Friday, 04 September 2020 00:00

በሩሲያ ምሥጢራዊ መረጃ  በሚያወጡ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ ቅጣት ሊጣልባቸው ነው

Written by  ካሳሁን ለምለሙ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቷን ምሥጢራዊ መረጃ አውጥተው ለሚዲያ ፍጆታ በሚያውሉ መነኰሳትና ቀሳውስት ላይ ጠንካራ ርምጃ እንደሚወስድ ኦርቶዶክስ ታይምስ ዘገበ፡፡  የቤተ ክርስቲያኒቷን ምሥጢራዊ መረጃ በሚያወጡ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ የማያዳግም የርምት ርምጃ እንደሚወስድ የጠቆመው ዘገባው ይህ የሆነበት ምክንያት ውስጣዊ የቤተክርስያኒቷ ምሥጥራዊ  መረጃ ለሦስተኛ ወገን ተጋላጭ እንዳይሆኑና አግባብ ላልሆነ የሚዲያ ፍጆታ እንዳይውሉ  ለመከላከል ነው ተብሏል፡፡  ድርጊቱን ፈጽመው በተገኙ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ ለአንድ ወይም ለሦስት ዓመታት ያህል ከሃይማኖታዊ አገልግሎት እንዲሚገለሉ ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመሆኑም መነኰሳቱም ሆኑ ቀሳውስቱ መረጃዎችን ይፋ ሊያደርጉ የሚችሉት ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከሊቃነ ጳጳሳት ፍቃድ ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ተመላክቷል፡፡  የየትኞቹን መረጃዎች ምሥጢራዊነት መጠበቅ እንደሚገባ ግራ የተጋቡት አንዳንድ የቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስቱና መነኰሳቱ የቀሳውስትን የግል ጉዳይ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷን የተመለከቱ ከፍተኛ የወንጀል ድርጊቶችን ምሥጢራዊነት መጠበቁ ያላስደሰታቸው  ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወሰነው ውሳኔ እንዴት ሥራ ላይ እንደሚውል፤ ጥቅሙንና ዓላማውን ጭምር ለመረዳት እንደሚፈልጉ ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡   
Read 419 times