፤ ሕዝቡም ይኽንን ድንቅ ነገር አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ችቦም አብርተው እየዘመሩ መስቀሉን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት፡፡

ልጆችዬ! አያችሁ አይደል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ፡፡ እነዛ ክፉ ሰዎች መስቀሉን ቢቀብሩትም ተደብቆ ሊቀር አልቻለም፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአረጋዊ ኪራኮስ ምክርና ንግሥት ዕሌኒ አማካይነት ከተቀበረበት በክብር ወጣ፡፡ መስቀሉም እንደበፊቱ ሕዝቡን ከበሽታ ማዳን፣ የሞተን ማስነሣት ጀመረ፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም የክርስቶስ መስቀል ከቁፋሮ የተገኘበትን ቀን መታሰቢያ በማድረግ በየዓመቱ መስከረም ፲፮ ቀን ደመራ ይደመራ፣ ችቦ ይበራል፣ መዝሙር ይዘመራል፤ በዓሉመ በድምቀት ይከበራ፡፡ 

የመስቀል በዓል በአገራችን

ልጆች! ከላይ እንደተማርነው መስቀል የሚከበርበትን ምክንያት አውቃችኋል አይደል? ታዲያ ይኽ የመስቀል በዓል በተለየ ሁኔታ በአገራችን ኢትዮጵያ በደመቀ መልኩ ይከበራል፡፡ ከዐዲስ ዓመት ቀጥሎ የምናከብረው በመኾኑ የመስቀል በዓል ለእኛ ልዩ ትርጒም አለው፡፡ 

በቤተ ክርስቲያናችን ደመራ በመደመር፣ ችቦ በማብራት፣ ቅዳሴ በመቀደስና ማኅሌት በመቆም፤ እንዲኹም በየሰፈሩና በየአካባቢው ዳመራ እየተተከለ፣ ችቦ እየተለኮሰ ይከበራል፡፡ በይልጥ ደግሞ በመስቀል ዐደባባይ ትልቅ ዳመራ ተተክሎ ሰንበት ተማሪዎች ትርዒት እያቀረቡ፣ መዝሙር እየዘመሩ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተሰባስበው ሕዝቡ ጧፍ እያበሩ በድምቀት ይከበራል፡፡ ስለዚኽ ልጆች የመስቀልን በዓል ስናከብር የሰላማችንና የድኅነታችን ዓርማ መኾኑን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን፣ የዘላለም ሕይወትን ሊሰጠን መሥዋዕትነት የከፈለበት፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መኾኑን እያሰብን ማከበር ይገባናል። 

በሉ ልጆች ለዛሬ በዚኽ ይበቃናል፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ደኅና ሰንብቱ፡፡

 

በዓላቱ መንፈሳዊ ዕሴታቸውን እንዳይለቁ

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1141

ብዙዎች በልበ ሙሉነት ‹‹ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት›› ብለው ሲናገሩ በርካታ ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው፡፡ ታሪኳ፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓቷ፣ በዓላቷ፣ የሕዝቦቿ አብሮ የመኖር ባህል፣መከባበር፣ እንግዳ መቀበል፣ አለባበስ ስያሜውን እንድታገኝ ካስቻሏት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ምእመናን የነዚህ መንፈሳዊ ዕሴቶች ባለቤት በመሆን ግንባር ቀደሞቹ ናቸው፡፡ እምነታችን በእነዚህ ዕሴቶች ያሸበረቀ ልዩ መስተጋብር ያለውና በሌሎች ዘንድ በአርአያነት የሚጠቀስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ሀገራችን በዓለም ደረጃ እንድትታወቅ፣ ክፍ ብላም እንድትታይ አስችሏታል፡፡ የዘመን መለወጫው፣ የደመራ፣ የልደት፣ የጥምቀቱና የፋሲካው ክብረ በዓላት የበዓሉ ባለቤት ከሆነው ከኦርቶዶክሳዊው ምእመን አልፈው በሀገሪቱ ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ የሞቁ የደመቁ፣ ግዘፍ ነሥተው የሚታዩ ናቸውና፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነች ምእመናን ልጆቿ እነዚህን መንፈሳዊ ዕሴቶች ለመጠበቅ የሚያደርጉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ቀላል አይደለም፡፡

በታሪክ የሀገር መሪዎች የነበሩ ነገሥታቱ ሳይቀሩ በግንባር ቀደምነት ይሳተፉባቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች አሻራቸው ሳይጠፋ ዘመናትን ተሻግረው እዚህ ደርሰዋል፡፡ ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከአባቶች ወደ ልጆች በቅብብሎሽ እዚህ የደረሰው መንፈሳዊ በዓላችን ከትላንት በሰፋ፣ ባሸበረቀ ለሌሎች መስህብ በሆነ መልኩ ሲከናወን ማየትን ያህል የሚያስደስት ነገር የለም፡፡

ዛሬ ዛሬ እነዚህ በዓላት ከፍ ባለ ደረጃ እንዲከበሩ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በተለይም ወጣቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ በዓላት ከመድረሳቸው በፊት በየአካባቢው ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አብያተ ክርስቲያናትን፣ መንገዶችን በማጽዳት፣ ሰደቅ ዓላማ በመስቀል፣ ምእመናንን በማስተናገድ፣ ጸበል ጸዲቅ በማዘጋጀት የሚደረገው መንፈሳዊ ርብርብ ቀላል አይደለም፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያን ያለን መፈሳዊ ቅንዓት እና ተነሣሽነት በመንፈሳዊ ዕውቀት ላይ የተመሠረተና ፈሪሃ እግዚአብሔር የታከለበት ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ በብዙዎች ሳይሆን በአንዳንዶች ዘንድ የሚታይ እና ነቀፌታን የሚያስከትል አገልግሎት ዘወትር ክርስቲያናዊ ተግባሩ ማድረግ በቤተ ክርስቲያን ስምም ሆነ በአካባቢዋ እንዳይሠራ መከላከል የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡

እናት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል፣ የድርሻውን ለመወጣት ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የቤተ ክርስቲያን ልጅ በመጀመሪያ ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር መንፈሳዊ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሚሰጠውን አገልግሎት መንፈሳዊ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በዓላትን ጠብቆ መስቀልና ጥምቀት በሚውሉበት ቀን ብቻ  የሚመጣውን ትውልድ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ተገቢ መሆኑን፣ በጾምና በጸሎት ዘወትር ቤተ ክርስቲያን መሳለምና ማስቀደስ በንስሓ ሕይወት ውስጥ መኖርና ከቅዱስ ቁርባን መሳተፍ በሚችሉበት መንገድ ማስተማር የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት ያቀናልና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በተለይ የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ በዓላት ላይ የሚታዩ የሥነ ምግባር ግድፈቶችን ለማረም ከአገልግሎት በፊት እና በኋላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል በየዋህነት እና በስመ ኦርቶዶክሳዊነት ደፋ ቀና የሚሉትን ሰብስቦ መሠረታዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በመንፈስ ተጀመርው በሥጋ በሚያልቁ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን በዓላት ላይ በሚደረጉ አገልግሎቶች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድ ሊላት ይገባል፡፡ ዛሬ ዛሬ ብዙዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ተሰባስበው አገልግሎቱን በሥጋዊ መንገድ ሲያከናውኑ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያፈነገጠ ልብስ ለብሰው፣ በአካላዊ ቁመናቸው ፍጹም ዓለማዊ ሆነው፣ በተንጨባረረ ፀጉር በቤተ ክርስቲያን ዐደባባይ ላይ የሚቆሙ መንፈሳዊ አገልጋዮች በመጀመሪያ መንፈሳዊ ማድረግ እና መምከር ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብሎም ከመንፈሳውያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም ወንድሞችና እኅቶች ይጠበቃል፡፡ 

ታላላቅ የቤተ ክርስቲያንን በዓላትን አስመልክቶ ለሰንደቅ ዓላማ፣ ለጸበል ጸዲቅ፣ ለቄጠማ እየተባሉ ከየምእመናኑ የሚሰበሰቡ በርካታ ገንዘቦች ለታለመላቸው ዓላማ ሳይውሉ ቀርተው የግለሰቦችን ኪስ የሚያደልቡ፣ ከመንፈሳዊነት ባፈነገጠ መልኩ ለመዝናናት፣ ለመጠጥ ሲውሉ ማየት ሥርዓት እየሆነ መጥቷልና ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ሊባል ይገባል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያንን ስም የሚያጎድፍ መንፈሳዊ በዓላቱንም የሚያጠለሽ ድርጊት በቤተ ክርስቲያን ዙሪያና በቤተ ክርስቲያን ስም ሲደረግ እያዩ እንዳላዩ አልፎ ሂያጅ ከመሆን ቆም ብሎ ትክክለኛውን ነገር በመንገር እና በመገሠጽ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት ተገቢ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ በእነዚህ ታላላቅ በዓላት አገልግሎት ስም በየሰፈሩ የተደራጁ በርካታ ወጣቶችና፣ ማኅበራት ቢኖሩም በትክክለኛው መንገድ ቤተ ክርስቲያንን እየደገፉ ያሉት የትኞቹ ናቸው? የሚለው ግን አጠያያቂ ነው፡፡ ከላይ ለማንሣት እንደሞከርነው መንፈሳዊ ቅንዓቱ ፣ የቤተ ክርስቲያን ፍቅሩ፣ ለአገልግሎት መትጋቱ ቢኖርም አንዳንዶቹ በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጡ የመስቀል ወፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ምግብና መጠጥ ብቻ የሚያሰባስባቸው የስም ክርስቲያኖች በመሆናቸው እነዚህን ከመንፈሳውያኑ አገልጋዮች ለይቶ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር ይገባል፡፡

