- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1080
የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት የታሊባን ታጣቂዎች በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረውን ጥቃት ማባባሳቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡
ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ሪፖርቶችን ዋቢ አድርጎ ዘገባው እንዳስረዳው በአፍጋኒስታን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በነጻነት የማምለክ ሕጋዊ ፍቃድ የተሰጠው በጣሊያን ኢምባሲ ለሚገኘው የሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡
ኦፕን ዶርስ የተባለውን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ዘገባው እንዳስታወቀው አፍጋኒስታን በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ጠቀምጣለች፡፡
በአሁኑ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎችና መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ከአፍጋኒሰታን የወጡ ሲሆን በምዕራብ አፍጋኒስታን ፓርቲን ግዛት የሚገኘው የሐዋሪያው ቅዱስ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ጊዜዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ከዘገባው መረዳት ተችሏል፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1165
የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት የታሊባን ታጣቂዎች በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረውን ጥቃት ማባባሳቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡
ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ሪፖርቶችን ዋቢ አድርጎ ዘገባው እንዳስረዳው በአፍጋኒስታን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በነጻነት የማምለክ ሕጋዊ ፍቃድ የተሰጠው በጣሊያን ኢምባሲ ለሚገኘው የሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡
ኦፕን ዶርስ የተባለውን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ዘገባው እንዳስታወቀው አፍጋኒስታን በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ጠቀምጣለች፡፡
በአሁኑ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎችና መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ከአፍጋኒሰታን የወጡ ሲሆን በምዕራብ አፍጋኒስታን ፓርቲን ግዛት የሚገኘው የሐዋሪያው ቅዱስ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ጊዜዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ከዘገባው መረዳት ተችሏል፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1155
አሸባሪው ሸኔ ከተባባሪዎቹ ጋር በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ኪረሙ ወርዳ ቤተ ክህነት በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ ኦርቶደክሳውያን ክርስቲያኖችን የማጽዳት ተግባር እየፈፀመ መሆኑን የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች ገለጡ፡፡
ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ አንድ የአካባቢው የሃይማኖት አባት እንደተናገሩት “ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ/ም በኪረሙ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኙ የሳደሮ ቅዱስ ገብርኤልና ኩቲ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በቅዳሴ ላይ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንን በሙሉ የሽብር ቡድኑ ገድሏቸዋል” ብለዋል፡፡
በምእመናንና በአገልጋዮች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት አሁን የተጀመረ እንዳልሆነ ያስታወቁት እኒህ የሃይማኖት አባት በዚህ ወቅት የተፈጸመው ጥቃት ግን ከዚህ በፊት ከነበረው የባሰ ነው፡፡ ሰሞኑን በጭካኔ የተገደሉት ምእመናን አብዛኛዎቹ በቅዳሴ ላይ እንዳሉ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከቅዳሴ መልስ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
