Friday, 11 December 2020 00:00

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ካራኪን ዳግማዊ ከአራስፅካህ የተፈናቀሉ ክርስቲያኖችን ጎበኙ

Written by  ካሳሁን ለምለሙ

Overview

የአርመንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ካራኪን ዳግማዊ በአርመንያና በአዘርባጃን መካከል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ምእመናንን መጎብኘታቸው ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነብቧል።   ከወራቶች በፊት በነበረው ጦርነት ምክንያት በርካታ አርመንያውያን ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች አካባቢያቸውን ለቀው በአርመንያ ባሉ አህጉረ ስብከት በሚገኙ አጥቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።  ቅዱስ ፓትርያርኩም ክርስቲያኖች ተጠልለው ከሚገኙበት ቦታ በአንዱ ተገኝተው ያጽናኑ ሲሆን ተገቢው ጥበቃና ክብክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንን ማረጋገጥ እንደቻሉ ዘገባው አመልክቷል።   የአርመንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለተፈናቃዮች የምግብ፣ የልብስና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን እያደረገች ሲሆን ተጨማሪ ርዳታ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ካለ ደግሞ ‹‹የእችሚአዳጊን ጓደኞች›› በሚለው አድራሻ በኩል ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።   
Read 599 times