Saturday, 07 August 2021 00:00

አጫጭር ዜና

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

በካናዳ ሹሪ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት የሚገኘው የግብጽ ኮፕቲክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንፃ ቤተ ክርቲያን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጂ አስነበበ፡፡      ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት በቅርብ በእሳት መቃጠሉን ዘገባው ያስረዳ ሲሆን ካለፈው ረዕቡ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኑ የጥቃት ዒላማ ሆኖ መቆየቱንም የአካባቢው የፖሊስ አካላት እንደተናገሩ ተገልጧል፡፡    የሚና ሚሲሳውጋ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖሊስ ጉዳዩን በፍጥነት መርምሮ እንዲያሳውቅ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታውቆ ድርጊቱ በራሱ ጥያቄ የሚያስነሣ ከመሆኑ ባሻገር የሚመለካታቸው የመንግሥት አካላት እሳቱን ቶሎ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡ የተቃጠለው የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የግብጽ፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሊባኖስ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በጋራ ይገለገሉበት እንደነበረ ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡    የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ ኦሬንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡

 

Read 350 times