Friday, 06 August 2021 00:00

ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ለባህል ዋጋ የሚሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ ሊደግፉ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ለባህል ዋጋ የሚሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ መደገፍ እንደሚገባቸው ጥሪ መቅረቡን ኦርቴዶክስ ኮግኔት ፔጅ በገጹ አስነበበ፡፡  በቅርቡ በኤይ  ኤን ኤስ ሲ ኦፒ አማካይነት በተጠናው ጥናት መሠረት ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ባህል ልዩ ትኩረት የሚሠጠውን ሀገር አቀፍ ወግ አጥባቂ ፓርቲን መደገፍ እንዳሰቡ ዘገባው አስረድቷል፡፡  የሮማንያውያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ በጣም ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ስትሆን ቤተክርቲያኗ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዳንኤል ትመራለች፤ቅዱስነታቸውም የምእመናንን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጥቅሞችን ከማስጠበቅ አኳያ የላቀ አገልግሎት እየፈጸሙ መሆናቸውን ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል፡፡     
Read 427 times