Thursday, 26 August 2021 00:00

ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ የነበረው ጥቃት መባባሱ ተገለጠ

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት የታሊባን ታጣቂዎች በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረውን ጥቃት ማባባሳቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡      ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ሪፖርቶችን ዋቢ አድርጎ ዘገባው እንዳስረዳው በአፍጋኒስታን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በነጻነት የማምለክ ሕጋዊ ፍቃድ የተሰጠው በጣሊያን ኢምባሲ ለሚገኘው የሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡  ኦፕን ዶርስ የተባለውን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ዘገባው እንዳስታወቀው አፍጋኒስታን በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ጠቀምጣለች፡፡  በአሁኑ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎችና መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ  ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ከአፍጋኒሰታን የወጡ ሲሆን በምዕራብ አፍጋኒስታን ፓርቲን ግዛት የሚገኘው የሐዋሪያው ቅዱስ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ጊዜዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ከዘገባው መረዳት ተችሏል፡፡   
Read 485 times