በሩሲያ መንግሥት ድጋፍ በሶሪያ መለስተኛ የሆነ አዲስ የሐግያ ሶፊያ ቤተመቅደስ ሊገነባ እንደሆነ ኦርቶዶከስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል፡፡
ቤተመቅደሱ የሚገነባው በርካታ የግሪክ ኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ክርስቲያን በሚኖሩባት አል ሱቋአያላቢያህ ሲሆን ግንባታውም በቅርቡ ተጀምሮ በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ዘገባው አመልክቷል፡፡
በቱርክ የሚገኝው ጥንታዊውና ታሪካዊው የሐግያ ሶፊያ ቤተመቅደስ ከርጅም ጊዜ በኋላ በቱርክ መንግሥት እምቢተኝነት የቤተመቅደሱ ይዘት በተወሰነ ደርጃ ተለውጦ በይፋ ወደ መስጅድነት ተቀይሮ ለሕዝበ ሙስሊሙ ማምለኪያነት እንደዋለም ዘገባው አስታውሷል፡፡