በቤተ ክርስቲያን በዓላት ስም የሚደረጉ የሠፈር ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አቅጣጫቸውን እየሳቱ ነውና በየአካባቢ የምንገኝ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አባቶች እና እናቶች ትክክለኛውን መንገድ በማሳየት፣ በማስተማር ማስተካከል ይጠበቅብናል፡፡ ለምሳሌ በየሰፈሩ ወጣቶች እና የአካባቢው ምእመናን ተሰብስበው ደመራ በመለኮስ የመስቀል በዓልን ያከብራሉ፡፡ በዓሉን ለማክበር መሰባሰባቸው እሰይ የሚያሰኝ ቢሆንም ያለ ዕውቀት የሚሄዱትን በማስተማር፣ ዝግጅቱ መንፈሳዊ እንዲሆን ቃለ እግዚአብሔር እንዲሰጥ በማድረግ፣ ከዘፈን ይልቅ መንፈሳዊነቱን ጠብቆ በመዝሙር እንዲሆን ማድረግ በአጠቃላይ በዓላት መንፈሳዊ ዕሴታቸውን እንዳይለቁ ለማድረግ በያለንበት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

አሜሪካ ዓለም አቀፍ የኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑ ተገለጠ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1016
አሜሪካ ዓለም አቀፍ የኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑ ተገለጠ

አሜሪካ በኦርቶዶክሳውያን መካከል ያለውን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሚስተር ሰርጌ ላቭሮቭ መናገራቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡

አሜሪካ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰች መሆኗን የገለጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴሩ በኮኒስታንቲኖፕል ሀገረ ስብከት አፍራሽ ሚና በመጫወት የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል  ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑንንም አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምዕራባውን በተለይም አሜሪካ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ጫና እያሳደሩባት መሆኑን ያጋለጡት ሰርጌ ላቭሮቭ “ዓላማቸውም የዓለም ኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለማጥፋት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ምዕራባውያን በኮኒስታንቲኖፕል የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የተጠቀሙትን መንገድ በቤላሩስና በሜዲትራሊያን ሀገሮች ላይ በዋናነትም ሶርያን፣ የሊባኖስን እንዲሁም ባልካንን በመቆጣጠር የሰርቢያ ኦርቶዶክስ  ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት አቅደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል፡፡ 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አያይዘውም መሥሪያ ቤታቸው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ባህል፣ ዕሴትና ለሩሲያ የውጭ ግንኙነት እያበረከተች ያለችውን አስተዋጽኦ እያስተዋወቀ መሆኑን ገልጠው ይሁን እንጅ የቤተ ክርስተያኗ የቀደመ ትውፊት “ሃይማኖት አያስፈልግም” በሚሉ የምዕራባውያን ሊሂቃን  እየተፈታነ መሆኑንም አክለዋል፡፡ 

 

አሜሪካ ዓለም አቀፍ የኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑ ተገለጠ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 898
አሜሪካ ዓለም አቀፍ የኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑ ተገለጠ

አሜሪካ በኦርቶዶክሳውያን መካከል ያለውን አንድነት ለመናድ አቅዳ እየሠራች መሆኑን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሚስተር ሰርጌ ላቭሮቭ መናገራቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡

አሜሪካ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰች መሆኗን የገለጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴሩ በኮኒስታንቲኖፕል ሀገረ ስብከት አፍራሽ ሚና በመጫወት የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል  ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑንንም አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምዕራባውን በተለይም አሜሪካ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ጫና እያሳደሩባት መሆኑን ያጋለጡት ሰርጌ ላቭሮቭ “ዓላማቸውም የዓለም ኦርቶዶክሳውያንን አንድነት ለማጥፋት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ምዕራባውያን በኮኒስታንቲኖፕል የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የተጠቀሙትን መንገድ በቤላሩስና በሜዲትራሊያን ሀገሮች ላይ በዋናነትም ሶርያን፣ የሊባኖስን እንዲሁም ባልካንን በመቆጣጠር የሰርቢያ ኦርቶዶክስ  ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት አቅደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል፡፡ 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አያይዘውም መሥሪያ ቤታቸው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ባህል፣ ዕሴትና ለሩሲያ የውጭ ግንኙነት እያበረከተች ያለችውን አስተዋጽኦ እያስተዋወቀ መሆኑን ገልጠው ይሁን እንጅ የቤተ ክርስተያኗ የቀደመ ትውፊት “ሃይማኖት አያስፈልግም” በሚሉ የምዕራባውያን ሊሂቃን  እየተፈታነ መሆኑንም አክለዋል፡፡ 

 

ማዕተብ ሳይኖር ክርስቲያን መሆን አይቻልምን? ክፍል አንድ

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1042

ማዕተብ ሳይኖር ክርስቲያን መሆን አይቻልምን? 

ክፍል አንድ

ውድ የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጆች! እንደምን ሰነበታችሁ? ስሜ ወለተ ወልድ እባላለሁ። የ፴ ዓመት ወጣት ነኝ፤ ባለ ትዳርና የሦስት ልጆች እናት ስሆን ባለቤቴ የሌላ እምነት ተከታይ ነው። ከባለቤቴ ጋር የተጋባነው ከቤተ ሰቦቼ ጋር ተጣልቼ የጎዳና ተዳዳሪ በሆንኩበት ወቅት ነው። ስንጋባ የምበላው፣ የምጠጣው፣ የምለብሰው የምኖርበት ሁሉ ስላልነበረኝ ለትዳር ሲጠይቀኝ እሽ አልኩት። የሌላ እምነት ተከታይ መሆኑንም አልደበቀኝም። ግን ሁለታችንም በሃይማኖታችን ልንኖር ተስማምተን ነው የተጋባነው። በኑሯችን ተስማምተን፣ ወዶኝ ወድጄው እኖራለሁ።  ከእርሱ እየተደበቅሁም ልጆቼን ክርስትና አስነሥቻቸዋለሁ። እርሱን ግን ቀስ በቀስ እመልሰዋለሁ ብየ ነበር እርሱም በበኩሉ እኔን ለመመለስ አስቦ መሰል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እኔን ለመስበክና ወደ እርሱ እምነት ለመውሰድ ይሞክራል። ከልጆቼ አንገት ላይ የማስርላቸውን ማዕተብም በየቀኑ ከአንገታቸው እየበጠሰ ይጥለዋል።  ልጆቹን እርሱም ሲመቸው ወደ መስጊድ እየወሰደ የራሱን የእምነት ሥርዐት ያስተምራቸዋል። እኔም የራሴን የኦርቶዶክስ እምነትና ሥርዐት አስተምራቸዋለሁ። እርሱም የእኔ ሃይማኖት ስህተት እንደሆነ ይነግራቸዋል፤ እኔም የእኔ እምነት ትክክል እንደሆነ እነግራቸዋለሁ። በመካከል ልጆች ችግር ላይ ወድቀዋል። እንዳንፋታ ልጆቼን ማን ያሳድግልኛል? እርሱ እንዳያሳድጋቸው ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ ነውና ከሃይማኖት ይለያቸዋል። እኔስ እንዴት ልኖር እችላለሁ። ቤተሰቦቼም እንኳን ከሌላ እምነት ተከታይ ጋር ኖሬ ጥንትም ከቤት አስወጥተውኛልና አሁን አይቀበሉኝም። ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ “ከወንድሞቻችን መካከል የማታምን ባልዋንም የምታፈቅር ከእርሱም ጋር ለመኖር የምትወድ ሚስት ያለችው ሰው ቢኖር ሚስቱን አይፍታ። ሴቲቱም የማያምንና ሚስቱንም የሚያፈቅር ከእርሷም ጋር ለመኖር የሚወድ ባል ቢኖራት ባልዋን አትፍታ” የሚል ትምህርት እንዳለ እሰማለሁ። ለመሆኑ ልጆችም ሆኑ እኔ ማዕተብ ሳናስር ክርስቲያን ሆነን መኖር አንችልምን? መፍትሔውን እንድትሰጡኝ እጠይቃለሁ።

እኅታችን ወለተወልድ በመጀመሪያ ለችግሮችሽ ሁሉ መፍትሔ አገኛለሁ ብለሽ አምነሽ ወደ እኛ በመምጣትሽ በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን። እኛም እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን፣ መጻሕፍትን አንብበን፣ ሊቃውንትን ጠይቀን እግዚአብሔር ያቀበለንን እንጽፍልሻለን።

ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር በርካታ ውጣ ውረዶች ይኖሩበታል። እኩያት ኃጣውእ፣ የዓለም ፍላጎት፣ ፈተናዎች፣ ወዘተ. ይበረቱበታል። እግዚአብሔርን አጋዥ አድርጎ በቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ተማፅኖ የታገሠ በበረከት ላይ በረከትን በክብር ላይ ክብርን ያገኛል። መታገሥ ያልቻለ ደግሞ መፍትሔ የማይሆነውን ሁሉ እንደ መፍትሔ እየቆጠረ ወደ ባሰው ችግር እየገባ ሊያገኘው የሚገባውን በረከት ሳያገኝ ይቀራል። እኅታችን በመጀመሪያ ከቤተ ሰቦችሽ የተጣላሽበትንና ከቤት የወጣሽበትን፣ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆንም የተዳረግሽበትን ችግር ባትነግሪንና ባናውቀውም የመጀመሪያው ምክንያት ሊኖር እንደሚችል እንገምታለን። ይሁን እንጂ ባለፈው ነገር ላይ ብዙ ጊዜ ሳናጠፋ ለሚመጣው ሕይወትሽ ጠቃሚ የሚሆነው ላይ እናተኩራለን። በመሆኑም ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር በሕይወቱ ፈተና ሊደርስበት እንደሚችልም በማመን ለመጣው መውጫ ለሚመጣው ደግሞ ማምለጫ ይሆኑት ዘንድ ሊያውቃቸው የሚገቡ ነጥቦችን እንመልከት።