አሁን ባለው መረጃ መሠረት ሥልሳ ያህል ምእመናን መገደላቸውን ያረጋገጡት የአካባቢው የሃይማኖት አባት የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችልና ከሞት የተረፉትም በየጫካው ሸሽተው እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
የኪረሙ ወረዳ ሦስት ቀበሌ ምእመናን በሙሉ ለሞት፣ ለስደት፣ ለሀብት ንብረት ውድመትና ዘረፋ እንደተዳረጉ የስታወቁት እኒህ የሃይማኖት አባት አካባቢው ወደቀደመ ሰላሙ ቢመለስ እንኳን የሚበሉት ምግብና የሚጠለሉበት ቤት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
የችግሩን ውስብስብነትና ከአቅም በላይ መሆኑን ለክልሉ መንግሥት ያስረዱ መሆኑን ያስታወቁት እኒህ አባት በሕይወት የተረፉ ምእመናን ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲሄዱ የሽብር ቡድኑ የዘጋውን የቡሬ መንገድ መንግሥት እንዲያስከፍት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሌላው የሀገረ ስብከቱ አገልጋይ የሆነው ወጣት በበኩሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታዋቂ ባለሀበት ምእመናንና ሌሎች በሽብር ቡድኑ እንደታገቱ ገልጦ አጠቃላይ ጥቃቱ ዘርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አገልጋዩ አያይዞም በዚህ ዓመት በነሐሴ ወር ብቻ የዐስራ ስድስት ምእመናን ከብቶች እንደተዘረፉባቸው ጠቁሞ በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ ባለፀጋ ምእመናን እየታደኑ እንደተገደሉም አስገንዝቧል፡፡ የሽብር ቡድኑ ዋና ዓላማ ክርስቲያኖችን ከአካባቢያቸው በማጽዳት ቤተ ክርስቲያን እንዲዘጋና አገልግሎት እንዲቆም ማድረግ መሆኑን አክሏል፡፡
በተጨማሪም ሸኔ በምእመናን ላይ ካደረሰው ጭፍጨፋ ባሻገር ከሌላ የተለያዩ ቀበሌዎች ተደራጀተው የመጡ ወጣቶች የኩቲ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ መዝረፋቸውን አገልጋዩ ተናግሯል፡፡
በመጨረሻም ከዚህ ቀደም በሽብር ቡድኑ እጅ የበርካታ ካህናትና ዲያቆናት ሕይወታ እንደጠፋ ያስረዳው አገልጋዩ ይህ ድርጊትም ሆን ተብሎ ቤተ ክርስቲያንን የመዝጋትና አጠቃላይ የምሥራቅ ወለጋ የገጠሩን ክፍል ከኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የማጽዳት ተግባር መሆኑን በአጽኖት አስረድቷል፡፡ ከሞት የተረፉ ካህናትና ዲያቆናት በሕይዎት የመኖር ዋሰትና ወደሚያገኙበት አካባቢዎች መሰደዳቸውንም አክሏል፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 629
በካናዳ ሹሪ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት የሚገኘው የግብጽ ኮፕቲክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንፃ ቤተ ክርቲያን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጂ አስነበበ፡፡
ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት በቅርብ በእሳት መቃጠሉን ዘገባው ያስረዳ ሲሆን ካለፈው ረዕቡ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኑ የጥቃት ዒላማ ሆኖ መቆየቱንም የአካባቢው የፖሊስ አካላት እንደተናገሩ ተገልጧል፡፡
የሚና ሚሲሳውጋ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖሊስ ጉዳዩን በፍጥነት መርምሮ እንዲያሳውቅ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታውቆ ድርጊቱ በራሱ ጥያቄ የሚያስነሣ ከመሆኑ ባሻገር የሚመለካታቸው የመንግሥት አካላት እሳቱን ቶሎ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡
የተቃጠለው የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የግብጽ፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሊባኖስ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በጋራ ይገለገሉበት እንደነበረ ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ ኦሬንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡
- Details
- Written by: በዝግጅት ክፍሉ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1014
በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓል ጠብቀው ጃንጥላ በመዘርጋት፣ ጨርቅ በማንጠፍ እንዲሁም ቄጠማ በመጎዝጎዝ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚለምኑ ግለሰቦች እና ቡድኖች እየተበራከቱ መጥተዋል። በአለባበሳቸው የቤተ ክርስቲያን ሰዎች መስለው ፤ቤተ ክርስቲያን እንደላከቻቸው አድርገው የሐሰት ደብዳቤ በማዘጋጀት እከሌ የተባለው ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ ከፍጻሜ እንዲደርስ ለማድረግ፤ በእርጅና ምክንያት እየፈረሰ ያለውን እከሌ የተባለ ገዳም ለማሳደስ . . . ወዘተ የሚሉ ምክንያቶችን በመደርደር ከምእመኑ ገንዘብ የሚሰበስቡ በርካቶች ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን፣ የእመቤታችንን፣ የቅዱሳንን፣ የሰማእ,ዕታትን እና የመላእክትን ሥዕለ አድኅኖ በመያዝ እና በስማቸው በመለመን ከምእመኑ የሚሰበስቡት ገንዘብ የትየለሌ ነው፡፡
