Monday, 09 November 2020 00:00

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታወቀ

Written by  በካሣሁን ለምለሙ
የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታወቀ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኢሪንጀ ሰሞኑን በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል፡፡ ቅዱስነታቸው በዚህ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው አስታውሶ ቤልግሬድ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ሕክምና ማእከል ውስጥ ተገቢው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቅዱስነታቸው ከዚህ ቀደም በሀገራችን ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች አካባቢዎች በቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያወገዙ ሲሆን በሀገራቸው አምባሳደር በኩልም ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን አጋርነት ማሳየታቸው ይታወሳል፡፡  
Read 631 times