ሀ. ከዐቅማችን በላይ እንደማንፈተን መረዳት፡- በሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር በሃይማኖት ጸንቶ በበጎ ምግባር እየተመላለሰ ለሚኖር የሰው ልጅ የማይቻል ፈተና አላዘዘም፤ አያዝዝምም። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቀቆብ ‹‹የሚፈተን ሰው ቢኖር እግዚአብሔር ይፈትነኛል አይበል፤ እግዚአብሔር ለክፉ አይፈትንምና፤ እርሱስ ማንንም አይፈትንም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፡፡›› (ያዕ. ፩፥፲፫-፲፬) በማለት እንደ ነገረን ለምንወድቅበትና ለምንጠፋበት ፈተና አሳልፎ አይሰጠንም፡፡ ይሁን እንጂ ከእምነት መጉደል የተነሣ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ሁሉ ከእኛ አቅም በላይ አድርገን እንቆጥራቸዋልን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ይዘን ማለትም በእርሱ አምነን ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምንችል “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” (ማር. ፱፥፳፫) ብሎ ነግሮናል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ማንም ሰው ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየው የሚችለው ነገር ሊኖር እንደማይችል “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ረኀብ ነውን? መራቆት ነውን? ጭንቀት ነውን? ሾተል ነውን?” (ሮሜ.፰፥፥፴፪) በማለት በዚህ ምድር ላይ የሚያጋጥሙን መከራዎች ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩን እንደማይችሉ አስረድቶናል።

ሐዋርያው እነዚህን ሁሉ የዘረዘራቸው እኛ አክብደን እንዳንመለከታቸውና ከመንፈሳዊ ሕይወት እንዳንወጣ ነው። እነዚህ የተዘረዘሩት ሁሉ በቅዱስ ወንጌልም የተዘረዘሩና ስለጽድቅ ብሎ የሚራብ፣ የሚጠማ፣ የሚያዝን፣ የሚሰደድ በአጠቃላይ መከራ የሚቀበል ሁሉ ብፁዕ እንደሚባል ራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል። ስለዚህ ራሳችንን እያዳከምን የማንችለው መስሎን እንሰናከላለን እንጂ የማንችለውን ፈተናና የማንወጣውን መከራ አያመጣብንምና አስተሳሰባችንን ማስተካከል ያስፈልጋል።

ለ. በዐቅማችን ልክ ማሰብና ማቀድ፡- እግዚአብሔር አምላካችን የሚያስብ አእምሮ ሰጥቶ አታስቡ ባይለንም ከአቅማችን በላይ እንድንጨነቅ ግን አይፈቅድልንም። ላደርገው እችላለሁ ብለን ስናቅድም የእግዚአብሔርን ፈቃድ አስቀድመን፣ ከሥጋዊው ጉዳይ ይልቅ ለመንፈሳዊው ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተን ሊሆን ይገባል። ለእኛ የሚያስፈልገንን ከእኛ በላይ የሚያስብ በጸሎተ ኪዳንም “ወዘእንበለ ንስአሎ ይሁብ ፍትወተነ ዘእምፈቃዱ፤ ሳንለምነው የሚያስፈልገንን ከፈቃዱ የሚሰጠን እርሱ ነው” ተብሎ እንደ ተጻፈ እኛ ከመለመናችን አስቀድሞ የሚያስፈልገንን ሁሉ ይሰጠናል። መዝሙረኛው ዳዊትም “ወኢያሕጥኦሙ እምዘፈቀዱ፣ ከሚፈልጉት ሁሉ አላሳጣቸውም” (መዝ. ፸፯፥፴) ብሎ እንደነገረን ለእኛ የሚሆነንን ሁሉ ይሰጠናል። ይሁን እንጂ ማንኛውንም ነገር ልናከናውን ስናስብ የምንችለውን ያህል ማሰብና ማቀድ ይኖርብናል።  

እኅታችን ወለተወልድ እውነት ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን በላከው መልእክቱ የማያምን ባል ያላት ሴት እንዲሁም የማታምን ሚስት ያለችው ሰው አብረው ለመኖር ፈቃደኛ ከሆኑና ከወደዱ አይፋቱ ብሎ ተናግሯል። ይህም ግን ቀስ በቀስ ማሳመን ከቻለ ያመነው ቅድስና ላላመነው ይተርፈውና ወደማመን ይመጣል በሚል እሳቤ እንጂ እንዲሁ ይኑሩ ማለት አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ቢሆን አስቀድመው መጠናናትና በሃይማኖት መመሳሰል ይኖርባቸዋል። ባይሆን ደግሞ እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ከተከሠቱና በሁለቱ መካከል የሃይማኖት መለያየት ካለ ያመነው ያላመነውን አስተምሮና አሳምኖ ወደራሱ ሃይማኖት ማምጣት ይኖርበታል። ይህን ደግሞ በተለይም ልዩነት እንዳለ ከመጋባታቸው በፊት ከታወቀ ማሳመን እችላለሁ ወይ? የሚለውን ከራሱ ዐቅም፣ የትምህርት ብስለት፣ የሃይማኖት ጽናት ወዘተ. ጋር መፈተሽና የሚችለውን ያህል ብቻ ማሰብና ማቀድ ይኖርበታል። 

ሐ. አጋጣሚዎችን ሁሉ ለበጎ መጠቀም ፡- ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን” (ሮሜ ፰፥፳፰) በማለት እንደተናገረ ችግር ሆነው የተፈጠሩ ክስተቶችን ለበጎ ነገር መጠቀም ያስፈልጋል። በሰው ሰውኛው ሲታዩ ከባድ ችግር የገጠማቸው ይሁን እንጂ ነገሮቹ ለበጎ የሆኑላቸው በርካታ ሰዎች ነበሩ። ታሪኩ በሰፊው በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ዮሴፍ ወንድሞቹ በቅንዐት ሰይጣናዊ ተነሣሥተው ሸጠውት ነበር። ይሁን እንጂ እነርሱ በክፋት ቢሸጡትም እግዚአብሔር ግን መሸጡንና መንገላታቱን ለበጎ አደረገለት። ዮሴፍ ከውድሞቹ ጋር ሲገናኝ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁንም ወደዚህ ስለሸጣችሁኝ አትፍሩ፤ አትቆርቆሩም፤ እግዚአብሔር ለሕይወት ከእናንተ በፊት ልኮኛልና” (ዘፍ. ፵፭፥፭) በማለት የተናገረውን ጽፎልን እናነባለን። 

እንደሚታወቀው ወንድሞቹ ሸጡት እርሱ “እግዚአብሔር ለሕይወት ከእናንተ በፊት ልኮኛል” በማለት የደረሰበትን ነገር ለበጎ መሆኑን ገለጸ። እኅታችን ከቤተ ሰቦችሽ መጣላትሽ፣ የጎዳና ተዳዳሪ መሆንሽ፣ በብዙ ችግር መሠቃየትሽ፣ በሃይማኖት ከማይመስልሽ ጋር በትዳር ሕይወት አንድ መሆንሽ ሁሉ ታስቦበት ይሁን ባይባልም ከሆነ በኋላ ግን እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን እንዲሠራ መለመንና የብዙዎችን ታሪክ የለወጠ አምላክ የአንቺንም ሕይወት ወደ መልካሙ ሕይወት እንዲለውጠው፣ የዮሴፍን መሸጥ ለመልካም ነገር የተጠቀመ እግዚአብሔር የአንቺንም መቸገር ለመልካም ነገር እንዲጠቀመው ያለማቋረጥ መጸለይ ይኖርብሻል።

ከዮሴፍ በተጨማሪ እንደ ሰው ሰውኛው ሲታይ እጅግ ከባድ ችግር የገጠማት እግዚአብሔር ግን ድንቅ ሥራውን የሠራባት የአንዲትን ቅድስት እናት ሕይወት እንጨምር። እርሷም ንግሥት ዕሌኒ ናት። ንግሥት ዕሌኒ ሃይማኖቱ የሚመስላት በበጎ ምግባር የሚመላለስ የምታምነው የሚያምናት ተርቢኖስ የተባለ ባል ነበራት። ነጋዴ ነበርና ለረጅም ጊዜ ንግድ ቆይቶ ሲመለስ ከጓደኞቹ ጋር ከሄዱበት በጥሩ ሁኔታ በመመለሳቸው ደስ ብሏቸው እንዲሁ ሚስቶቻችንም ሌላ ሳይወዱ ሳይለምዱ ብናገኛቸው እንዴት ያማረ ነው እየተበባሉ ሲነጋገሩ ተርቢኖስ ሚስቱን እጅግ ከማመኑ የተነሣ የእኔስ እንኳን ልታደርገው ሐሳቡንም አታውቀውም ብሎ ተናገረ። ከመካከላቸው አንዱ እኔ ሄጄ ወድጃት፣ ለምጃት ብመጣስ ብሎት እርሱም አታደርገውም ተባብለው ተወራረዱ። ሰይጣን የሚያመጣው ፈተና ከባድ ነውና እርሷ ሳትፈጽመው ግን ሁለቱ ባልና ሚስት የሚተዋወቁበትን ቀለበት በሠራተኛዋ አማካኝነት ይዞ ሄዶ ሳይወዳት፣ ሳይለምዳት እንደወደዳት እንደለመዳት አድርጎ ተናገረ። የሚያምናት ባለቤቷ ተርቢኖስም ነገሩን በሰከነ መንፈስ ሳያጣራ የተነገረው ሁሉ እውነት መስሎት “ሥራሽ ያውጣሽ” ብሎ በሳጥን ከቶ ከባሕር ጣላት።

 

 

 

 

የታፈነው የምሥራቅ ወለጋ ኦርቶዶክሳውያን የሰቆቃ ድምፅ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 947

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየደረሳባት ያለው መከራና መገፋት ከዚህ ቀደም ከነበረው በደል ቢከፋ እንጂ የሚቀል አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው በፀረ ክርስቲያን ኃይሎች እኩይ ድርጊት እንደቀልድ ስትቃጠልና ስትዘረፍ ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል፡፡ ምእመናንም ኦርቶዶክሳዊ መሆናቸው ብቻ እንደ በደል ተቈጥሮ በየጊዜው ደማቸው በከንቱ ሲፈስ፣ሀብት ንብረታቸው ሲዘረፍና ሲቃጠል፣ ከሞት የተረፉት ደግሞ ለስደትና  ለከፋ ሥነ ልቡናዊ ጫና ሲዳረጉ ማየትን እየለመድነው ከመምጣታችን የተነሳ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተን ድርጊቱን በሁሉም አግባብ እንዳናወግዘውና እንዳንታገለው አድርጎናል፡፡ 

በአብዛኛው የሀገራችን ክፍል ኦርቶዶክሳውያንን መግደልና ቤተ ክርስቲያንን ማውደም መብት መስሎ እስኪታይ ድረስ ለወንጀል ድርጊቱ የተሰጠው ትኩረት እጅግ አናሳ ነው፡፡ አጥፊዎች በሕግ አግባብ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሠራር ባለመኖሩ የወንጀል ድርጊቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ማዘኗና የምእመናን ዕንባ መፍሰሱ አላቆመም፡፡ በተለይ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየደረሠ ያለው ሰቆቃ ትውልድ የማይረሳው ቤተ ክርስቲያን በጥቁር ታሪክነት የምትጽፈው ነው፡፡ በነዚህ ጥቂት ዓመታት ብቻ በሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣በሶማሌ፣ በባሌና በአርሲ፣በጅማ በደቡብ ክልል፣ በሰሜን ሸዋና በከሚሴ እንዲሁም በምሥራቅና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ምድር ላይ  በርካታ ግፎች ተፈጽመዋል፤ አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል፤ ምእመናን በጭካኔ ታርደዋል፤ አካባቢያቸውን ጥለውም እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ 

ሰሞኑን ማለትም ከነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ/ም ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ኪረሙ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር ባሉ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች አፅራረ ቤተ ክርስቲያንና አፅራረ ምእመናን በአብያተ ክርስቲያናትና በምእመናን ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በጥቃቱም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በዝርፊያና በቃጠሎ ወድመዋል፤ በርካታ ምእመናንም ለሞት፣ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል መዳረጋቸውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ምንጮች አይተናል፤ ሰምተናልም፡፡ ዝግጅት ክፍላችንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን የአካባቢውን የሃይማኖት አባት አነጋግሮ መረጃ አጠናቅሯል፡፡ 

በዚህ መሠረት በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በአገልግሎት ላይ ያሉ አባት ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ እንዳስታወቁት በሀገረ ስብከቱ በየጊዜው የተለያዩ አዳዲስ ችግሮች ሲፈጠሩ መቆየታቸውን አንሥተው፤ በተደጋጋሚ በአካባቢው በሚከሠቱ የፀጥታ ችግሮች የተነሣ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን ለከፋ ጉዳት ሲጋለጡ መቆየታቸውንም ተናግረዋል፡፡ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በጭካኔ መገደላቸውን እንዲሁም የበርካቶች ሀብት ንብረት መዘረፉንና ምእመናን ከየአካባቢያቸው ተፈናቅለው በሕይወት የመኖር ዋስትና ወደሚያገኙበት ቦታ መሰደዳቸውን ያረጋገጡት እኒህ አባት በሀገረ ስብከቱ የገጠሩ ክፍል አገልጋይ የነበሩ ካህናትና ምእመናን ከፊሎቹ ተገድለው ሌሎቹ ደግሞ ለስደት በመዳረጋቸው በዚህ ወቅት የቤተ ክርስቲያን ጣራና ግድግዳው ብቻ መቅረቱን አክለዋል፡፡ “በሀገረ ስብከቱ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥፋት ሰንደን ከያዝናቸው መረጃዎች ውጭ ያልተነገረላቸውና በፀጥታ ሥጋት ምክንያት መረጃ ያላገኘንባቸው በደል የደረሰባቸው በርካታ አካባቢዎች አሉ፡፡ እስካሁን ድረስ መረጃ ያልተገኘባቸው አካባቢዎች ቢጨመሩ በምሥራቅ ወለጋ ያለቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ሁኔታ የህልውና አደጋ ላይ እንደወደቀች አመላካች ይሆናል” ሲሉ የሃይማኖት አባቱ ተናግረዋል፡፡

እኒህ አባት አያይዘውም “የወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች በአካባቢያቸው ያሉትን ችግሮች በየጊዜው ለሀገረ ስብከቱ በሚያሳውቁበት ወቅት እኛም ጉዳዩ ውሎ ሳያድር ለሚመለከተው የመንግሥት አካልና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ስናሳውቅ ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ በመንግሥትም ሆነ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ያን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታል የሚል ግምገማ የለኝም” ያሉት እኒህ አባት ከዚህ ቀደም በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በተለያዩ የወረዳ ቤተ ክህነቶች ሥር ያሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል ወይም ተዘርፈዋል” ሲሉ አክለዋል፡፡ በመቀጠልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በዚህ ዓመት ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ/ም ጀምሮ በኪረሙ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ መውደማቸውን አስታውቀው “በርካታ ምእመናንና አገልጋዮች ተገድለዋል፤ እንዲሁም ተፈናቅለዋል” ብለዋል፡፡ እንደ አካባቢው የሃይማኖት አባት ገለጻ ከሆነ ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን ለማጥቃት የጥፋት ኃይሎቹ ክርስትና ሃይማኖትንና ተከታዮቹን ምእመናንን እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ‹‹በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሣሪያ ደብቃችኋል›› በሚል ሽፋን ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሞባቸዋል፡፡ 

እኒህ አባት አክለውም “ቤተ ክርስቲያን የወንጀለኛ መደበቂያም ሆነ የመሣሪያ ማከማቻ ያለመሆኗ እየታወቀ ሆን ተብሎ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናንን ለማጥፋት” የጥፋት ኃይሎቹ የተጠቀሙበት ምክንያት ነው፡፡ በቅርቡ በጥፋት ኃይሎቹ የተገደሉት አገልጋዮችና ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ላይ እንዳሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከቅዳሴ አገልግሎት ተመልሰው ወደየቤታቸው በሚሄዱበት ጊዜ እንደሆነ የገለጹት እኒህ የሃይማኖት አባት የተገደሉ አገልጋዮችና ምእመናን ቁጥር እስካሁን ድረስ በውል ማወቅ እንዳልተቻለ አስረድተዋል፡፡ 

አያይዘውም “በሀገረ ስብከቱ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት  የቤተ ክርስቲያንን ውድቀት የሚፈልጉ አካላት ለጥፋት ኃይሎቹ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ጥቃት ለመፈጸም እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የወንጀለኛ መደበቂያና የመሣሪያ ማከማቻ እንደሆነች አስመስለው የሚናገሩ ፀረ ቤተ ክርስቲያን ኃይሎች መኖራቸው ለቤተ ክርስቲያን መጎዳት ዓይነትና ምክንያት ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡ 

በመቀጠልም የጥፋት ኃይሎቹ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችን እየመረጡ ይገድላሉ፤ ያፈናቅላሉ፤ ካሉ በኋላ እኝህ አባት “በኪረሙ ወረዳ የቤተ ክህነት ሥር በአብዛኛው ሁሉም  እየተመረጡ የሚገደሉት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩ  ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን ለማጥቃት ያለመ እንደሆነ የሚያስረዱ ከበቂ በላይ ምልክቶች አሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አጥፊዎቹ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና አገልጋዮችን ከመግደልና ከማመፈናቀል በተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠልና ጣራና ግድግዳቸውን ነቅሎ የመውሰድ ተግባር እየፈጸሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ሌላው የኪረሙ ወረዳ ቤተ ክህነት አገልጋይ የሆኑት አባት ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ እንዳስታወቁት “ወቅታዊውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያን ችግር ውስጥ እንድትወድቅ የሚፈልጉ አንዳንድ ፀረ ሰላም ኃይሎች ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥለዋታል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የዜጎችና የቤተ እምነቶችን ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአካባቢው ስለተፈጠረው  ውድመት የተጠራና የተጠናቀረ መረጃ ባይኖርም ቊጥራቸው ከዚህ በላይ ሚሆን በርካታ ምእመናን መገደላቸውና መፈናቀላቸውን ከዚህም የተነሣ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ባዶ መሆናቸውን ያስረዱት እኝህ አባት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን ከአካባቢው እየተፈናቀለ እና ጉዳዩም ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ በመሆኑ መንግሥት አስቸኳይና ተከታይ የሆነ የሰላምና የደኅንነት ሥራዎችን ሊሠራ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ “በአካባቢው ያሉ ለችግር የተጋለጡ አብያተ ክርስቲያናትንና ምእመናንን ለመጎብኘት የክልሉ መንግሥት የደኅንነት ድጋፍ እንዲያደርግልን ጥያቄ ብናቀርብም እስካሁን ድረስ ምላሽ አላገኘንም” ሲሉም እኝህ አባት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በክልሉ በመንግሥት በኩል አልፎ አልፎ ከሚገባው ቃል ውጭ ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣት እንዳልተቻለም አክለዋል፡፡ አካባቢው የጦርነት ቀጠና በመሆኑ በፀጥታ ችግር ምክንያት ሀገረ ስብከቱ ወደ ወረዳው አጣሪ ልዑክ መላክ አልቻለም” ያሉት እኝህ አባት ይሁን እንጂ ወረዳ ቤተ ክህነቱ የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ለክልሉ መንግሥት፣ ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለሀገረ ስብከቱ ማሳወቃቸውን አንሥተዋል፡፡

ከጥቃት በሕይወት የተረፉ ምእመናን በተለያየ አካባቢ ተጠልለው እንደሚገኙ የገለጡት እኝህ አባት የክልሉ መንግሥት ምእመናኑ ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ የተጠናከረ ጥበቃ እያደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ባሉ አብያተ ክርስቲያናት የሚያገለግሉ አባቶች አብዛኛውን ጊዜ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የመጡ በመሆኑ የፀጥታ ችግሩ ከተፈጠረ ጊዜ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን እየዘጉ ወደመጡበት እየተሰደዱ ነው” ሲሉ የሃማኖት አባቱ አስረድተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ በታጣቂ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው እንዳለፈ አክለው ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረው አገልግሎት ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከነበረው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተወዳዳሪ የነበረ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡

የአብነት ተማሪዎች እንኳን የድሮው ትውፊት ሳይቋረጥ ‹‹ቁራሽ›› ለምነው ይማሩበት የነበረ አካባቢ እንደነበረ ያስታወሱት እኝህ አባት አገልግሎቱ እጅግ ሰፊ የመሆኑን ያህል የአገልጋይ እጥረት የሌለበት አካባቢ እንደነበረም አንሥተዋል፡፡ አያይዘውም “አሁን ካህናት ሞተውና ፈልሰው፣ የነበረውም አገልግሎት ተዳክሞና አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ በከፍተኛ ወጭ የተገነቡት ተዘግተው የሚገኙት እነዚህ በርካታ ግዙፍ አብያተ ክርስቲያናት ቆርቆሯቸው እየተነቀለ እየተወሰደ መሆኑን ያስረዱት የሃይማኖት አባቱ በርካታ ተማሪዎች ይዘው በማስተማር ላይ የነበሩ ሊቃውንት ጉባኤያቸውን በትነው ተሰደዋል ካሉ በኋላ “የቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎትና የዕውቀት ምንጭ በመበተኑ በአካባቢው ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት አቁማለች” ሲሉም ሲሉም ሐዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ 

እንደ እኒህ አባት አገላለጽ ከሆነ ችግሮቹ በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ በአካባቢው ያሉ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ጥቃቱ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ የጥፋት ኃይሉ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ይቀጥልበታል የሚል ስጋት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ቀድም በአካባቢው አልፎ አልፎ የፀጥታ ችግሮች ቢኖሩም ከ ፳፻፲፫ ዓ/ም ጀምሮ ግን ችግሩ ተባብሶ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ የህልውና አደጋ ጥሏል ያሉት እኝህ አባት “ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በብዙ መከራ ውስጥ ነውና መከራና ፈተና ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አዲስ አይደለምና በሰሞኑ በነበረው ጭፍጨፋ ቤተ ክርስቲያናችንን ለወንበዴ ጥለን አንሄድም ያሉ አባቶችና ምእመናን ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም “እነዚህ የሕይወት ዋጋ የከፈሉ ምእመናንና አባቶች የእምነት ትርጉም የገባቸውና የሐዋርያትን መንገድ የተከተሉ ሰማዕታት ናቸው፡፡ በአገልግሎት ላይ እያሉ መሞትና እምነቴን አልክድም ቤተ ክርስቲያኔንም አላስደፍርም ብሎ መሠዋት ሰማያዊ ክብር እንደሚያስገኝ ጠንቅቀው ያወቁ ናቸው” ብለዋል፡፡ አክለውም በሕይወት የተረፉት ምእመናንና አገልጋዮችም የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ እግዚአብሔር መሆኑን አምነው ወደ እርሱ ማዘንና ዕንባቸውን በፊቱ ማፍሰስ ይኖርበናቸዋል” ሲሉ የመከሩት እኝህ አባት መንግሥትም ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

በተጨማሪም “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው የግል ጉዳያቸውን የሚያራምዱ አካላት ከድርጊታቸው ተቆጥበው ቤተ ክርስቲያናችንን ባያጠቋት፣ ባያሳድዷትና አደጋ ላይ ባይጥሏት መልካም ነው፡፡ ምእመናንም የቤተ ክርስቲያንን ውድቀት የሚመኙ በርካታ አካላት መኖራቸውን በመረዳት ለእነዚህ ፀረ- ኦርቶዶክስ ኃይላት ቦታ መስጠት ተገቢ አይደለም” ሲሉ መክረዋል፡፡ በመጨረሻም መንግሥትም በአካባቢው ያለው የፀጥታ ችግር ሁኔታ እጅግ ውስብስብ መሆኑን  ተረድቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባና ቤተ ክህነትም ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ የአካባቢው ፀጥታ እንዲከበር ጥረት ቢያደርግ መልካም እንደሆነ የሃይማኖት አባቱ አንሥተዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን ለኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ለኮማንደር ታሪኩ ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሣታቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ መረጃውን የሰጡንን  የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች ሥማቸውን ያለጠቀስነው ለደኅንነታቸው ሲባል እንደሆነ ለመግለጥ እንወዳለን፡፡    

 

“ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችንና የሀገራችን የዕውቀት ምንጮች ናቸው” ዲ/ን አንድነት ተፈራ ክፍል ሁለት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1409

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በጥሞና ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡ 

 ስምዐ ጽድቅ፡- ከአገልግሎቱ ጋር ተያይዞ ክፍላችሁና የአብነት ትምህርት ቤቶች ቅንጅት ምን ይመስላል? የገጠማችሁ ተግዳሮትስ ምንድን ነው?

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- ማኅበረ ቅዱሳን በአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ላይ በሚሠራው ሥራ ላይ ከገዳማቱና ከየአብነት ትምህርት ቤቶቹ እንዲሁም ከአህጉረ ስብከት ጋር በጋራ ጥናት በማጥናት ነው፡፡ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ሥራዎችን ይሠራል፡፡ ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችም ጭምር በውይይትና በንግግር የሚከናወኑ ናቸው፡፡ ሥራዎች ከመሠራታቸው በፊት የሚሠሩትን ሥራዎች በጥናት መለየት የመጀመሪያው ተግባር ሆኖ ለሥራው ተግባራዊነትም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር ይደረጋል፡፡ ሁልጊዜም ግልጽ የሆነ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ሥራዎችን እንጀምራለን፡፡ 

በርካታ ሥራዎች በጥንካሬ እንደሚሠሩት ሁሉ በሥራዎች መካከል ተግዳሮቶች ይገጥሙናል፡፡ ማኅበሩ በሚሠራቸው ሥራዎች ወቅት ከሚገጥሙት ችግሮች መካከል የአህጉረ ስብከት ኃላፊነት መጓደልና ሥራዎችን በኃላፊነት ወስዶ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ችግር በስፋት ይስተዋላል፡፡ ሌሎች ደግሞ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በመረከብ ተማሪዎችን መልምለው ከማስገባት አንጻር የአብነት ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ኃላፊነታቸውን አይወጡም፡፡ ነገር ግን ከፕሮጀክቶቹ  በፊት በሚፈጽሟቸው ተግባራት ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረምን ሲሆን የመግባቢያ ሰነዱም ማድረግ ያለባቸውን ነገር ሁሉ በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ቢሆንም ግን  አብዛኛው አህጉረ ስብከት ከመግባቢያ ሰነዱ ውጭ በሆነ መንገድ ፕሮጀክቶቹን ይረከባሉ፡፡ ማኅበሩ በዋናነት የሚያደርገው ፕሮጀክቶቹን አጠናቆ ማስረከብ ሲሆን አህጉረ ስብከቱ ደግሞ ተማሪዎችንና መምህራንን የመመልመል፣ በጀት የመመደብና አጠቃላይ የማስተዳደር ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ግን ይህንን እያደረጉ አይደለም፡፡ ምእመናንም የተሠሩ ፕሮጀክቶች ቶሎ ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚያደርጉት እገዛ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ሌላው ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ስናስብ የሚያጋጥመን  የገንዘብ ችግር ነው፡፡ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፕሮጀክቶችን ለመጀመርና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችንም ለማጠናቀቅ ተቸግረናል፡፡ የቁሳቁስ የዋጋ ግሽበት ሌላው ተግዳሮት ነው፡፡ የግንባታ ቁሳቁስ የዋጋ ግሽበት ሀገራዊ በመሆኑ ነገሩን ትንሽ አክብዶታል፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- በአገልግሎት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ምንድን ነው?

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- ችግሮች ሲኖሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እናደርጋለን፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት መመሥረታቸው ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ፋይዳ ለሚመለከታቸው አካላት ማስረዳት ሌላኛው የችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ ነው፡፡ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከአካባቢው ምእመናን ጋር ሁለንተናዊ ውይይቶች በተጋጋሚ ይካሄዳሉ፡፡ አቅምና ፍላጎት ያላቸውን አህጉረ ስብከት በመለየት ቅድሚያ እንዲሰጡ በማድረግ ተግዳሮቶቻችንን እንቀንሳለን፡፡ ለፕሮጀክቶቹ ቀድመው በጀቶች እንዲያዙ፣ የተማሪዎችና የመምህራን መረጣ እንዲያጠናቅቁ ይደረጋል፡፡ ፕሮጀክቶችም ቶሎ ቶሎ ክትትል ይደረግባቸዋል፤ በክትትሉ መሐል የተገኙ ክፍተቶችንም ለማረም ጥረት ይደረጋል፡፡ እንደ አጠቃላይ ፕሮጀክቶች በታቀደው መልኩ እንዲከናወኑ ጥረት በማድረግ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ይሞከራል፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- በዚህ ወቅት ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት እየተሠጣቸው ያለው ትኩረት ምን ይመስላል? 

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- ምንአልባት የአብነት ትምህርት ቤቶችና የገዳማት ደረጃ በዚህ ዘመን ተሻሽሎ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ኅብረተሰቡ ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለገዳማት እየሰጠው ያለው ትኩረትና ተቆርቋሪነት ከድሮው ጋር ሲነጻጸር በጣም አናሳ ነው፡፡ ከዚህ ቀደሞ የአብነት ተማሪዎች ‹‹በእንተ ስማለማርያም›› ብለው በሚማሩበት ወቅት ኅብረተሰቡ ያግዛቸው ይደግፋቸው ነበረ፡፡ በዚህ ዘመን ግን የዚያን ዓይነት ድጋፍና ክብካቤ የለም፡፡ በዚያን ወቅት ገዳማት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ነበሯቸው፤ በየአካባቢው ያለው የኅብረተሰብ ክፍልም ኃላፊነት ወስዶና የእኔ  ብሎ ድጋፍና ክትትል የሚያደርግበት ሁኔታ ነበር፡፡ በወቅቱ አንዳንድ ፈተናዎች እንኳን ቢኖሩም ተደጋግፎ የማለፍ ልምድ ነበር፡፡ ኅብረተሰቡም ለአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ለተማሪዎችና ለገዳማትና መምህራን የነበረው ክብር በዚህ ዘመን ካለው በእጅጉ ይለያል፡፡ ከአብነት ትምህርት ቤቶች የሚገኘው ሀገር በቀል ዕውቀቶች የሚታመንባቸው ሲሆን ትውልዱን በግብረ ግብ ስብእና ከመቅረፅ አንፃር የተለየ ድርሻ አላቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ በወቅቱ የአብነት ትምህርት ቤቶች ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡት አዎንታዊ ፋይዳ ጎልቶ የታየበትና ለኅብረተሰብ አካላትና ከባለድርሻ አካላት ተቀባይነትና ድጋፍ ያገኙ ነበር፡፡ ኅብረተሰቡም ቢሆን ልጆቹን ወደ አስኳላ (ዘመናዊ ትምህርት ቤት) ከመውሰዱ በፊት የአብነት ትምህርት ተምረው እንዲያልፉ ያደርግ ነበር፡፡ 

በዚህ ዘመን ደግሞ ለሀገር በቀል ዕውቀቶች ያለን አመለካከት ዝቅተኛ በመሆኑ በመንግሥትም ሆነ በኅብረተሰቡ ዘንድ ለአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሰጠው ትኩረት ከዕለት ዕለት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ መንግሥትም ሆነ ኅብረተሰቡ ከሀገር በቀል ዕውቀት ይልቅ ለውጭ ዕውቀትና ለባዕድ አስተምህሮ እየተገዛ መምጣቱ ከአብነት ትምህርት ቤቶች የሚገኘው ሀገር በቀል እውቀት በከፍተኛ ደረጃ እየተዘነጋ ይገኛል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን ‹‹ኋላ ቀር›› አድርጎ መመልከት መጀመሩ ትኩረት እየተነፈጋቸው በመምጣቱ ተረሱ፤ ተጣሉም፡፡ ይህም ከፍተኛ የአገልጋይ እጥረትን አምጥቷል፡፡ ለአንዳንድ የአብነት ትምህርት ቤቶች መጥፋትም ምክንያት ሆኗል፡፡ 

ለምሳሌ አቡሻኸር፣ አጫብር፣ የቆሜ ዜማ እንዲሁም የተጉለቴ አቋቋም ለመዳከምና ለመጥፋት ከተቃረቡት ትምህርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የገዳማዊ ሥርዓቱም ሆነ የአብነት ትምህርት ቤቶች ይዘት የተለወጠ ባይሆንም ነገር ግን ብዙ ትኩረት ማነስና ፈተናዎች የበዛባቸው ሆነዋል፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚኖራቸው ፋይዳ ምንድን ነው? እነዚህን ተቋማት ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳትን ማጠናከር ጥቅሙ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገርም  ጭምር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የነበሩ የሀገር መሪዎች በአብነት ትምህርት ቤቶች ያለፉ ነበሩ፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች ተዳከሙ ማለት የቤተ ክርስቲያን ዓለማና ሐዋርያዊ አገልግሎተቷ ተቋረጠ ማለት ነው፡፡ መናፍቃንን ተከራክረው የሚረቱ፣ ያላመኑትን የሚያሳምኑ እንዲሁም ያልጸኑትን የሚያጸኑ በአብነት ትምህርት ቤት ተምረው የሚወጡ አገልጋዮች ናቸውና፡፡ ስለዚህ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማስቀጠል የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማስቀጠል ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ሕልውናና መሠረቶች ያሉት አብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ላይ ነው፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምራን፣ካህናትና ሊቃውንት የሚወጡት ከአብነት ትምህርት ቤቶችና ከገዳማት ስለሆነ ነው፡፡ 

ከአብነት ትምህርት ቤቶችና ከገዳማት የሚገኘው ዕውቀት ሌላ ቦታ የማይገኝ ሀገር በቀል በመሆኑ ለሀገርና ለትውልድ እድገት ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ያለው ሀገር በቀል ዕውቀት በሌሎች ዓለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት የለም፡፡ እነዚህ ዕውቀቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕውቀቶች ብቻ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ማለት ደግሞ የሀገር ዕውቀት ነው፡፡

አብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት የሕዝብን ሥነልቡና በመጠበቅና ግብረገብ የሆነና ሀገር ጠባቂ ትውልድ ከመፍጠር አኳያ የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለውና ለሀገሩና ለሕዝብ ፍቅር ያለው ትውልድ የሚፈጥሩት እነዚህ ተቋማት ተቋማት ላይ በትኩረት መሥራት ቤተ ክርስቲያን፣ ትውልድና ሀገር ላይ መሥራት ማለት ነው፡፡ በትክክል የተሠራበት ትውልድ ሀገር ይገነባል፡፡ ያልተሠራበት ደግሞ ሀገር ያፈርሳልና የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ያላቸውን ድርሻ ተረድቶ ማጠናከርና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት የተጠናከሩ እንዲሆኑ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡ 

ከአብነት ትምህርት ቤቶች ተምረው ለሚወጡ ተማሪዎች ተገቢው ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ለትምህርት ቤቶቹም ተገቢ የሆነ በጀት ሊበጀትላቸው ይገባል፡፡ መምህራንም ተገቢ ክብር ተሰጥቷቸው ለድካማቸው የሚገባ ክፍያ ሊያገኙ ይገባል፤ የተሻሻለ ሕይወትም ይገባቸዋል፡፡ ምእመናን ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሕንፃ ከመሥራት የሰውን ልጅ መሥራት ላይ ትኩረት ቢያደርጉ ይመከራል፡፡ ምእመናን ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለገዳማት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 ከአብነት ትምህርት ቤቶችና ከገዳማት የሚገኘው ሀገር በቀል ዕውቀት ለሀገር ጠቃሚ መሆኑን መንግሥት ተረድቶ አስፈላጊውን እገዛ ሊያደርግ ይገባል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችና የገዳማት ውጤቶች ለሀገሪቱ የቱሪዝም ምንጮች ናቸው፡፡ የጥምቀትና የመስቀል በዓላት ደግሞ ለዚህ ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንና ከእርሷ የሚመነጨው ሀገር በቀል ዕውቀቶች የሀገር ውበትና ጌጦች መሆናቸውን መንግሥት በቅጡ ሊረዳ ይገባል፡፡ ስለሆነም መንግሥት ከዛሬው በተሻለ ትኩረት ቢሰጣቸው መልካም ነው እላለሁ፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- ቀረ የሚሉት ሐሳብ ካለ?

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችንና የሀገራችን የዕውቀት ምንጮች ናቸው፤ ስለዚህ ምንጮች ከደረቁ የዕውቀት የዕውቀት ምንጮቻችን ሊደርቁ ስለሚችል በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በንቃት ልንጠብቃቸው ይገባል፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት የሚናፍቁ ነፍሳትን እንድንደርስላቸው ከተፈለገ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን ማጠናከርና ያሉባቸውን ቀዳዳዎች መድፈን ያስፈልጋል፡፡  

ስምዐ ጽድቅ፡- ለነበረን ቆይታ በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን፡፡ 

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- የክፍሉን አጠቃላይ አገልግሎት እንዳካፍላችሁ ስለጋበዛችሁኝ እኔም አመሰግናለሁ፡፡

 

የኔታ ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ከ፲፱፻፳፫ እስከ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1294
የኔታ ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ከ፲፱፻፳፫ እስከ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም

የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት ካለ አብነት ትምህርት ቤት ማሰብ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ሳይበረዝ እና ሳይደለዝ ከዘመናችን እንዲደርስ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያናችን  ሊቃውንት ታላቅ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ወንበር ዘርግተው፣ ጉባኤ አስፍተው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድን በማፍራት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የማይደርቅ ምንጭ ሆነው ዛሬም ድረስ ዘልቀዋል፡፡

የአብነት መምህራን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የነገ ህልውና ዕድሜያቸውን ሙሉ አገልግለዋል፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በቅድስት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተተክለው ብዙ ፍሬን አፍርተዋል፤ የማይደርቁ ምንጭ ሆነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምንጩ ጠጥታ እንድትረካ የበኩላቸውን ሲተጉ ኖረዋል፡፡ ዓለም እና የዓለም ነገር ሳይማርካቸው ዐረፍተ ዘመን እስኪገታቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ሕይወታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ትጉሃን አባቶች መካከል ደግሞ አንዱ የኔታ ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ናቸው፡፡ እኛም የአባታችንን የሕይወት ታሪክ፣ መንፈሳዊ ትምህርታቸውንና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸውን ባጠቃላይ እስካረፉበት ኅዳር ፳፮ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ያለውን ዜና ሕይወታቸውን በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል መልካም ንባብ፦

በደብረ ሊባኖስ ገዳም የመጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር የነበሩት ታላቁ ሊቅ የኔታ ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ከአባታቸው ከመምሬ ተድላ ወልዱ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ካሰች ለማ  በወሎ ክፍለ ሀገር ኮረም ወረዳ ልዩ ስሙ ሰፍያ በሚባል ቀበሌ በቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም  ተወለዱ፡፡  

የኔታ ገብረ ሕይወት ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከወላጅ አባታቸው ከመምሬ ተድላ ወልዱ ንባብና የቃል ትምህርት ተምረዋል፡፡ ለመንፈሳዊ ትምህርት ካላቸው ጉጉት የተነሣ በታላቅ ወንድማቸው አማካይነት ወላጆቻቸውን ተደብቀው በዚያው ወሎ ክፍለ ሀገር ሙጃ ወረዳ ላስታ መዋዒት ቅድስት ማርያም ወደሚባል አካባቢ በመሄድ መሪጌታ ፈቃዱ መረጮ ከሚባሉ መምህር መዝሙረ ዳዊት ጨምሮ ሌሎች የንባብ ትምህርቶችን ተምረዋል፡፡ ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ መምህራቸው ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው በዚያው በሙጃ ወረዳ ጦቃ ቅዱስ ዮሐንስ አጥቢያ የመምህራቸው የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ባህታዊ ገብረ መስቀል ዘንድ ተቀምጠው የጀመሩትን የዳዊት ንባብና የቃል ትምህርት አጠናቀዋል፡፡ በወቅቱም የትግራይ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የዲቁና መዓርገ  ክህነት ተቀብለው በትውልድ ቦታቸው ለጥቂት ጊዜ በዲቁና ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ወደ ትምህርታቸው በመመለስም እዚያው ሙጃ ወረዳ  ወፍጫት መድኃኔ ዓለም በሚባል ቦታ ከነበሩት ከመሪጌታ መኮንን ሊበን ለሦስት ዓመታት ቅኔ ከነ አገባቡ ተምረዋል፡፡ ቀጥሎም በዚያው በወሎ ክፍለ ሀገር በዳኅና ወረዳ በአመለ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድጓ መምህርነት ሲያገለግሉ ከነበሩት ከየኔታ መኮንን ዳቤ ድጓንና ምዕራፍን በሚገባ ተምረዋል፡፡ ከዚያም በዚያው በላስታ ላሊበላ ወረዳ ወደሚገኘው ወደ ሣር ዝና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በወቅቱ የድጓ መምህር ከነበሩት ከመምህር ኃይለ ማርያም ዘንድ ተቀምጠው የምዕራፍንና የድጓ ትምህርታቸውን እንደገና አጠናክረው በመማር አጠናቀዋል፡፡ 

የድጓ ትምህርታቸውን ለማስመስከር ወደ ቤተ ልሔም ለመሄድ በዕቅድ ላይ እንዳሉ በጤና መታወክ ምክንያት ሐሳባቸው ሳይሳካላቸው በመቅረቱ ወደ መቄት ወረዳ ወንተላ ቅድስት ማርያም በመሄድ መምህር አየለ ከሚባሉ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ አቋቋም ተምረዋል፡፡

የኔታ ገብረ ሕይወት የአቋቋም ትምህርታቸውን በመማር ላይ እንዳሉ ቀድሞ ያማቸው የነበረው ሕመም ስለተመለሰባቸው ወደ ታሪካዊው ገዳም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ጠበል በመጠመቅ ሙሉ ጤንነታቸውን ስላገኙ በ፲፱፻፵፮ ዓ.ም በተግባር ቤት ለአንድ ዓመት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ደግሞ ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር ጉንድ ተክለሃይማኖት በመሄድ መምህር ድኅማ ከሚባሉት ሊቅ የዳዊት፣ የነቢያት፣ የሰሎሞን፣ የውዳሴ ማርያም፣ የቅዳሴ ማርያም፣ የኪዳንና የትምህርተ ኅቡዓት ትርጓሜንና የባሕረ ሐሳብ ትምህርትን ተምረዋል፡፡ ከዚያም በመቀጠል ከመምህር አፈወርቅ በቅጽል ስማቸው አባ አቡሻኽር ከሚባሉት ሊቅ አቡሻኽርን በሚገባ ተምረዋል፡፡ 

በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተመልሰው በመምህር ገብረ ኢየሱስ ስም ከተመሠረተው አዳሪ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በመግባት ከመምህር ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ  የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜን በሚገባ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ 

በመመህርነት ከመመረቃቸውም በፊት በመማር ላይ በነበሩበት ጊዜ ቀን የተማሩትን ማታ ማታ በማስተማር የዚያን ጊዜ ተማሪዎች የነበሩትን በኋላም ፦

1ኛ. የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን የዳዊት፣ የነቢያት፣ የሰሎሞን ትርጓሜና የባሕረ ሐሳብ ትምህርትን፣

2ኛ. ያረፉትን ብፁዕ አቡነ ቶማስን የውዳሴ ማርያም፣ የቅዳሴ ማርያም፣ የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜና የባሕረ ሐሳብ ትምህርትን፣

3ኛ. ያረፉትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን የዳዊትን ትርጓሜ፣ሌሎችንም ደቀ መዛሙርት የዳዊት፣ የነቢያትና የሰሎሞን ትርጓሜ፣ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያምን ትርጓሜ እንዲሁም የባሕረ ሐሳብን ትምህርት ያስተማሩ፣ ታላላቅን ያፈሩ ታላቅ መምህር ነበሩ፡፡

የኔታ ገብረ ሕይወት በመምህርነት ከተመረቁ በኋላ ከ፲፱፻፷፩ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ፲፱፻፸፱ ዓ.ም ድረስ ለ፲፰ ዓመታት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ምክትል መምህር በመሆን፣ ከ፲፱፻፸፱ ዓ.ም በሞተ ሥጋ እስከተለዩበት እስከ ኅዳር ፳፮ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ድረስ በዋና መምህርነት ባጠቃላይም በገዳሙ ለ፴፬ ዓመታት ወንበር ዘርግተው ጉባኤ አስፍተው በማስተማር አያሌ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡፡ 

የኔታ ገብረ ሕይወት በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም ከደብረ ሊባኖስ ወደ ዋልድባ ገዳም ለምናኔ  ሲሄዱ በወቅቱ ጦርነት ስለነበር ዋልድባ መድረስ ስላልቻሉ የሄዱበት ሳይታወቅ በአራት ወራቸው በጉንድ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ያሉ መሆናቸው ስለታወቀ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ማኅበር ሰዎችን ልከው ወደ ገዳሙ እንዲመለሱ አድርገዋቸዋል፡፡ የማስተማር ሥራቸውን እንደቀድሞው በመቀጠልም እስከ ከ፲፱፻፸፱ ዓ.ም ለ፲፰ ዓመታት በማስተማር ፲ መምህራንን አውጥተው አስመርቀዋል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ  በገዳሙ ተግባር ቤት በተለያየ የሥራ ቦታ እየዋሉ ማታ ማታ የውዳሴ ማርያም፣ የቅዳሴ ማርያምና የባሕረ ሐሳብ ትምህርት ያስተማሯቸው ደቀ ማዛሙርት ብዙዎች ናቸው፡፡

የኔታ ገብረ ሕይወት በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም በድንግልና ኑረው በ፲፪ አበው ምንኵስና የተቀበሉ ሲሆን በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም ደግሞ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የቅስና መዓርግን ተቀብለዋል፡፡ የኔታ ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት  እንዳያስተምሩ፣ አጎንብሰው መጽሐፍ እንዳይመለከቱ ከዶክተሮች መመሪያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ‹‹ከወንበሬ (ከጉባኤዬ) ሕይወቴ ታልፋለች እንጂ ትምህርቱን አላቋርጥም፤ ማዕደ እግዚአብሔር አይታጠፍም›› በማለት እስከ ዕለተ ሞታቸው ሲያስተምሩ ኖረዋል፡፡ 

ወንጌልን በቃል ሳይሆን በሥራ የተረጎሙ ትዕግሥትን እንደሸማ የተጎናጸፉ፣ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ ሁሉን አክባሪ የነበሩት የኔታ ገብረ ሕይወት በተለይም በጣና ሐይቅ ዳጋ እስጢፋኖስ በሌሎችም ገዳማት እየተዘዋወሩ መጻሕፍትን ሲመለከቱና ሲያመሠጥሩ እንዲሁም እስከ ኅዳር ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ድረስ ሲያስተምሩ ቆይተው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በተወለዱ በ፸፪ ዓመታቸው  ኅዳር ፳፮ ቀን ፲፱፻፺፭ ከዚህ ዓለም በሞተ በሥጋ አርፈዋል፡፡

                                        በረከታቸው ይደርብን

ምንጭ ፦ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ጥር ወር ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ፶ኛ ቁጥር ፳

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በዓላቱ መንፈሳዊ ዕሴታቸውን እንዳይለቁ

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1595

ብዙዎች በልበ ሙሉነት ‹‹ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት›› ብለው ሲናገሩ በርካታ ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው፡፡ ታሪኳ፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓቷ፣ በዓላቷ፣ የሕዝቦቿ አብሮ የመኖር ባህል፣መከባበር፣ እንግዳ መቀበል፣ አለባበስ ስያሜውን እንድታገኝ ካስቻሏት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ምእመናን የነዚህ መንፈሳዊ ዕሴቶች ባለቤት በመሆን ግንባር ቀደሞቹ ናቸው፡፡ እምነታችን በእነዚህ ዕሴቶች ያሸበረቀ ልዩ መስተጋብር ያለውና በሌሎች ዘንድ በአርአያነት የሚጠቀስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ሀገራችን በዓለም ደረጃ እንድትታወቅ፣ ክፍ ብላም እንድትታይ አስችሏታል፡፡ የዘመን መለወጫው፣ የደመራ፣ የልደት፣ የጥምቀቱና የፋሲካው ክብረ በዓላት የበዓሉ ባለቤት ከሆነው ከኦርቶዶክሳዊው ምእመን አልፈው በሀገሪቱ ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ የሞቁ የደመቁ፣ ግዘፍ ነሥተው የሚታዩ ናቸውና፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነች ምእመናን ልጆቿ እነዚህን መንፈሳዊ ዕሴቶች ለመጠበቅ የሚያደርጉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ቀላል አይደለም፡፡

በታሪክ የሀገር መሪዎች የነበሩ ነገሥታቱ ሳይቀሩ በግንባር ቀደምነት ይሳተፉባቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች አሻራቸው ሳይጠፋ ዘመናትን ተሻግረው እዚህ ደርሰዋል፡፡ ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከአባቶች ወደ ልጆች በቅብብሎሽ እዚህ የደረሰው መንፈሳዊ በዓላችን ከትላንት በሰፋ፣ ባሸበረቀ ለሌሎች መስህብ በሆነ መልኩ ሲከናወን ማየትን ያህል የሚያስደስት ነገር የለም፡፡

ዛሬ ዛሬ እነዚህ በዓላት ከፍ ባለ ደረጃ እንዲከበሩ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በተለይም ወጣቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ በዓላት ከመድረሳቸው በፊት በየአካባቢው ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አብያተ ክርስቲያናትን፣ መንገዶችን በማጽዳት፣ ሰደቅ ዓላማ በመስቀል፣ ምእመናንን በማስተናገድ፣ ጸበል ጸዲቅ በማዘጋጀት የሚደረገው መንፈሳዊ ርብርብ ቀላል አይደለም፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያን ያለን መፈሳዊ ቅንዓት እና ተነሣሽነት በመንፈሳዊ ዕውቀት ላይ የተመሠረተና ፈሪሃ እግዚአብሔር የታከለበት ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ በብዙዎች ሳይሆን በአንዳንዶች ዘንድ የሚታይ እና ነቀፌታን የሚያስከትል አገልግሎት ዘወትር ክርስቲያናዊ ተግባሩ ማድረግ በቤተ ክርስቲያን ስምም ሆነ በአካባቢዋ እንዳይሠራ መከላከል የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡

እናት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል፣ የድርሻውን ለመወጣት ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የቤተ ክርስቲያን ልጅ በመጀመሪያ ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር መንፈሳዊ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሚሰጠውን አገልግሎት መንፈሳዊ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በዓላትን ጠብቆ መስቀልና ጥምቀት በሚውሉበት ቀን ብቻ  የሚመጣውን ትውልድ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ተገቢ መሆኑን፣ በጾምና በጸሎት ዘወትር ቤተ ክርስቲያን መሳለምና ማስቀደስ በንስሓ ሕይወት ውስጥ መኖርና ከቅዱስ ቁርባን መሳተፍ በሚችሉበት መንገድ ማስተማር የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት ያቀናልና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በተለይ የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ በዓላት ላይ የሚታዩ የሥነ ምግባር ግድፈቶችን ለማረም ከአገልግሎት በፊት እና በኋላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል በየዋህነት እና በስመ ኦርቶዶክሳዊነት ደፋ ቀና የሚሉትን ሰብስቦ መሠረታዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በመንፈስ ተጀመርው በሥጋ በሚያልቁ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን በዓላት ላይ በሚደረጉ አገልግሎቶች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድ ሊላት ይገባል፡፡ ዛሬ ዛሬ ብዙዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ተሰባስበው አገልግሎቱን በሥጋዊ መንገድ ሲያከናውኑ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያፈነገጠ ልብስ ለብሰው፣ በአካላዊ ቁመናቸው ፍጹም ዓለማዊ ሆነው፣ በተንጨባረረ ፀጉር በቤተ ክርስቲያን ዐደባባይ ላይ የሚቆሙ መንፈሳዊ አገልጋዮች በመጀመሪያ መንፈሳዊ ማድረግ እና መምከር ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብሎም ከመንፈሳውያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም ወንድሞችና እኅቶች ይጠበቃል፡፡ 

ታላላቅ የቤተ ክርስቲያንን በዓላትን አስመልክቶ ለሰንደቅ ዓላማ፣ ለጸበል ጸዲቅ፣ ለቄጠማ እየተባሉ ከየምእመናኑ የሚሰበሰቡ በርካታ ገንዘቦች ለታለመላቸው ዓላማ ሳይውሉ ቀርተው የግለሰቦችን ኪስ የሚያደልቡ፣ ከመንፈሳዊነት ባፈነገጠ መልኩ ለመዝናናት፣ ለመጠጥ ሲውሉ ማየት ሥርዓት እየሆነ መጥቷልና ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ሊባል ይገባል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያንን ስም የሚያጎድፍ መንፈሳዊ በዓላቱንም የሚያጠለሽ ድርጊት በቤተ ክርስቲያን ዙሪያና በቤተ ክርስቲያን ስም ሲደረግ እያዩ እንዳላዩ አልፎ ሂያጅ ከመሆን ቆም ብሎ ትክክለኛውን ነገር በመንገር እና በመገሠጽ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት ተገቢ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ በእነዚህ ታላላቅ በዓላት አገልግሎት ስም በየሰፈሩ የተደራጁ በርካታ ወጣቶችና፣ ማኅበራት ቢኖሩም በትክክለኛው መንገድ ቤተ ክርስቲያንን እየደገፉ ያሉት የትኞቹ ናቸው? የሚለው ግን አጠያያቂ ነው፡፡ ከላይ ለማንሣት እንደሞከርነው መንፈሳዊ ቅንዓቱ ፣ የቤተ ክርስቲያን ፍቅሩ፣ ለአገልግሎት መትጋቱ ቢኖርም አንዳንዶቹ በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጡ የመስቀል ወፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ምግብና መጠጥ ብቻ የሚያሰባስባቸው የስም ክርስቲያኖች በመሆናቸው እነዚህን ከመንፈሳውያኑ አገልጋዮች ለይቶ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር ይገባል፡፡

በቤተ ክርስቲያን በዓላት ስም የሚደረጉ የሠፈር ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አቅጣጫቸውን እየሳቱ ነውና በየአካባቢ የምንገኝ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አባቶች እና እናቶች ትክክለኛውን መንገድ በማሳየት፣ በማስተማር ማስተካከል ይጠበቅብናል፡፡ ለምሳሌ በየሰፈሩ ወጣቶች እና የአካባቢው ምእመናን ተሰብስበው ደመራ በመለኮስ የመስቀል በዓልን ያከብራሉ፡፡ በዓሉን ለማክበር መሰባሰባቸው እሰይ የሚያሰኝ ቢሆንም ያለ ዕውቀት የሚሄዱትን በማስተማር፣ ዝግጅቱ መንፈሳዊ እንዲሆን ቃለ እግዚአብሔር እንዲሰጥ በማድረግ፣ ከዘፈን ይልቅ መንፈሳዊነቱን ጠብቆ በመዝሙር እንዲሆን ማድረግ በአጠቃላይ በዓላት መንፈሳዊ ዕሴታቸውን እንዳይለቁ ለማድረግ በያለንበት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

መንግሥት የቤተ ክርስቲያንንና የምእመናንን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቀርቡ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 25 September 2021
Hits: 1976

የሀገሪቱ መንግሥት የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና የምእመናንን ደኅንነት ሊያስጠብቅ እንደሚገባ የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የሃማኖት አባቶች ጥሪ አቀርቡ፡፡ 

በቅርቡ ማለትም ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ/ም በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ኪረሙ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥረ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች አሸባሪው ፀረ ሰላም ታጣቂ ቡድን በፈጸመው ጥቃት ቁጥራቸው የማይናቅ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ለሞትና ለስደት መዳረጋቸውን የሃማኖት አባቶቹ አንስተው በተጨማሪም በከፍተኛ ወጭ የተገነቡ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በዝርፊያና በቃጠሎ መውደማቸውን አስረድተዋል፡፡    

የሃይማኖት አባቶቹ አያይዘውም “ወቅታዊ የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያን ችግር ውስጥ እንድትወድቅ የሚፈልጉ የአንዳንድ ፀረ ሰላም ኃይሎች እኩይ ድርጊት ተዳምሮ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏታል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የምእመናንና የአብያተ ክርስቲያናትን ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

“በሀገረ ስብከቱ ሥር  ያሉ ለችግር የተጋለጡ አብያተ ክርስቲያናትንንና ምእመናንን ለመጎብኘት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደኅንነት ድጋፍ እንዲያደርግልን ጥያቄ ብናቀርብም እስካሁን ድረስ ምላሽ አላገኘንም” ሲሉም የሃይማኖት አባቶቹ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በክልሉ መንግሥት በኩል አልፎ አልፎ ከሚገባው የድጋፍ ቃል  ውጭ ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣት እንዳልተቻለም አክለዋል፡፡ 

የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት አካባቢ የጦርነት ቀጠና በመሆኑ በዚህ የተነሣ በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ወረዳው ሀገረ ስብከቱ አጣሪ ልዑክ መላክ አልቻለም ያሉት የሃይማኖት አባቶቹ ይሁን እንጂ ወረዳ ቤተ ክህነቱ የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለሀገረ ስብከቱ ማሳወቁን አንስተዋል፡፡

 

ከዚህ ጋር በተያያዘ “በአካባቢው ያገለግሉ የነበሩ ካህናት በመሞታቸውና በመፍለሳቸው የተነሣ ከዚህ ቀደም የነበረው አገልግሎት ተዳክሞና አብያተ ክርስቲያናትም ተዘግተው ይገኛሉ ካሉ በኋላ የሀገረ ስብከቱ የሃማኖት አባቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው የግል ጉዳያቸውን የሚያራምዱና ቤተ ክርስቲያንን እያስጠቁ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም መክረዋል፡፡ 

የሃይማኖት አባቶቹ አክለውም “የቤተ ክርስቲያንን ውድቀት የሚመኙ በርካታ አካላት መኖራቸውን በመረዳት ለእነዚህ ፀረ- ኦርቶዶክስ ኃይላት ክፍተት መስጠት ተገቢ አይደለም፡፡ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ችግር እጅግ ውስብስብና አሳሳቢ መሆኑን መንግሥት ተረድቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባና ቤተ ክህነትም ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ የአካባቢው ፀጥታ እንዲከበር ጥረት ቢያደርግ መልካም ሊሆን እንደሚችል  አስረድተዋል፡፡ 

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን ለኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ታሪኩ ስልክ የደወልንላቸው ቢሆንም ስልክ ባለማንሣታቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ 

 

Page 1 of 19

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት