ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ስምዓ ጽድቅ

“ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችንና የሀገራችን የዕውቀት ምንጮች ናቸው ክፍል አንድ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 07 August 2021
Hits: 747
“ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችንና የሀገራችን የዕውቀት ምንጮች ናቸው          ክፍል አንድ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያልተበረዘና ያልተከለሰ እንዲሁም ወጥ የሆነ የአምልኮና የአስተዳደር ሥርዓት ያላት ናት፡፡ ይህም በዓለማችን ካሉት አጠቃላይ አብያተ ክርስቲያናት የተለየች ያደርጋታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷንና ትውፊቷን ለማስቀጠል የተለያዩ ተቋማትን መሥርታ እንቅስቃሴ ከጀመረች ዘመናትን አስቆጥራለች፡፡ ካሏት የአስተዳደር ክፍሎች በተጨማሪ በፈቃደኝነት በቤተ ክርስቲያን ሕግና ደንብ የተመሠረቱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ለምእመናን ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት  በተለያየ መልኩ ሲደግፉ ይታያሉ፡፡በርካታ ማኅበራት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር ተመሥርተው የቤተ ክርስተያንን አገልግሎት ለመደገፍ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ ቀላል የማይባሉ ጊዜያትን አሳልፈዋል፡፡ በሀገራችን ከመንፈሳዊ ማኅበራት እንቅስቃሴ አንፃር ስንመለከት ከዛሬ ሠላሳ ዓመታት ወዲህ በይፋ የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ለአብነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ማኅበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በሁለንተናዊ ዘርፍ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሲደግፍ ቆይቷል፡፡ 

በተለይ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች መካከል ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል፡፡ ማኅበሩ በአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ላይ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲኖራቸው በማድረግ  አብነት ትምህርት ቤቶች ያሏቸውን ደግሞ እንዲሁም በሰው ኃይልና በቁሳቁስ የማጠናከር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ 

ገዳማዊ ሥርዓቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ እና ገዳማት ራሳቸውን በገቢ እንዲችሉ ለማስቻል  ጊዜያዊና ዘላቂ ድጋፎችን አድርጓል፡ እያደረገም ይገኛል፡፡ ገዳማውያን በዕለት ጉርስ በዓመት ልብስ እጦት  እንዳይበተኑ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሀብት ሰብስቦ እገዛ ያደርጋል፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ረገድም ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ሰባክያነ ወንጌል እንዳታጣ በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ዝግጅት ክፍላችንም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ ከሆኑን ዲ/ን አንድነት ተፈራ ጋር በክፍሉ አጠቃላይ  አገልግሎ ዙሪያ አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ ከኃላፊው ጋር ያደረግነውን ቆይታም በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- የክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት ምን ምን ናቸው?

ዲ/ን አንድነት ተፈራ፡- የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ በዋናነት በትኩረት እየሠራ የሚገኘው አብነት ትምህርት ቤቶችና በገዳማት ላይ ነው፡፡ ክፍሉ ለገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ከጊዜያዊ ድጋፍ ጀምሮ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ቋሚ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች በሰው ሠራሽ፣ በተፈጥሮና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ተጎጂ ሲሆኑ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ጊዜያዊና ቋሚ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ለገዳማቱ የቀለብ፣ የአልባሳት፣ የንዋ ቅድሳት እንዲሁም የተለያዩ የመባ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡ እንደሚታወቀው የአብነት ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ‹‹በእንተ ስማ ለማርያም›› ብለው በሚያኙት ቁራሽ ይማሩ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ለምኖ የመማር ባህሉ እየተቀየረ በመምጣቱ የአብነት ተማሪዎች ለከፋ የቀለብ እጥረት ይጋለጣሉ፡፡ ስለሆነም ክፍሉ ለአብነት ተማሪዎች የቻለውን ያህል የቀለብ አቅርቦት ያደርጋል፡፡ ድጋፍ በመደረጉም በተወሰነ ደረጃ የሚዘጉ የአብነት ትምህርት ቤቶችን መታደግ ተችሏል፡፡ ጉባኤያትን ከመታጠፍ፣ ተማሪዎችን ከመበተንና ከመፍለስ የመታደግ ሥራ ተሠርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ባለመቅረፉ አንዳንድ የአብነት ትምህርት ቤቶች እስከ አሁን ድረስ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ 

