Friday, 11 December 2020 00:00

ለአርመንያ ክርስቲያኖች የርዳታ ጥሪ ቀረበ

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

በናጎሮን ካራባክህ ከአራስፅካህ ለተፈናቀሉ የአርመንያ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች “ችልድረንስ ፈንድ ፎር አርመንያ” የተባለ ግብረሠናይ ድርጅት ዓለም አቀፍ የርዳታ ጥሪ ማቅረቡን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል፡፡  ለአርመናውያን ፪፻፳ ዓ.ም አስቸጋሪና እጅግ ፈታኝ ወቅት እንደነበረ ያነሣው ግብረሠናይ ድርጅቱ ፈተናው ለአራስፅካህ አርመናውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አርመናውያን ችግር ነው ብሏል፡፡ አያይዞም “ከቅርብ ወራት በፊት በአዘርባጃንና በአርመንያ መካከል በተደረገው ጦርነት አርመናውያን ዘመዶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ቤቶቻቸውን፣ አካሎቻቸውን አጥተዋል” ሲል ድርጅቱ አስታውቆ “በርካታ ሕፃናት ወላጅ አልባ ከመሆናቸው በተጨማሪ አያሌ ቤተሰብም በድንገት ተበትኗል” ሲል ገልጧል፡፡ በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት ሁሉም አርመናውያን የገንዘብና የሥነ ልቡና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ድርጅቱ አስርድቷል፡፡ በተለይ በጦርነቱ የተጎዱ አርመናውያን ሕፃናትንና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ብሔራዊ ግዴታ መሆኑንም አስተውቋል፡፡  ድርጅቱ በተለይ ካናዳ የሚኖሩ አርመናውያን በጦርነቱ ቤተሰቦቻቸው ለሞቱባቸው፣ ለቆሰሉባቸውና ለጠፉባቸው አፋጣኝ ርዳታ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ እግዚአብሔር አርመናውያንን እንዲጠብቅና በመላው ዓለም ሰላም እንዲሰፍን እንደሚጸልይም ገልጧል፡፡   
Read 218 times