በዚህ ሴቶች፣ ወንዶች በአጠቃላይ ከምእመን እስከ ካህን (እውተነኛ ናቸው ወይ? የሚለው አጠያያቂ ሆኖ) በሚሳተፉበት እና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም በሚደረገው የመንገድ ላይ ሕገወጥ ልመና ከሚገኘው ገንዘብ ቤተ ክርስቲያን እየተጠቀመች ነው ወይ? ገንዘቡስ ለታለመለት አላማ ይደርሳል? የሚል ጠያቂ ቢኖር የግለሰቦችን አሊያም የቡድኖችን ኪስ ከማደለብ ውጪ ሌላ ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም አንዳች ነገር እንደሌለው በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ረጅም ርቀት ላይ ሣር ጎዝጉዘው እና ድምጽ ማጉያ ይዘው ለማስቀደስ አሊያም ለማንገሥ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄደውን የዋህ ምእመን ከመንገድ አስቀርተው እጅ የሚያዘረጉ ባሕታውያን ሳይሆኑ ባሕታውያን ነን የሚሉት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ‹‹እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ! እናንተም አትገቡም ፤የሚገቡትንም ከመግባት ትከለክሉአቸዋላችሁ›› (ማቴ. ፳፫፥፲፬) የተባለባቸው ወደ ቤቱ የሚገሰግሱትን ከመንገድ አስቀርተው ከበረቱ ውጪ በማለማመድ የራሳቸውን ኪስ እያደለቡ ሆዳቸውን የሚሞሉትን ተው የሚላቸው ማን ይሆን? የጅምር ቤተ ክርስቲያን ፎቶግራፍ ይዘው በየንግሡ ‹‹የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማስጨረሻ›› እያሉ በየዓመቱ ገንዘብ በከረጢት የሚሰበስቡ አዛውንት እናቶችን ለልመናቸው ገንዘብ ከመለገስ ውጪ ‹‹ሕንጻው ምን ላይ ደረሰ? የሚል ጠያቂ የለም፡፡
በእርግጥ ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ አሊያም ለማሳነጽ ገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ በእውነተኛ መንገድ የቤተ ክርስቲያንን ትክክለኛ መረጃ ይዘው በትክክለኛ ሰነድ ገንዘብ የሚሰበስቡ ምእመናን፣ አባቶች፣ እናቶች የሉም ለማለት አይደለም። ነገር ግን በከተማው ውስጥ ሚዛን ደፍቶ የሚታየው ሕገወጥ ለማኞች መሆናቸውን ስንቱ ተገንዝቦት ይሆን?ሁሉም ለለማኙ ክፍል ገንዘብ ከመስጠቱ ባሻገር የሚለምኑላቸው አብያተ ክርስቲያናት መታደሳቸውን፣ መሠራታቸውን አልያም ለውጥ ማሳየታቸውን ጠያቂ የለም፡፡ ቢያንስ የሚለምኑለት ደብር የት እንደ ሆነ ትክክለኛ መረጃቸውን ለማረጋገጥ ሙከራ የሚያደርግም የለም፡፡ በዓላትን ጠብቀው ብቅ የሚሉት የቤተ ክርስቲያን አዛኝ የሚመስሉት ዣንጥላ ዘርጊዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ለምነው የምእመናንን ኪስና መቀነት አራግፈው የራሳቸውን ኪስ እና ቤት ሲሞሉ ተው የሚላቸው አካል ሊኖራቸው ይገባል፡፡
የተደራጀ እና ምሉእ መዋቅር ያላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እዚያው ደጃፍዋ፣ ጉያዋ ሥር ተወሽቀው በስምዋ የሚነግዱትን እንዲሁም ሰድበው ለሰዳቢ አሳልፈው የሚሰጥዋትን የቤተ ክርስቲያን እንቅፋቶች መቆጣጠር ከርስዋ የሚጠበቅ ነው፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 633
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሀገራችን በኪነ ጥበብ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ሕንፃ ዘርፍ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ላቅ ያለና ዘመን የማይሽረው ነው።ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ዘመን ጀምሮ ለሀገርና ለወገን የሚበጀውን ተግባር ሁሉ ስትፈጽም ቆይታለች። ይህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በረጅም ጊዜ ታሪኳ ለሀገርና ለትውልድ ያበረከተችውንና እያበረከተችው ያለችውን ታላቅ አስተዋጽኦ ለመረዳት ያስችላል። በተለይም ሀገራችን በሀገር በቀል ዕሴቶች እንድትገነባና ትውልዱ በሥነ ምግባር ታንጾ ለሀገሩና ለሕዝቡ ታማኝና ተቆርቋሪ ሆኖ እንዲያድግ አድርጋ ከማሳደግ አኳያ የማይተካ ሚና መጫወቷን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው።ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት ረገድ እንዲሁ ለዓለም ያበረከተችው የሃይማኖት፣የሥነ ምግባር፣ የዕውቀት ወዘተ ለውጥ ዓለማችን በዕውቀትና በሥልጣኔ ጎዳና እንድትጓዝ ለማድርግ አብቅቷታል።ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም አስቀድማ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተለይታ የራሷ ፊደል፣ አኀዝ እና የዘመን አቆጣጠር እንዲኖራት ያስቻለች የሀገር ባለውለታ ናት።የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ማዕከል ከመሆኗም ባሻገር ምጣኔ ሀብታዊ፣ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ሥነ ጥበባዊ ጠቀሜታ ያላቸው የበርካታ ቅርሶች ባለቤት መሆኗም ይታወቃል፡፡
- Details
- Written by: መጽሐፈ ሲራክ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 607
የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ክፍል ከዚህ በፊት በነበረው ተከታታይ እትም ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ሦስተኛውንና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
በደርግ ዘመን ጃንሆይን ገፍተው ጥለው ‹‹እግዜር የለም›› የሚል ሥርዓት እና መሪ መጣ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አድሃሪ ናት ተብላ ንብረቶቿ በሙሉ ተወረሱ፡፡ እንደሚታወቀው ፍልስፍናው ግራ እጅ አውጥቶ ‹‹እናሸንፋለን›› ነው እንጂ እግዚአብሔር ይመስገን ማለት አይባልም ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ለጉዳይ ስንሄድ አቤቱታችንን ይሰማሉ፣ ያልናቸውን ለመፈጸም ይሞክራሉ፡፡ እንዲያውም ፍልስፍናው ስለሚያስቸግራቸው በይፋ አይናገሩ እንጂ በእምነት ጉዳይ አንዳንዶቹ ህሊናቸው ቅር እያለው እንደሆነ ይታወቃል። ልጆቻቸው ክርስትና እንዳይነሱ
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 623
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሆኑት ሚስተር ሰርጂ ላቭሮቭ የመካከለኛው ምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ ክርስቲያኖችን ከጥቃት በመከላከል ዙሪያ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ ማቅረባቸውን የሩሲያን መገናኛ ብዙኃን ዋቢ አድርጎ ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘገበ፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሞስኮ መንበረ ፓትርያርክ የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በቅንጅት ጉባኤ ሊያካሄዱ መሆኑን ሚስተር ላቭሮቭ ማስረዳታቸውን ዘገባው አስታውቆ በጉባኤውም የሮማን ካቶሊክ፣ የሀንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ የቤላሩስ፣ የሊባኖስና የአርመን እንዲሁም የሚመለከታቸው የሌሎች ሀገራት ተወካዮች እንደሚገኙ ተገጧል፡፡
በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ያሉ ክርስቲያኖች በሚደረስባቸው ተደጋገሚ ጥቃት አካባቢያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ላቭሮቭ ማስታወሳቸውን ያስገነዘበው ዘገባው በኢራቅ፣ በሊቢያ እንዲሁም በሶርያ የሚገኙ ክርስቲያኖች በከፋ ሁኔታ መገኘታቸው ታውቋል፡፡
የሶርያ አረብ ኅብረት ክርስቲያኖችን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ መጠቆማቸውን ያስገነዘበው ዘገባው “የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለተጎጂ ክርስቲያኖች ድምፅ ከመሆን በተጨማሪ በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ ርምጃ በመውሰድ የክርስቲያኖችን ሞትና ስደት ማስቆም ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡
Read more: የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስቲያኖችን ከጥቃት በመከላከል ዙሪያ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ አቀርቡ
- Details
- Written by: እህተ ሚካኤል
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 535
- Details
- Written by: ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1034
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ከገዢዎች ጋር የነበራት ትስስር የሚመነጨው እነርሱ ክርስቶስን ከሚፈልጉበት የሕይወት ርምጃና ንግሥናቸውን እንድትባርክ መሻት ባደረባቸው ጊዜ ነበር፡፡ ነገሥታቱ እና የነገሥታቱ ባለሟሎች በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ የክርስትና ተቀባይና አስፋፊ ስለነበሩ የሃይማኖት አገልጋይነታቸውን ከቤተ መንግሥት አገልግሎታቸው ለይቶ ለማየት ያስቸግር ነበር፡፡ የፖለቲካ መርኆቻቸው፣ የአመራር ጥበባቸው፣ ርዕዮተ ዓላማቸው የሕግና የአስተዳደር ይዞታቸው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከነበሩ ከእነርሱ ከራሳቸው ምንጭ ስለነበር በዘመኑ ፖለቲካዊ አስተሳሰባቸውንና ሃይማኖታዊ ሕይወታቸው ጥብቅ ቁርኝጥ ነበረው፡፡ ኑሮአቸው ሁሉ ስለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ነበር፡፡
- Details
- Written by: በዝግጅት ክፍሉ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 765
የተወደዳችሁ የስምዐ ጽድቅ አዘጋጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ስሜ ወለተ ሰማዕት ይባላል ባለትዳር እና የሦስት ልጆች እናት ነኝ፡፡ ስምዐ ጽድቅ ላይ የሚወጡ ጽሑፎችን ተከታትዬ አነባለሁ በዚህም ብዙ መንፈሳዊ ዕውቀት አግኝቼበታለሁ፡፡ በተለይ ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ዐምድ ላይ የሚወጡ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ብዙ ቁም ነገሮችን አስጨብጠውኛል፡፡ እኔም ለዘመናት ውስጤን ሲረብሸው የነበረውን እና መፍትሔ ያላገኘሁለትን ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡ ውስጤን ሰላም ለነሳው ጥያቄዬ የሚያሳርፍ መልስ ትሰጡኛላችሁ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 448
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያልተበረዘና ያልተከለሰ እንዲሁም ወጥ የሆነ የአምልኮና የአስተዳደር ሥርዓት ያላት ናት፡፡ ይህም በዓለማችን ካሉት አጠቃላይ አብያተ ክርስቲያናት የተለየች ያደርጋታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷንና ትውፊቷን ለማስቀጠል የተለያዩ ተቋማትን መሥርታ እንቅስቃሴ ከጀመረች ዘመናትን አስቆጥራለች፡፡ ካሏት የአስተዳደር ክፍሎች በተጨማሪ በፈቃደኝነት በቤተ ክርስቲያን ሕግና ደንብ የተመሠረቱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ለምእመናን ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በተለያየ መልኩ ሲደግፉ ይታያሉ፡፡በርካታ ማኅበራት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር ተመሥርተው የቤተ ክርስተያንን አገልግሎት ለመደገፍ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ ቀላል የማይባሉ ጊዜያትን አሳልፈዋል፡፡ በሀገራችን ከመንፈሳዊ ማኅበራት እንቅስቃሴ አንፃር ስንመለከት ከዛሬ ሠላሳ ዓመታት ወዲህ በይፋ የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ለአብነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ማኅበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በሁለንተናዊ ዘርፍ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሲደግፍ ቆይቷል፡፡
በተለይ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች መካከል ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል፡፡ ማኅበሩ በአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ላይ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲኖራቸው በማድረግ አብነት ትምህርት ቤቶች ያሏቸውን ደግሞ እንዲሁም በሰው ኃይልና በቁሳቁስ የማጠናከር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡
ገዳማዊ ሥርዓቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ እና ገዳማት ራሳቸውን በገቢ እንዲችሉ ለማስቻል ጊዜያዊና ዘላቂ ድጋፎችን አድርጓል፡ እያደረገም ይገኛል፡፡ ገዳማውያን በዕለት ጉርስ በዓመት ልብስ እጦት እንዳይበተኑ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሀብት ሰብስቦ እገዛ ያደርጋል፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ረገድም ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ሰባክያነ ወንጌል እንዳታጣ በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ዝግጅት ክፍላችንም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ ከሆኑን ዲ/ን አንድነት ተፈራ ጋር በክፍሉ አጠቃላይ አገልግሎ ዙሪያ አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ ከኃላፊው ጋር ያደረግነውን ቆይታም በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- የክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት ምን ምን ናቸው?
ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ በዋናነት በትኩረት እየሠራ የሚገኘው አብነት ትምህርት ቤቶችና በገዳማት ላይ ነው፡፡ ክፍሉ ለገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ከጊዜያዊ ድጋፍ ጀምሮ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ቋሚ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች በሰው ሠራሽ፣ በተፈጥሮና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ተጎጂ ሲሆኑ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ጊዜያዊና ቋሚ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ለገዳማቱ የቀለብ፣ የአልባሳት፣ የንዋ ቅድሳት እንዲሁም የተለያዩ የመባ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡ እንደሚታወቀው የአብነት ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ‹‹በእንተ ስማ ለማርያም›› ብለው በሚያኙት ቁራሽ ይማሩ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ለምኖ የመማር ባህሉ እየተቀየረ በመምጣቱ የአብነት ተማሪዎች ለከፋ የቀለብ እጥረት ይጋለጣሉ፡፡ ስለሆነም ክፍሉ ለአብነት ተማሪዎች የቻለውን ያህል የቀለብ አቅርቦት ያደርጋል፡፡ ድጋፍ በመደረጉም በተወሰነ ደረጃ የሚዘጉ የአብነት ትምህርት ቤቶችን መታደግ ተችሏል፡፡ ጉባኤያትን ከመታጠፍ፣ ተማሪዎችን ከመበተንና ከመፍለስ የመታደግ ሥራ ተሠርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ባለመቅረፉ አንዳንድ የአብነት ትምህርት ቤቶች እስከ አሁን ድረስ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በርካታ የአብነት ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ አገልግሎት አቁመዋል፤ ተማሪዎቻቸውም የተሻለ ሥራ ፍለጋ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተሰደዋል፡፡ ግማሾቹ ሎተሪ አዟሪ ሆነዋል፤ ሌሎችም ደግሞ በቀን ሥራ የሚተዳደሩ ሆነዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ እርሻ ሥራ ተመልሰዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ተተኪ ወይም ተረካቢ የቤተ ክርስቲያን አገልጋን ማግኘት አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ እነዚህንና መሰስል ችግሮችን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ባይቻልም የአብነት ትምህርት ቤቶች መደበኛ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉና የአብነት ተማሪዎችም በትምህርታቸው እንዲገፉ ክፍሉ የአልባሳት፣ የምግብ፣ የመጻሕፍት እንዲሁም የማደሪያ ድጋፎችን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በክፍሉ ውስን አቅም የተነሣ አገልግሎቱን በሚፈለገው መልኩ ለማስቀጠል ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶቹ ቁጥር ብዙ ነው፤ ፍላጎቱም በዚያው ልክ ሰፊ ነው። ገዳማት ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ ቋሚ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ዕለታዊና ወርሓዊ ገቢ እንዲያስገኙ የማድረግ ሥራዎች ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡
አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ገዳማት በተለያዩ ልማቶች ገቢን በማመንጨት ራሳቸውን እንዲችሉ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በተለይ ከልማት ጋር ተያይዞ ንብ ማነብን ጨምሮ የእርሻና የከብት ርባታ ሥራዎችን በመሥራት ገዳማውያኑ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጭምር እየተሠራ ነው፡፡ ክፍሉ ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለገዳማት ከሚያደርገው ልዩ ልዩ ቋሚና ጊዜያዊ ድጋፎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ጭምር ይሰጣል፡፡ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎቹ የአብነት ተማሪዎቹም ሆኑ ገዳማውያኑ ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑና ከኅብረተሰቡ ጋር ተግባብተው እንዲያገለግሉና እንዲገለገሉ ያግዛቸዋል፡፡ በተለይ ገዳማት የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል፡፡
በቋንቋቸው ተምረው የሚያስተምሩ የአብነት ተማሪዎችን ከማፍራት አኳያ እንዲሁ ክፍሉ ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸው አካባቢዎች ያሉ አድባራት የዕለት ተዕለት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ከሌላ አካባቢ አገልጋይ እያመጡ እንደሚጠቀሙ ይታወቃል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአገልጋይ እጥረት በመኖሩም መናፍቃን ምእመናንን በቀላሉ እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ይህንን ችግር በመረዳት የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸውን አንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም፣ ያሉትን ደግሞ የማጠናከር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም መሠረት በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በባሌ፣ በነጌሌ፣ በወላይታ፣በከንባታ፣ በሀላባና ጠንባሮ፣ በዳውሮ፣ በጋሞጎፋ፣ በኢሉባቦር በጅንካ፣ በአፋር፣ በሶማሌ አህጉረ ስብከት በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ሰፊ ሥራ የተሠራባቸውና እየተሠራባቸው ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡ በቀጣይም በተለያዩ አህጉረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋትና የማጠናከር ሥራዎችን እንሠራለን፡፡ የዚህ ተግባር ዓላማ አብያተ ክርስቲያናት በራሳቸው ቋንቋ የሚያስተምሩ፣ የሚቀድሱና የሚዘምሩ አገልጋዮችን ማፍራት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስቀጠል፣ ምእመናንን ለማጽናት፣ ያላመኑትን ለማሳመን በየአካባቢው አገልጋዮችን ማፍራት ለነገ የማይባል ነው፡፡ ይህ ተግባር የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ፣ አገልግሎቱም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ክፍሉ በዋናነት እያከናወናቸው ካሉ ተግባራት ባሻገር የአብነት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ዘመናዊ (የአስኳላ) ትምህርት እንዲማሩ እያደረገ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምህርት ዕድል ተመቻችቷል፡፡ በተመቻቸላቸው ነፃ የትምህርት ዕድልም ብዙዎቹ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ በሁለት ጎን የተሣሉ አገልጋዮች ለመሆንም በቅተዋል፡፡ ዘመናዊ ትምህርት ተምረው በአብነት ትምህርት ቤቶች ያላለፉ ወጣቶችም ጭምር የአብነት ትምህርት እንዲማሩ፣ የተማሩት ደግሞ ዘመናዊ ትምህርትን እንዲማሩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የክፍሉ ሥራዎች በጣም ሰፊ ቢሆኑም የተጠቀሱት ግን ጥቂቶቹ ናቸው። በአጠቃላይ ክፍሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ፕሮጀክቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- አዳዲስ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከማቋቋም ውጭ ለቀደምት የአብነት ትምህርት ቤቶች ልዩ ትኩረት አልተሰጣቸውም ይባላልና በዚህ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው?
ዲ/ን አንድነት፡- ማኅበረ ቅዱሳን የአቅም ውስንነት ስላለበት ሁሉም ቦታ ላይ መድረስ አይችልም። ይህም በመሆኑ በየአካባቢው ያለው አገልጋይም ሆነ የኅብረተሰብ ክፍል የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመጠበቅና ከማልማት አኳያ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተ ክርስቲያን የአሠራር ክፍተት ለአንዳንድ የአብነት ትምህርት ቤቶች ችግር በምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል። ይህም ሆኖ ግን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች አልተዘነጉም፡፡
ማኅበሩ በተለይ በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ በሁለት ወሳኝ መንገዶች እየሠራ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው የአብነት ትምህርት ቤቶች ባልተስፋፉበት አካባቢ ማስፋፋት ሲሆን የአብነት ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ደግሞ የማጠናከርና ደረጃቸውን ማሻሻል ሁለተኛው የማኅበሩ ሥራ ነው፡፡
በዚህ ሂደትም በርካታ ክርስቲያኖችና የአብነት ትምህርት ቤቶች ያሉበትን የሰሜኑን የሀገራችን ክፍል በተለየ ሁኔታ መጀመሪያ የቅኔ የምስክር ት/ቤቶችን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራባቸው ይገኛል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶችና በገዳማት ዙሪያ ሠርቶ ያስረከባቸው ፕሮጀክቶች አንድ መቶ አርባ ስድስት ደርሰዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹም የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን በእጅጉ ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ ርክክብ ያልተደረገባቸው በሥራ ላይ ያሉ ከዐሥር በላይ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡ ማኅበሩ እየሠራ ያለው ሁሉንም አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ነው፡፡ ለአንዱ አካባቢ የተለየ ትኩረት ለሌላው ደግሞ ዝቅተኛ ትኩረት አይኖረውም፡፡ ሥራዎች የሚሠሩት እንደአስፈላጊነቱና እንደ ክፍተቱ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የቅኔ ምስክር ትምህርት ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ እየሰጠን እየሠራን ነው፡፡ ምእመናንና ባለድርሻ አካላት የሚተባበሩ ከሆነ ደግሞ ሁሉም ዘንድ ለመድረስ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ በየአካባቢው ያለው ምእመን በአካባቢው ያለውን የአብነት ትምህርት ቤቶች ችግር ለመፍታት ቢነሣ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ በጥናትና መሰል ሙያዊ ድጋፎች እገዛ ያደርጋል፡፡