በርካታ የአብነት ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ አገልግሎት አቁመዋል፤ ተማሪዎቻቸውም የተሻለ ሥራ ፍለጋ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተሰደዋል፡፡ ግማሾቹ ሎተሪ አዟሪ ሆነዋል፤ ሌሎችም ደግሞ  በቀን ሥራ የሚተዳደሩ ሆነዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ እርሻ ሥራ ተመልሰዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ተተኪ ወይም ተረካቢ የቤተ ክርስቲያን አገልጋን ማግኘት አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ እነዚህንና መሰስል ችግሮችን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ባይቻልም የአብነት ትምህርት ቤቶች መደበኛ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉና የአብነት ተማሪዎችም በትምህርታቸው እንዲገፉ ክፍሉ የአልባሳት፣ የምግብ፣ የመጻሕፍት እንዲሁም የማደሪያ  ድጋፎችን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በክፍሉ ውስን አቅም የተነሣ አገልግሎቱን በሚፈለገው መልኩ ለማስቀጠል ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል፡፡  የአብነት ትምህርት ቤቶቹ ቁጥር ብዙ ነው፤ ፍላጎቱም በዚያው ልክ ሰፊ ነው። ገዳማት ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ ቋሚ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ዕለታዊና ወርሓዊ ገቢ እንዲያስገኙ የማድረግ ሥራዎች ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ 

አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ገዳማት በተለያዩ ልማቶች ገቢን በማመንጨት ራሳቸውን እንዲችሉ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በተለይ ከልማት ጋር ተያይዞ  ንብ ማነብን ጨምሮ የእርሻና የከብት ርባታ ሥራዎችን በመሥራት ገዳማውያኑ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጭምር እየተሠራ ነው፡፡ ክፍሉ ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለገዳማት ከሚያደርገው ልዩ ልዩ ቋሚና ጊዜያዊ ድጋፎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ጭምር ይሰጣል፡፡ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎቹ የአብነት ተማሪዎቹም ሆኑ ገዳማውያኑ ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑና ከኅብረተሰቡ ጋር ተግባብተው እንዲያገለግሉና እንዲገለገሉ ያግዛቸዋል፡፡ በተለይ ገዳማት የእርስ በእርስ የልምድ  ልውውጥ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል፡፡ 

በቋንቋቸው ተምረው የሚያስተምሩ የአብነት ተማሪዎችን ከማፍራት አኳያ እንዲሁ ክፍሉ ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸው አካባቢዎች ያሉ አድባራት የዕለት ተዕለት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ከሌላ አካባቢ አገልጋይ እያመጡ እንደሚጠቀሙ ይታወቃል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአገልጋይ እጥረት በመኖሩም መናፍቃን ምእመናንን በቀላሉ እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ይህንን ችግር በመረዳት የአብነት ትምህርት ቤቶች የሌሉባቸውን አንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም፣ ያሉትን ደግሞ የማጠናከር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም መሠረት በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በባሌ፣ በነጌሌ፣ በወላይታ፣በከንባታ፣ በሀላባና ጠንባሮ፣ በዳውሮ፣ በጋሞጎፋ፣ በኢሉባቦር በጅንካ፣ በአፋር፣ በሶማሌ አህጉረ ስብከት በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ሰፊ ሥራ የተሠራባቸውና እየተሠራባቸው ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡ በቀጣይም በተለያዩ አህጉረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋትና የማጠናከር ሥራዎችን እንሠራለን፡፡ የዚህ ተግባር ዓላማ አብያተ ክርስቲያናት በራሳቸው ቋንቋ የሚያስተምሩ፣ የሚቀድሱና የሚዘምሩ አገልጋዮችን ማፍራት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስቀጠል፣ ምእመናንን ለማጽናት፣ ያላመኑትን ለማሳመን በየአካባቢው አገልጋዮችን ማፍራት ለነገ የማይባል ነው፡፡ ይህ ተግባር የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ፣ አገልግሎቱም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፡፡ 

ክፍሉ በዋናነት እያከናወናቸው ካሉ ተግባራት ባሻገር የአብነት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ዘመናዊ (የአስኳላ) ትምህርት እንዲማሩ እያደረገ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነፃ የትምህርት ዕድል ተመቻችቷል፡፡ በተመቻቸላቸው ነፃ የትምህርት ዕድልም ብዙዎቹ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ በሁለት ጎን የተሣሉ አገልጋዮች ለመሆንም በቅተዋል፡፡ ዘመናዊ ትምህርት ተምረው በአብነት ትምህርት ቤቶች ያላለፉ ወጣቶችም ጭምር የአብነት ትምህርት እንዲማሩ፣ የተማሩት ደግሞ ዘመናዊ ትምህርትን እንዲማሩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የክፍሉ ሥራዎች በጣም ሰፊ ቢሆኑም የተጠቀሱት ግን ጥቂቶቹ ናቸው። በአጠቃላይ ክፍሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ፕሮጀክቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ፡- አዳዲስ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከማቋቋም ውጭ ለቀደምት የአብነት ትምህርት ቤቶች ልዩ ትኩረት አልተሰጣቸውም ይባላልና በዚህ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው? 

ዲ/ን አንድነት፡-  ማኅበረ ቅዱሳን የአቅም ውስንነት ስላለበት ሁሉም ቦታ ላይ መድረስ አይችልም። ይህም በመሆኑ በየአካባቢው ያለው አገልጋይም ሆነ የኅብረተሰብ ክፍል የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመጠበቅና ከማልማት አኳያ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተ ክርስቲያን የአሠራር ክፍተት ለአንዳንድ የአብነት ትምህርት ቤቶች ችግር በምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል። ይህም ሆኖ ግን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች አልተዘነጉም፡፡ 

ማኅበሩ በተለይ በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ በሁለት ወሳኝ መንገዶች እየሠራ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው የአብነት ትምህርት ቤቶች ባልተስፋፉበት አካባቢ ማስፋፋት ሲሆን የአብነት ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ደግሞ የማጠናከርና ደረጃቸውን ማሻሻል ሁለተኛው የማኅበሩ ሥራ ነው፡፡

 በዚህ ሂደትም በርካታ ክርስቲያኖችና የአብነት ትምህርት ቤቶች ያሉበትን የሰሜኑን የሀገራችን ክፍል በተለየ ሁኔታ መጀመሪያ የቅኔ የምስክር ት/ቤቶችን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራባቸው ይገኛል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶችና በገዳማት ዙሪያ ሠርቶ ያስረከባቸው ፕሮጀክቶች አንድ መቶ አርባ ስድስት  ደርሰዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹም የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን በእጅጉ ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ ርክክብ ያልተደረገባቸው በሥራ ላይ ያሉ ከዐሥር በላይ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡ ማኅበሩ እየሠራ ያለው ሁሉንም አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ነው፡፡ ለአንዱ አካባቢ የተለየ ትኩረት ለሌላው ደግሞ ዝቅተኛ ትኩረት አይኖረውም፡፡ ሥራዎች የሚሠሩት እንደአስፈላጊነቱና እንደ ክፍተቱ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የቅኔ ምስክር ትምህርት ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ እየሰጠን እየሠራን ነው፡፡ ምእመናንና ባለድርሻ አካላት የሚተባበሩ ከሆነ ደግሞ ሁሉም ዘንድ ለመድረስ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ በየአካባቢው ያለው ምእመን በአካባቢው ያለውን የአብነት ትምህርት ቤቶች ችግር ለመፍታት ቢነሣ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ በጥናትና መሰል ሙያዊ ድጋፎች እገዛ ያደርጋል፡፡ 

Hits: 554

Hits: 730

በካናዳ የሚገኘው የግብጽ ኮፕቲክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት ቃጠሎ ደረሰበት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 07 August 2021
Hits: 456
በካናዳ የሚገኘው የግብጽ ኮፕቲክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን  ባልታወቀ ምክንያት ቃጠሎ ደረሰበት

በካናዳ ሹሪ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት የሚገኘው የግብጽ ኮፕቲክ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንፃ ቤተ ክርቲያን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጂ አስነበበ፡፡

ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት በቅርብ በእሳት መቃጠሉን ዘገባው ያስረዳ ሲሆን ካለፈው ረዕቡ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኑ የጥቃት ዒላማ ሆኖ መቆየቱንም የአካባቢው የፖሊስ አካላት እንደተናገሩ ተገልጧል፡፡ 

የሚና ሚሲሳውጋ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖሊስ ጉዳዩን በፍጥነት መርምሮ እንዲያሳውቅ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታውቆ ድርጊቱ በራሱ ጥያቄ የሚያስነሣ ከመሆኑ ባሻገር የሚመለካታቸው የመንግሥት አካላት እሳቱን ቶሎ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡

የተቃጠለው የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የግብጽ፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሊባኖስ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በጋራ ይገለገሉበት እንደነበረ ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ ኦሬንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡

Hits: 523

ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ለባህል ዋጋ የሚሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ ሊደግፉ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1040
  • አጫጭር ዜናዎች

ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ለባህል ዋጋ የሚሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ መደገፍ እንደሚገባቸው ጥሪ መቅረቡን ኦርቴዶክስ ኮግኔት ፔጅ በገጹ አስነበበ፡፡ 

በቅርቡ በኤይ  ኤን ኤስ ሲ ኦፒ አማካይነት በተጠናው ጥናት መሠረት ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ሮማንያውያን ለሃይማኖትና ባህል ልዩ ትኩረት የሚሠጠውን ሀገር አቀፍ ወግ አጥባቂ ፓርቲን መደገፍ እንዳሰቡ ዘገባው አስረድቷል፡፡ 

የሮማንያውያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ በጣም ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ስትሆን ