ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ሐመር መጽሔት *

የታኅሣሥ ወር ሐመር መጽሔት

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 23 December 2021
Hits: 4031
የታኅሣሥ ወር ሐመር መጽሔት
Download attachments:
  • hamer_sihuf.pdf

መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 15 December 2021
Hits: 2278

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።

                                                ዘመኑ በጋራ የምንቆምበት ነው

   የምንገኝበት ዘመን መከራ የበዛበት በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ መተባበርና መደጋገፍ የሚጠይቅ ነው።መከራ ሲገጥመን መተባበር እንደሚኖርብን የማንም ማሳሰቢያና ማባበያ አያስፈልገንም። በአገራችን እየደረሰ ያለው መከራ ሊያስተባብረን ካልቻል ሌላ የሚያፋቅረን ነገር ማግኘት አንችልም። የምንኖርባትን ዓለም ጣዕም የቀየሩት ራሳቸውን ብቻ ለማትረፍ ሲደክሙ የኖሩት ሳይሆኑ በመተባበር ለመከራ የተዳረጉትን ሰዎች ሕይወት ሲታደጉ የኖሩት መሆናቸውን መገንዘብ ይገባል። ከመለያየት ይልቅ መተባበር፣ ከመቀበል ይልቅ ለተቸገሩት መስጠት የቻሉት የሰው ፍቅር የበለጠባቸው፣ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸው ለችግር ለተጋለጡትም የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የተረዱ ናቸው። መስጠት ደስታን ሲሰጥ መቀበል ኃፍረትን ያላብሳል። መተባበርና መደጋገፍ ኃይል ሲፈጥር መለያየት ደግሞ አገርን ስለሚያዳክምና ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው ተብሎ የተነገረውን ስለሚቃረን መተባበር ይገባል። ዘመኑ መደጋገፍና መረዳዳት የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ከራስ ወዳድነት መላቀቅ ታላቅነት ነው። ቀያቸውን ለቀው የተሰደዱ፣ ሀብት ንብረታቸውን አጥተው በችግር የሚሰቃዩ፣ ወገኖቻቸው አልቀው በኀዘን የተጨበጡ ወገኖቻችን ቍጥር ከሚሊዮን በላይ ሆኗል። የተቸገሩትን መርዳት ሃይማኖታዊ ግዴታችን፣ ሥነ ምግባራዊ መገለጫችን መሆኑን ተረድተን ከሌሎቹ ቀድመን ለተቸገሩ ወገኖቻችን መድረስ የሚገባን ክርስቲያኖች ነን። አገራችን ሰላም ውላ እንድታድር ታላቅ ኃላፊነት እንዳለብን መዘንጋት የለብንም። መልካም በማድረግ የተጎዱትን የምንደግፈው በሌሎች ላይ የደረሰው መከራ እንዲደርስብን ስለማንፈልግ ብቻ ሳይሆን ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ በአምላኩ ዘንድ የሚመሰገን በመሆኑ ጭምር ነው። የሃይማኖት ልዩነት ሳንፈጥር ለተቸገሩ ወገኖቻችን ስንደርስላቸው በአንድ በኩል ክርስቲያናዊ አስተምህሯችን ለሌሎች ይገለጣል። ከዚህ በተጨማሪም ክርስቲያኖች የተቸገሩትን በመደገፋችን የሞራል ልዕልናችንን ዓለም ያውቀዋል። ሰዎች ሲቸገሩ ዓይተው የሚያዝኑ ክርስቲያኖች ንዑዳን ክቡራን ተብለው ተመስግነዋል። ወገኖቻችን አገር ለቀው ተሰደው፣ ቀያቸውን ትተው ተፈናቅለው እያየን ለእነርሱ የምናደርገው ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ለእነርሱ ማዘናችን ንዑዳን ክቡራን ያሰኘናል ማለት ነው። በእርግጥ ክርስቲያኖች ለተቸገሩ ወገኖቻችን ሁሉ መልካም የምናደርገው ሰዎች ያመስግኑን፣ ንዑድ ክቡር ይበሉን ብለን አይደለም። ሰዎችን መደገፋችን አምላካችንን ስለሚያስደስተው ክርስቲያኖች በዚህ ምድር ስንኖር አምላካችንን የሚያስደስት በጎ ምግባር መፈጸም ስላለብን ነው። መከራ ሲመጣ ደግሞ የበለጠ መተባበርና መደጋገፍ ይኖርብናል። የተፈጠርንለት ዓላማ ሠርተን ያገኘነውን ራሳችን በልተን እንድንደሰት ሳይሆን ሠርተን ካገኘነው ለሌላቸው ወገኖቻችን እንድናካፍል፣ ተባብረን ወገኖቻችንን ከሞት እንድንታደግ ነው። ተጋግዘን ለተቸገሩ ወገኖቻችን በመድረስ ሕይወታቸው እንድትቀጥል፣ ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሓ እንዲያገኙ ስናግዛቸው ደስታችን ፍጹም ይሆናል። በሃይማኖት የሚመስሉን ብቻ ሳይሆኑ የማይመስሉን ወገኖቻችንም በደረሰባቸው ችግር ምክንያት አገር ለቀው ሲሰደዱ፣ በስደት ወደ አሕዛብ አገር ሲሄዱ መታደግ ከክርስቲያኖች ሁሉ የጠበቅ ተግባር ነው። ለወገኖቻችን ራሳችንን ዐሳልፈን ለመስጠት የሚያስችል መንፈሳዊ ጥብዓት ባይኖረን እንኳ ከገንዘባችን ከፍለን ለተቸገሩ ወገኖቻችን መደገፍ ከሚጠበቅብን ክርስቲያናዊ ትሩፋት ትንሹ ነው። እስከ ሞት ድረስ የተቸገሩትን በመርዳት መታደግ፣ ሰውን ሁሉ መውደድ እንደሚገባን የተነገረን ለራሳችን ከሚያስፈልገን ቀንሰን ሌሎችም እንደሚያስፈልጋቸው አምነን እንድንረዳቸው ነው። እውነተኛ ወገን የሚታወቀው በመከራ ዘመን በመሆኑ አገር ለቀው ለተሰደዱ፣ በችግር አሽክላ ታስረው ለሚሰቃዩ፣ ረሃብና ኀዘን ተጨምሮባቸው ለሚንገላቱ ወገኖቻችን በመድረስ አለኝታነታችንን በተግባር እናሳያቸው። ከመንፈስ ልዕልና የደረሱት ሰዎች ለራሳችን ይቅርብን ብለው ወገናቸውን ሲያስቀድሙ እኛ ደግሞ ቢያንስ ካለን በማካፈል ለወገን አለኝታነታችንን እናረጋግጥ። በዘመናችንም ቅዱሳን ከፈጸሙት ያልተናነሰ ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን የሚገልጠው ጦርነት በተነሣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ምእመናን የፈጸሙት ተግባር ነው። በጦርነት ምክንያት ቀያቸውን ለቀው የተሰደዱትን፣ በልዩ ልዩ ምክንያት ለችግር የተጋለጡትን ወገኖቻችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የቋንቋም ሆነ የመልክአ ምድር ልዩነት ሳናደርግ መርዳት ከክርስቲያኖች ሁሉ የሚጠበቅ በጎ ተግባር ነው። በአሳብ አንድ ሆነን የወገን ፍቅር በልጦብን ተባብረን የተቸገሩትን ከደገፍን “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ”፤ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ የተሠራች ከተማ መሰወር አይቻላትም” ተብሎ የተነገረውን በተግባር ፈጸምን ማለት ነው። በክርስቲያናዊ ምግባራችን አልጫውን ዓለም ማጣፈጥ፣ ጨለማውን ዓለም ማብራት ሲገባ ገብር ሐካይ መሆን የለብንም።ክርስቲያኖች የተራራ ላይ ብርሃንና የምድር ጨው መሆናችን የሚገለጠው ሠርተን ካገኘነው ለወገኖቻችን ስንተርፍ ነው። ሰዎች ለመከራ በተጋለጡበት ዘመን የተቸገሩትን መረዳት ለተረጅዎች የሚኖረውን ጠቀሜታ ቃላት የመግለጥ አቅም የላቸውም። ተባብረን ወገኖቻችንን ስንረዳቸው ተጎጂዎች የሚያስብልን ወገን አለ ብለው ተስፋቸው ይለመልማል፤ ዙሪያው ገደል የሆነባቸው መውጫ መንገዱ ይታያቸዋል። ተስፋቸው መለምለም ብቻ ሳይሆን ተፈናቃዮች በደረሰባቸው መከራ ምክንያት በረሃብ እንዳያልቁ ያደርጋል። ልጆቻቸው ተርበው ሲያለቅሱባቸው ተስፋ ቆርጠው አምላካቸውን እንዳይክዱና ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ በመተባበር ወገኖቻችንን መርዳት ይኖርብናል። ተፈናቃዮች ዕድሜ ልካቸውን በሰው ድጋፍ ላለመኖርና ሠርተው ተለውጠው ራሳቸውን በመቻል ሌሎችን እንዲረዱም ተግባራዊ ትምህርት ያገኙበታል ብለን እናምናለን።

በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 04 November 2021
Hits: 3201
  • ዐውደ ስብከት

ቸርነት፣ ደግነት፣ ምሕረትና ይቅር ባይነት የባሕርይ ገንዘቦቹ የሆኑት አምላካችን እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠራቸው የሰው ልጆች ከመንገዱ በመውጣት በጠላት ወጥመድ ተይዘው እንዳይቀሩ “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ ዘወትር ይጠራቸዋል፡፡ ይህ ጥሪ የንስሓ ጥሪ ነው፡፡ ንስሓ መጸጸት፣ መቆጨት፣ በሠሩት ክፉ ተግባር ማዘን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ንስሓ በሙሉ ልብ መመለስንና መለወጥን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ ድካም የሚስማማውን ሥጋ እንደ መልበሱ ይደክማል፤ ይዝላልም፡፡ ከእውነት መንገድ፣ ከጽድቅ ሕይወት ወጥቶ ይስታል፡፡ ይሁን እንጂ የሚያስብ አእምሮና የሚያመዛዝን ሕሊና ያለው ፍጡር በመሆኑ የሠራውን ስሕተት አስተውሎ ይጸጸታል፡፡ ጸጸቱ የአሳብ ለውጥ መኖሩን ያመለክታል፡፡ ይህ የአሳብ ለውጥ ብቻ መፍትሔ አይሆንምና በተግባር መገለጥ አለበት፡፡ በአሳብም በተግባርም መለወጥ ማለት የንስሓ ጥሪን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ንስሓ እከብር ባይ ልቡና የሚያሳስበንን ሥጋዊ ፍላጎት ተከትለን፣ ስላጠፋነው ጥፋት፣ ስለበደልነውም በደል ምሕረትና ይቅርታ የምንጠይቅበት ለኃጢአትና ለጥፋት የጋበዘንን ሥጋችንን የምንገሥጽበት እና የምንቀጣበት፣ የእግዚአብሔርንም ቸርነት ደጅ የምንጠናበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ ንስሓን ስናስብ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን መዘንጋት የለብንም። እነሱም፡- መናዘዝ፣ የሚሰጠንን ቀኖና መፈጸምና፣ ለኃጢአታችን ሥርየት የተሠዋልንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መቀበል የሚሉት ናቸው። ፩. ኃጢአትን መናዘዝ የራስን ጥፋት አውቆ ለእግዚአብሔርም ለሰውም መናዘዝ የንስሓ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መናዘዝ ስንል ሰው በአሳብ፣ በንግግር እና በተግባር በፈጸመው ኃጢአት ተጸጽቶ “እባክህ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቀኝ” ብሎ ጥፋቱን ለካህን ዘርዝሮ የሚናገርበት ሥርዓት ነው፡፡ አንድን ተነሳሒ እና ካህንን የንስሓ ልጅና አባት የሚያሰኘው ዋናው ጉዳይም ይህ ነው፡፡ የክርስቲያኖች የንስሓ አባት የመያዛቸው መሠረታዊ ዓላማም ይህ ነው፡፡ መናዘዝ የሚለውን ቃል ስናነሣ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ማስታወስ ይገባል፡፡ አንድ አባት ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ ከሁለቱ ልጆች መካከል ታናሹ ከአባቱ ንብረት የሚደርሰውን ተካፍሎ ለመውጣት ፈለገ፡፡ አባቱም ከሀብቱ ለልጁ ሊደርሰው ይገባል ያለውን ድርሻውን ከፍሎ ሰጠው፡፡ ልጁም ድርሻውን ተቀብሎ ወደ ሩቅ ሀገር በመሔድ ሀብቱን አባክኖ ጨረሰው፡፡ ኋላም በሚኖርበት ሀገር ጽኑ ራብ በሆነ ጊዜ ለአንድ ገበሬ የእሪያ ጠባቂ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ ረሃብ ስለጸናበትም እሪያዎች ከሚበሉት አሰር ሊመገብ ቢፈልግም የሚሰጠውአልነበረም። ረሃብ ሲጸናበት “ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በረሃብ እጠፋለሁ። ተነሥቼም ወደ አባቴ ልሔድ። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ” አለ፡፡ ወደ አባቱ ሲሔድ አባቱ ገና ሩቅ ሳለ አይቶ አዘነለት። ሮጦም አንገቱን አቀፈና ሳመው። ጎረቤቶቹንም ጠርቶ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይበለን ብሎ ታላቅ ድግስ ደገሰ ይለናል (ሉቃ.፲፭፥ ፲፩-፴፪)፡፡ ይህን አምላካዊ ቃል በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሊቃውንት በብዙ መንገድ ያመሠጥሩታል፡፡ እኛ ግን አንዱን ብቻ ብንመለከት የሁለት ልጆች አባት የተባለው የሁሉ ፈጣሪና አባት እግዚአብሔር ነው፡፡ ሁለቱ ልጆች ደግሞ ቅዱሳን መላእክትና አዳም /የሰው ልጆች/ ፣ የጠፋው ታናሹ ልጅ የተባለውም አዳም ፣ ወደ ልቡ መመለሱ ደግሞ ንስሓ ለመግባት መወሰኑን፣ ጥፋተኛ ነኝና ልጅህ ልሆን አይገባኝም አገልጋይህ አድርገኝ ማለቱም ጥፋተኛነቱን አምኖ፣ ተጸጽቶ መናዘዙን ያስረዳልናል፡፡ የሰው ልጅ የለበሰው ሥጋ ለኃጢአት የሚስማማ ከመሆኑ የተነሣ ዕለት ዕለት አውቆ በድፍረት፣ ሳያውቅ በስሕተት እንዲሁም በቸልተኝነት ሕገ እግዚአብሔርን ይተላለፋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከቤተ እግዚአብሔርና ከመንፈሳዊ አገልግሎት ይርቃል፡፡ ይህም የሕሊና ዕረፍት፣ የአእምሮ ሰላም፣ የልብ ደስታ እንዲሁም ሰማያዊ ርስትን የሚያወርስ ተስፋንም ያሳጣዋል፡፡ ያን ጊዜም ያዝናል፤ ይከፋል፤ ወደ ልቡም ተመልሶ መፍትሔ ይፈልጋል፡፡ መፍትሔውም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ ሽማግሌ መፈለግ ነው፡፡ ይህ ሽማግሌም ካህን ነው፡፡ ካህኑም እንደ ሽማግሌነቱ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቀኝ ብሎ የመጣበትን ሰው አስታርቅህ ዘንድ ጥፋትህ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ እርቅ ፈላጊውም ጥፋቱን (ኃጢአቱን) ዘርዝሮ ይናገራል፡፡ መናዘዝ የሚባለውም ይህ ነው፡፡ ኃጢአትን ለካህን የመናዘዝ ሥርዓት በኦሪት የነበረ፣ በወንጌል የቀጠለ ነው፡፡ ለምሳሌ በኦሪት “ወንድ ወይም ሴት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይተላለፍ ዘንድ ሰው የሚሠራውን ኃጢአት ቢሠራ በዚያም ሰው ላይ በደል ቢሆንበት በሠራው ኃጢአቱ ላይ ይናዘዝ” (ዘፀ.፭፥፮) ተብሎ ተጽፏል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ እንደሚገባ ለምጻሞች ቀርበው ኢየሱስ ሆይ ማረን እያሉ ወደ እርሱ ሲመጡ “ወደ ካህን ሒዱና ራሳችሁን አስመርምሩ” በማለት ወደ ካህናት ልኳቸዋል፡፡ ሔደውም ራሳቸውን ለካህን ሲያስመረምሩ (ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ) ከበደላቸው ነጽተዋል(ሉቃ.፲፯፥፲፪-፲፭)። ራስህን ለካህን አሳይ ያለውም ለምጽ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ስለነበረ (ዘሌ.፲፫፥፵፭-፵፮) ከጊዜያዊውም፣ ለዳግም ሞት ከሚያበቃው ሞትም እንዲድን ነው። ለኃጢአት በሽታ መድኃኒቱ ንስሓ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ፪. ቀኖናን ተቀብሎ መፈጸም ቀኖና (canon) የሚለው ቃል ምንጩ ጽርዕ (የግሪክ) ነው። ትርጓሜውም መቃ፣ መስፈሪያ፣ መለኪያ፣ መለካት መቊጠር ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ፲፱፻፵፰፣ ገ.፯፻፺፱)። ከንስሓ ጋር በተያያዘ ያለው ትርጒም “አንድ ተነሳሒ በካህኑ ፊት ኃጢአቱን ከተናዘዘ በኋላ ካህኑ ለኃጢአት ማስተሥረያ የሚሰጠው የመንፈሳዊ ቅጣት መጠንና ዓይነት” ማለት ነው፡፡ ቀደም ብለን እንደተመለከትነው ሁሉ ካህኑ ኃጢአተኛውን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ ሽማግሌ እንደ መሆኑ መጠን እርቁ እንዲፈጸም ጥፋተኛው ግለሰብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለይቶ ማሳወቁ የማይቀር ነው፡፡ ምክንያቱም እርቅ ሲደረግ የበደለው አካል ይቅርታ ለማግኘት፣ የተበደለው አካል ደግሞ ይቅርታ ለማድረግ በየግላቸው ሊወጡት የሚገባቸው ድርሻ አለና፡፡ በዚህም መሠረት የተነሳሒ ድርሻ በፍጹም ልብ ከመመለስ በተጨማሪ የበደለውን መካስ፣ የቀማውን መመለስ እንዲሁም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በዕንባና በዋይታ ወደ እግዚአብሔር ማልቀስ ነው፡፡ ይቅርታ ማድረግ ግን ምሕረትና ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው የእግዚአብሔር ነው፡፡ ካህኑ ለኃጢአተኛው ሰው እግዚአብሔር ይቅር ይልህ ዘንድ መንፈሳዊ ተግባራትን ፈጽም ብሎ የሚያዝዘው ትእዛዝ ቀኖና ይባላል፡፡ ይኸውም በብሉይ ኪዳን የኃጢአት፣ የበደል፣ የደኅንነት ወዘተ. መሥዋዕት ተብለው የፍየል፣ የበግ፣ የርግብ ወዘተ መሥዋዕት በማቅረብ ይፈጸም የነበረ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ፣ መጽውት የሚለው መጠን እንደካህኑ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ቀኖና በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሠረት ሰው ከስሕተቱ የሚታረምበት መንፈሳዊ ተግሣጽ ሲሆን ይህ ግን ምድራውያን ነገሥታት ለወንጀለኞች እንደሚሰጡት ቅጣት የሚታይ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ይቅር የሚለው ኃጢአተኛነቱን አምኖ በማዘኑ፣ በመቆጨቱና ከጥፋቱ በመመለሱ እንጂ ስለበደሉ በሚከፍለው ካሳ ብዛት አይደለምና፡፡ ለዚህም ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክ ላይ ልጁ ለመናዘዝ ወደ አባቱ እየመጣ ሳለ “አባቱ ግን ገና ሩቅ ሳለ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው” (ሉቃ.፲፭፥፳) የሚለው የሚያሳየው የአባቱን ርኅራኄ እንጂ ቀኖናው ከኃጢአቱ አቻ መሆኑን አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” (፩ኛ ጴጥ.፬፥፫) ባለው መሠረት ነው።አባቶቻችንም ይህንን መሠረታዊ ትምህርት አብነት አድርገው ኃጢአተኛው በኃጢአት ባሳለፈበት ዘመን ፈንታ ቀሪ ዘመኑን በጽድቅ ጎዳና እንዲመላለስ የሚያበቃውን ቀኖና ይሰጡታል፡፡ ሐዋርያው “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” በማለት መናገሩ ከተመለሳችሁ ይበቃል ማለቱ አይደለም፡፡ በኃጢአት ፈንታ ፈቃደ እግዚአብሔርን ፈጽሙ ማለቱ እንጂ፡፡ አባቶች ካህናትም በዚሁ መሠረት ለኃጢአተኛ ሰው በቀማህበት ፈንታ መጽውት፣ ያለ ልክ በመብላትና በመጠጣት፣ በስካር፣ በኃጢአት ባሳለፍክበት ዘመን ፈንታ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ በማለት ለኃጢአተኛው ቀኖና የሚሰጡት መንፈሳዊውን ጣዕም እንዲቀምስ ነው፡፡ እንዲያውም አባቶቻችን ለባለጸጋ ጾምን፣ ምንም ለሌለው ድሃ ምጽዋትን በማዘዝ ኃጢአተኞች ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመፈጸም በሰውነታቸው ላይ ጨክነው መወሰንን እንዲለማመዱ ያዛሉ፡፡ ምክንያቱም ለባለጸጋ ምግብ በቤት ውስጥ ሞልቶ ተርፎ እያለ መጾም፣ ለድሃ ደግሞ ቆጥቦ ያስቀመጠውን ወይም ለምኖ ያገኘውን ገንዘብ መመጽወት ከባድ ነውና፡፡ ይሁንና ድሃ ጦሙን አድሮም ቢሆን ይመጸውታል፤ ባለጸጋም ለተወሰነ ቀን ነውና እንደምንም ራቡን ታግሦ ይጾማል፡፡ ከዚህም የተነሣ ሰውነታቸው ኃጢአትን ከመጸየፍ በተጨማሪ ለጽድቅ መታዘዝንም ይለማመዳል፡፡ ስለዚህ ተነሳሕያን የሚሰጣቸውን ቀኖና በዛ ብለው ሳያንጎራጉሩ፣ አነሰም ብለው ሳይጠራጠሩ በካህኑ ቀኖና ላይ የእግዚአብሔር ቸርነት እና የተነሳሒው ትሩፋት ተጨምሮበት ከታላቅ በደልና ኃጢአት እንደሚያነፃቸው አምነው ቀኖናቸውን ተቀብለው መፈጸም ይገባቸዋል፡፡ ፫. ሥጋውንና ደሙን መቀበል በክርስትና አስተምህሮ የአገልግሎቶች ሁሉ መደምደሚያው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የካህናትና የመምህራን መሾም ዋና ግቡ ምእመናንን አስተምረው ለሥጋውና ለደሙ ማብቃት ነው፡፡ ምክንያቱም የመንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ግቡ ሰማያዊ ርስት መውረስ ነውና፡፡ ያለክርስቶስ ሥጋና ደም ደግሞ ሰማያዊ ርስት ማለትም የዘለዓለም ሕይወት የለም፡፡ ምክንያቱም “..እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፤ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ.፮፣ ፶) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በጠፋው ልጅ ታሪክ አስቀድመን እንደተመለከትነው ልጁ ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ አባቱ ፍሪዳ አርዶ፣ ድግስ ደግሶ ተቀብሎታል፡፡ የጠፋው ልጅ አዳም ነው፡፡ የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የመጣው ደግሞ ክርስቶስ ነው፡፡ “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና” (ሉቃ.፲፱፥፲) እንዲል፡፡ ለአዳም ልጆች የሕይወት ምግብ ሊሆን የታረደው ፍሪዳም ራሱ ክርስቶስ ነው፡፡ በቀራንዮ ኮረብታ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ፣ ደሙን አፍስሶ መሥዋዕት ሆኗልና፡፡ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መሥዋዕት ከመሆኑ አስቀድሞ ሐሙስ ማታ “እንጀራን አንሥቶ ባርኮ ቈርሶ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፤ እንዲሁም ጽዋውን አንሥቶ አመስግኖ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴ.፳፮፥፳፮) በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም የክርስቶስ ሥጋና ደም ለእኛ የሕይወት ምግብና መጠጥ ሆኖ መቅረቡን የሚናገር ነው፡፡ ስለዚህ እኛም የዘለዓለም ሕይወት ለማግኘትና ሰማያዊ ርስትን ለመውረስ የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል ይኖርብናል፡፡ “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል” (ዮሐ.፮፥፶፮-፶፯) የሚለውም ይህንኑ የሚያስገነዝበንነው፡፡ በኦሪቱ በነበረው የመሥዋዕት ሕግ እስራኤላውያን የፋሲካውን በግ ሲመገቡ ጫማቸውን ተጫምተው፣ ወገባቸውን ታጥቀው፣ ኩፌታቸውን ደፍተው በትራቸውን ይዘው እየተቻኮሉ እንዲመገቡ ታዘው ነበር (ዘፀ.፲፪፥፲፩)፡፡ ይህም ዛሬ ላለነው ክርስቲያኖች ምሳሌ ሆኖን የአማናዊውን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል በጎ ምግባር ሠርተን፣ ወንጌሉን ተጫምተን፣ የንጽሕናን ዝናር ታጥቀን፣ አክሊለ ሦክን፣ ነገረ መስቀሉን እየዘከርን (መስቀሉን ተመርኩዘን)፣ ሞት እንዳለብን በማሰብ እንዳይቀድመን ፈጥነን ንስሓ በመግባት ሥጋውንና ደሙን መመገብ የሚገባን መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክም አባት ልጁ ከጠፋበት ሲመለስ ፊሪዳውን ከማረዱ በፊት “ባሪያዎቹን ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ ስጡት” በማለት ልጁ ታጥቦ ንጹሕ የሆነውን ልብስ ለብሶና አዲስ ጫማ ተጫምቶ እንዲዘጋጅ ነበር ያደረገው፡፡ ልጁን ወደ ልቡ እንዲመለስና የአባቱን ቤት እንዲያስብ ያደረገው ረሃብ ነበር፡፡ “እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ አለ” በማለት መናገሩ ምስክር ነው፡፡ ከአባቱ ቤት ካለው ማዕድ ለመቀበል ግን አስቀድሞ ያንን ማዕድ አቋርጦ በመውጣት የበደለውን አባቱን ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት፡፡ ስለሆነም አባቱን ማረኝ አለው፡፡ አባቱም ይቅር አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ከፊሪዳው ተመገበ፡፡ እኛም ገና በአርባና በሰማንያ ቀናችን ጀምረን ስንመገብ የኖርነውን ሥጋውንና ደሙን መቀበል አቋርጠን ወደ ተለያየ የኃጢአት ሕይወት ብንገባም እንኳ ወደ ልባችን ተመልሰን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ስንመጣ አስቀድመን ስለጥፋታችን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባን ያስገነዝበናል፡፡ ይህም ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ንስሐ ገብተን መዘጋጀት የሚገባ መሆኑን ይገልጣል። አንድም የንስሓ ጉዞ መጨረሻው በክርስቶስ ሥጋና ደም መታተም የሚገባው መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡ በአጠቃላይ ሰው በኃጢአቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ከተለየ በንስሓ መመለስ ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም በነቢዩ ላይ አድሮ አምላካዊ ጥሪውን ያስተላለፈውና “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ የሚጠራን ለንስሓ ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን፣ ቅዱስ ሥጋውን በልተን፣ ክቡር ደሙን ጠጥተን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲጨምረን የሚጠበቅብንን መወጣት አለብን፡፡ በንስሓ ተመልሰን በቤቱ እንድንኖር እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ ቅዱሳን በአማላጅነታቸው አይለዩን። አሜን!!   

“በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ”

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 22 October 2021
Hits: 2597
  • ዐውደ ስብከት

ቸርነት፣ ደግነት፣ ምሕረትና ይቅር ባይነት የባሕርይ ገንዘቦቹ የሆኑት አምላካችን እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠራቸው የሰው ልጆች ከመንገዱ በመውጣት በጠላት ወጥመድ ተይዘው እንዳይቀሩ “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ ዘወትር ይጠራቸዋል፡፡ ይህ ጥሪ የንስሓ ጥሪ ነው፡፡ ንስሓ መጸጸት፣ መቆጨት፣ በሠሩት ክፉ ተግባር ማዘን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ንስሓ በሙሉ ልብ መመለስንና መለወጥን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ ድካም የሚስማማውን ሥጋ እንደ መልበሱ ይደክማል፤ ይዝላልም፡፡ ከእውነት መንገድ፣ ከጽድቅ ሕይወት ወጥቶ ይስታል፡፡ ይሁን እንጂ የሚያስብ አእምሮና የሚያመዛዝን ሕሊና ያለው ፍጡር በመሆኑ የሠራውን ስሕተት አስተውሎ ይጸጸታል፡፡ ጸጸቱ የአሳብ ለውጥ መኖሩን ያመለክታል፡፡ ይህ የአሳብ ለውጥ ብቻ መፍትሔ አይሆንምና በተግባር  መገለጥ አለበት፡፡ በአሳብም በተግባርም መለወጥ ማለት የንስሓ ጥሪን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ 

ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ንስሓ እከብር ባይ ልቡና የሚያሳስበንን ሥጋዊ ፍላጎት ተከትለን፣ ስላጠፋነው ጥፋት፣ ስለበደልነውም በደል ምሕረትና ይቅርታ የምንጠይቅበት ለኃጢአትና ለጥፋት የጋበዘንን ሥጋችንን የምንገሥጽበት እና የምንቀጣበት፣ የእግዚአብሔርንም ቸርነት ደጅ የምንጠናበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ ንስሓን ስናስብ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን መዘንጋት የለብንም። እነሱም፡- መናዘዝ፣ የሚሰጠንን ቀኖና መፈጸምና፣ ለኃጢአታችን ሥርየት የተሠዋልንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መቀበል የሚሉት ናቸው። ፩. ኃጢአትን መናዘዝ ፩. ኃጢአትን መናዘዝ

የራስን ጥፋት አውቆ ለእግዚአብሔርም ለሰውም መናዘዝ የንስሓ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መናዘዝ ስንል ሰው በአሳብ፣ በንግግር እና በተግባር በፈጸመው ኃጢአት ተጸጽቶ “እባክህ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቀኝ” ብሎ ጥፋቱን ለካህን ዘርዝሮ የሚናገርበት ሥርዓት ነው፡፡ አንድን ተነሳሒ እና ካህንን የንስሓ ልጅና አባት የሚያሰኘው ዋናው ጉዳይም ይህ ነው፡፡ የክርስቲያኖች የንስሓ አባት የመያዛቸው መሠረታዊ ዓላማም ይህ ነው፡፡ 

መናዘዝ የሚለውን ቃል ስናነሣ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ማስታወስ ይገባል፡፡ አንድ አባት ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ ከሁለቱ ልጆች መካከል ታናሹ ከአባቱ ንብረት የሚደርሰውን ተካፍሎ ለመውጣት ፈለገ፡፡ አባቱም ከሀብቱ ለልጁ ሊደርሰው ይገባል ያለውን ድርሻውን ከፍሎ ሰጠው፡፡ ልጁም ድርሻውን ተቀብሎ ወደ ሩቅ ሀገር በመሔድ ሀብቱን አባክኖ ጨረሰው፡፡ ኋላም በሚኖርበት ሀገር ጽኑ ራብ በሆነ ጊዜ ለአንድ ገበሬ የእሪያ ጠባቂ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ ረሃብ ስለጸናበትም እሪያዎች ከሚበሉት አሰር ሊመገብ ቢፈልግም የሚሰጠው አልነበረም። ረሃብ ሲጸናበት “ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በረሃብ እጠፋለሁ። ተነሥቼም ወደ አባቴ ልሔድ። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ”  አለ፡፡ ወደ አባቱ ሲሔድ አባቱ ገና ሩቅ ሳለ አይቶ አዘነለት። ሮጦም አንገቱን አቀፈና ሳመው። ጎረቤቶቹንም ጠርቶ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይበለን ብሎ ታላቅ ድግስ ደገሰ ይለናል (ሉቃ.፲፭፥ ፲፩-፴፪)፡፡ 

“

Read more: “በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ”

መርከባችን ወደቡ ላይ እንድትደርስ ሁላችንም የቀዛፊነትን ድርሻ እንወጣ።

Details
Written by: ማኅበረ ቅዱሳን
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 1059
  • መልዕክት

ለዘመናት መንገደኞቿን አሳፍራ እግዚአብሔር አምላክ ወዳዘጋጀላቸውና ተስፋ ወደሚያደርጉት ወደብ ስታደርስ የኖረችው መርከብ (ቤተ ክርስቲያን)  በፈተና ውስጥ ያላለፈችበት ጊዜ ነበር ባይባልም ዛሬ ዛሬ ግን ከሌላው ጊዜ በተለየና በከፋ ሁኔታ ማዕበሉ እየናጣት ትገኛለች። እንደሚታወቀው ይቺ መርከብ ጉዞዋ በባሕር ላይ ነው። ባሕሩ ደግሞ በታላቅ ሞገድ የሚናወጽ ማዕበል ያለበት በመሆኑ ጠንካራና ባለሙያ ቀዛፊ ካልያዛት ከነተሳፋሪዎቿ ልትሰጥም ትችላለች። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። (ዕብ. ፲፪፥፰) በማለት እንደተናገረው ምንም እንኳን ከቅጣትና ከተጋድሎ በኋላ ዘለዓለማዊ ክብር የሚገኝ ቢሆንም ይህን የቅጣትና የተጋድሎ ማዕበል ግን በትዕግሥት ማለፍን ይጠይቃል። መርከባችን በባሕሩ ላይ ያለውን ጽኑ ማዕበል  ተቋቁማ ባሕሩን ከተሻገረች በኋላ ከገቡ የማይወጡበትን ካገኙ የማያጡትን ወደብ (መንግሥተ ሰማያት) ትወርሳለች። ይሁን እንጂ እንደዚህ ካለው ወደብ ላይ ለመድረስ በባሕሩ ውስጥ ያለውን ማዕበል ማለፍ ይጠይቃል።

መርከባችን የምትናጥበት ማዕበል የእርስ በእርስ ጦርነት፣ የዓለም ጠበብቶች መድኃኒት ያላገኙለት በሽታ፣ አርሶ አደሮቹ ዓመቱን ሙሉ ሲለፉበት የከረሙበትን ሰብል አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የሚያወድም የአንበጣ መንጋ፣ ጊዜውን ባልጠበቀ ዝናም የሚከሠት የጎርፍ አደጋ፣ በመርከቢቱ ውስጥ ሥር የሰደደውና መፍትሔ ያልተበጀለት የእርስ በእርስ ክፍፍል ወዘተ. ሁሉ እጅግ የመከራ ጊዜዋን እያራዘመና የመስጠም ዕድሏን እያሰፋው ይገኛል። ስለዚህ ምእመናን የተሳፈሩባት ይህቺ መርከብ ይህን ሁሉ ተግዳሮት አልፋ ተሳፋሪዎቿንም ወደ አሰቡትና ተስፋ ወደሚያደርጉት ወደብ ለማድረስ ሁሉም እንደየድርሻው መሳተፍ ይኖርበታል። 

Read more: መርከባችን ወደቡ ላይ እንድትደርስ ሁላችንም የቀዛፊነትን ድርሻ እንወጣ።

ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ ሞቱ (ዘኊ.፲፬፥፴፯)

Details
Written by: ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 1760
  • ዐውደ ስብከት

እግዚአብሔር አምላካችን የሰውን ልጅ ከፍጥረታት ሁሉ አልቆና አክብሮ በአርአያው ሲፈጥረው ስሙን ቀድሶ ክብሩን እንዲወርስ ነው። ስሙን ቀድሶ ክብሩን ይወርስ ዘንድ የሚያስችሉ ሕዋሳትንም በሚገባ አድሎታል። የተሰጠውን ሕዋሳት በአግባቡ ቢጠቀምባቸው ክብርን ያገኛል። ዐይኑን በአግባቡ ቢጠቀምበት መጻሕፍትን አንብቦ፣ መልካም ነገርን ሠርቶ ይድንበታል፣ ይጸድቅበታል።  በአግባቡ  ካልተጠቀሙበት ግን ሞትን ያስከትላል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ትምህርት በቅዱስ ወንጌል  “ቀኝ ዐይንህ ብታስትህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሁለት ዐይና ሆነህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትገባ ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሻልሃልና” (ማቴ.፭፥፳፱) ተብሎ የተመዘገበው እግዚአብሔር በሰጠን የአካል ክፍል ልንጠቀምበትም ልንጎዳበትም እንደምንችል ሲያስተምረን ነው። የዐይንን እንደማሳያ እንደተመለከትን ሁሉ የአንደበትም የሌላውም የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲሁ ነው። በአንደበታቸው የተጠቀሙትንና የተጎዱትን በዚህ ጽሑፍ እንመለከታለን። ለዚህ መነሻ እንዲሆነን አንድ ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናንሣ።   

“ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው የተመለሱት ሰዎች ስለርስዋ በማኅበሩ ሁሉ ፊት አጕረመረሙ። ስለዚያችም ምድር ክፉን ነገር ተናገሩ፤ ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ፤ ምድሪቱ ግን መልካም ነበረች። ነገር ግን ምድሪቱን ሊሰልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ በሕይወት ኖሩ።” (ዘኊ.፲፬፥፴፮-፴፯) እንዲል። በዚህ ምንባብ ላኪ፣ ተላኪ. መልእክት፣ የመልእክት ምክንያት፣ ተላኪዎች ሲመለሱ ይዘውት የተመለሱት ጉዳይ ወዘተ ይዳሠሣሉ።

Read more: ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ ሞቱ (ዘኊ.፲፬፥፴፯)

“እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ” (ዮሐ.፲፪፥፴፪)

Details
Written by: በዲ/ን ተስፋዬ ምትኩ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 2000
  • ትምህርተ ሃይማኖት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚች ምድር የመጣው፣ ዞሮ ያስተማረውና በመስቀል ተሰቅሎ የሞተው ሁሉን ወደ ራሱ ይስብ ዘንድ ነው። በመሆኑም ወደዚህ የመጣበትንና ዓለምን ያድን ዘንድ የወደደበትን ልዩ ጥበብ  “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ” በማለት ነገረን። ይህን የጌታችንን ንግግር ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ሲያብራራው “በምን ዓይነት ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ” (ዮሐ.፲፪፥፴፫) ብሏል።

ስለዚህ ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ ማለቱ ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉን ለመናገር ነው። ወደ እኔ እስባለሁ ማለቱ ደግሞ ሰውን በግብርም በክብርም እኔን እንዲመስል አደርጋለሁ ማለቱ ነው። በግብር መምሰል ስንል የሰው ልጅ አዳምና ሔዋን የዲያብሎስ አገልጋዮች ነን ብለው በፈረሙት የዕዳ ደብዳቤ መሠረት ለ፶፻፭፻ ዘመን የዲያብሎስ ተገዥዎች ሆነው ነበር። ይህ የዕዳ ደብዳቤ ደግሞ በክርስቶስ መስቀል የሚደመሰስ መሆኑን ሲያመለክት በግብር እንዲመስሉኝ አደርጋለሁ አለ። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስይስ ምእመናን በላከው መልእክቱ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል”  በማለት እንዳስረዳን። (ቆላ.፪፥፲፬) 

Read more: “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ” (ዮሐ.፲፪፥፴፪)

አቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ

Details
Written by: ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 1893
  • እናስተዋውቃችሁ
አቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ

ትውልድ

ጻድቁ አቡነ ዮሐንስ የአባታቸው ስም የማነ ብርሃን የእናታቸው ስም ሐመረ ወርቅ ይባላል። የተወለዱበት ቦታ አክሱም ጽዮን ነው። እናቱን ሐመረ ወርቅን ያለ ፈቃዷ ለአንድ ሀገረ ገዥ ሊያጋቧት ሲሉ የአባታችን የጻድቁን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን እና የሌሎችን ቅዱሳን መቃብር ሳልሳለም አላገባም። ፍቀዱልኝና ተሳልሜ እመጣለሁ አለቻቸው። ይህን ጊዜም ከብዙ ሠራዊትና ከብዙ ገንዘብ ጋር ሰደዷት። 

ቅድስት ሐመረ ወርቅ ደብረ ሊባኖስ የእመቤታችን የሥጋዋ ፍልሰት በሚከበርባት በነሐሴ ፲፮ ቀን ደረሰች። በዚያችም ሌሊት አባታችን ተክለ ሃይማኖትን በሕልሟ አየችው። የብርሃን ምሰሶም ከፊቷ አየች። ጻድቁም ይህ የብርሃን ምሰሶ ለአንቺና ለባለቤትሽ ለየማነ ብርሃን ነው አላት። ይህንም በገዳሙ ሱባኤ የገቡ መነኰሳት ለሰባት ተከታታይ ቀናት ያህል አዩ። ያዩትንም ለገዳሙ አበ ምኔት ለአባ ዳንኤል ነገሩት። እርሱም እኔም እንደናንተ አይቻለሁ አላቸው።

የአባቱ የየማነ ብርሃን ቤተሰቦችም እንዲሁ ደጋግና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለተራበ የሚያበሉ፣ ለተጠማ የሚያጠጡ ነበሩ፣ በመጋቢት ሃያ ሰባት ቀን እመቤታችን ተገለጸችላቸውና ከልጃችሁ ከየማነ ብርሃን የብዙዎች አባት የሚሆን ደግ ልጅ ታገኛላችሁ ከጻድቁ ከተክለ ሃይማኖት በቀር የሚበልጠው የለም እናቱ ሐመረ ወርቅም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ትገኛለች  አሏቸው። ስለዚህ የየማነ ብርሃን እናትና አባት ከልጃቸው ከየማነ ብርሃን ጋር በምልክት ይፈልጓት ዘንድ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄዱ።

Read more: አቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

Details
Written by: ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 2216
  • የጥያቄያዎቻችሁ መልስ

ውድ አንባብያን በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን ትንሣኤ ሙታንን በተመለከተ  ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (በተለምዶ ብሥራተ ገብርኤል እየተባለ በሚጠራው) ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናየን ጋብዘናል። መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳንም መደበኛ መምህር ናቸው። ያነሣንላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነውልን ቆይታችንን እንዲህ አዘጋጅተነዋል፤ መልካም ንባብ።

፩ ሐመር፡- ትንሣኤ ማለት ምን ማለት ነው?

መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ፡- ትንሣኤ ማለት “ተንሥአ” ካለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን መነሣት አነሣሥ የሚል ትርጕም ይኖረዋል። ዘርፍ ሲይይዝ ደግሞ ባለቤት ይኖረዋል ማለት ነው። ለምሳሌ፡- ትንሣኤ ክርስቶስ፣ ትንሣኤ ሥጋ፣ ትንሣኤ ልቡና፣ ወዘተ. ሲል የክርስቶስ ትንሣኤ፣ የሥጋ ትንሣኤ፣ የልቡና ትንሣኤ እየተባለ ባለቤቱን እየጨመረ ይፈታል። ከውደቀት ወይም ከሞት በኋላ ያለ ሕይወትን የሚገልጽ ነው።

፪. ሐመር፡- ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢር መካከል አንዱ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ነው። ምን ማለት ነው? ምንስ የምንማርበት ነው?

Read more: የጥያቄዎቻችሁ መልስ

“መልካም ማድረግን አትርሱ” (ዕብ.፲፫፥፲፮)

Details
Written by: ዲ/ን ተስፋዬ ምትኩ
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 3907
  • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት

ኃይለ ቃሉን የተናገረው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው። ሙሉ ቃሉን ስናነበው “መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና” ይላል። (ዕብ.፲፫፥፲፮) ይህን የቅዱስ ጳውሎስን ሐሳብ ያብራሩት መተርጕማነ መጻሕፍት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም “ለነዳያን መመጽወትን አትተዉ እናንተ በመስጠት እነሱ በመቀበል አንድ መሆናችሁንም አትርሱ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና” ብለዋል። (የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው ፲፱፻፵፰ ዓ.ም ገጽ ፬፻፸)

የመልካምነት መገለጫዎች ብዙ ናቸው። በርግጥ እንደየ ሰዉ አመለካከት፣ እምነትና ባህልም ይለያያል። ከዚህም የተነሣ ለአንዱ መልካም የሆነው ለሌላ ክፉ የሚሆንበት አጋጣሚም ብዙ ነው። በዙህም መሠረት እንደ ክርስትና ግን ነገሮችን መልካምና ክፉ፣ ኃጢአትና ጽድቅ፣ ጥሩና መጥፎ፣ ክብርና ውርደት፣… ብለን የምንለየው ሕግጋተ እግዚአብሔርን መሠረት አድርገን እንጂ የሰዎችን ባህልና አስተሳሰብ ወይም ዕድገትና ትምህርት መሠረት በማደረግ አይደለም። 

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋዕለ ሥጋዌው አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀርቦ “መምህር ሆይ፥ የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ?” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ” በማለት ነበር የመለሰለት። (ማቴ.፲፱፥፲፮-፲፯) 

Read more: “መልካም ማድረግን አትርሱ” (ዕብ.፲፫፥፲፮)

የፍስክ ብፌ

Details
Written by: በደመላሽ ኃ/ማርያም
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 2141
  • ኪነ ጥበብ

ብዙ ተማሪ ሲተራመስበት የነበረው ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን በሆዱ ከቶ ጭጭ ብሏል፡፡ እስከ መጨረሻው ክፍት ብሎ የነበረው በር የሚያስፈልገውን ያክል ተማሪ ከቶ ተዘግቷል፡፡ ከአርፋጅ ተማሪዎች ጋር ሲሯሯጡ የነበሩት ዩኒት ሊደርና ጥበቃዎች እፎይ ብለዋል፡፡ ጥበቃው አለሁ ለማለት ያህል ትልቁን የወታደር ከስክስ ጫማቸውን በከፊል ከውጭ አድርገው ጋደም ብለዋል፡፡ ለዐይነት ያህል የተማሪዎቹን ጫጫታ ለመርሳት በብዛት እሽ የምትል ሬዲዮናቸውን ከጆሯቸው አፋፍ አስቀምጠው ይሰማሉ፡፡ ዩኒት ሊደሩ የብዙ ሴትና ወንድ ተማሪዎችን መቀመጫ የቸበቸበች አርጩሜያቸውን ጥለው ጣታቸውን ለብዕር ሰጥተዋል፡፡ ቅጥር ግቢው ውስጥ በየክፍሉ ዕወቀትን ለማጋባት ከሚውተረተሩት መምህራን ድምፅ ውጪ ዝም ብሏል፡፡

       ሰሙነ ሕማማት በመሆኑና ኮሮና ቫይረስም በጋራ አልያችሁ ስላለ የከተማው ሰው ራሱን ከችግር ለመከላከል ከቤቱ ከቷል፡፡ ገሚሱ ከበሽታ ሽሽት፤ ገሚሱ ሥጋውን እየጎሰመ ፈጣሪውን ይቅር በለኝ ብሎ በስግደትና በጾም ለመለመን፡፡ በዚህ መካከል ታዲያ እውነትም የቫይረሱን አደገኛነት እና ገዳይነት ካልተረዱ ወጣቶች ውጪ እምብዛም የሰው ትርምስ አይታይም፡፡ 

Read more: የፍስክ ብፌ

አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ክፍል ሁለት

Details
Written by: ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ እንደሰበከው
Category: ሐመር በመስመር ላይ
Published: 28 April 2021
Hits: 2164
  • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን

ውድ አንባብያን ባለፈው እትማችን ቤተ ክርስቲያን ማን ናት? የሚለውን መሠረታውዊ ዕውቀት መረዳት ይቻል ዘንድ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ የሰበከውን ተከታታይ ጽሑፍ እንደምናቀርብ ቃል ገብተን የመጀመሪያውን ክፍል አቅርበንላችኋል። በመጀመሪያው ክፍልም የቤተ ክርስቲያንን ምንነት፣ የቤተ ክርስቲያን ባሕርያት አራት እንደሆኑ፣ ከእነዚህም መካከል ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት። የሚለውን ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ ወር እትማችን ድግሞ ከባለፈው የቀጠለውንና ሁለተኛውን የቤተ ክርስቲያን ባሕርይ “ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት” የሚለውን አቅርበንላችኋል። መልካም ንባብ፡-

አንድ ሰው ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲያስብ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ማሰብ የለበትም። በፖለቲከኞች ውስጥ አንድ የሚያደርግ  ምንም የእግዚአብሔር መንፈስና ረቂቅ ኃይል የለም። ምድራዊና ጊዜያዊ ዓላማ፣ አሠራርና አስተሳሰብ ነው የሚያሰባስባቸው። በክርስትና ግን እንደዚህ አይደለም፤ በክርስትና ትልቁ ነገር ከእግዚአብሔር ጋራ እንድ መሆን ነው። አሁን ተመልከቱ ክርስቶስ ሳያድርብን ስለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ነው እኛ መቆርቆር የምንችለው? አናስብ ማለት አይደለም ግን ሐሳባችንን እንኳን በየትኛው መንገድ ልናቀርብ እንደሚገባን እንድናውቅ ነው። አንድ ሰው ንስሐ ሳይገባ፣ ሳይቈርብ፣ እውነተኛ ሳይሆን፣ ክርስቶስ በእርሱ ሳያድር እንዴት ሆኖ ስለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መናገር ይችላል? በጣም ከባድ ነው። በመናገራችን አንድነቱ የሚመጣ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፤ በመናገራችን ሳይኾን የክርስቶስ በመሆናችን ነው አንድነቱ የሚመጣው። በሁላችንም ክርስቶስ ከአደረ፥ የክርስቶስ ማደሪያ ከኾንን አንድ መሆናችን አይቀርም። አሁን ከክርስቶስ የተለየን ሽፍቶች ተጣልተን ምን አንድነት ልናመጣ እንችላለን? ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት በዚህ አንድነት ማመን አለብን። ክርስቶስ እንዳለው እርሱ በእኛ ማደር ይፈልጋል፤ ለሚያንኳኳው ጌታ የልባችንን በር ከፍተን ልናስገባው ያስፈልጋል። 

Read more: አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ክፍል ሁለት

Page 1 of 9

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት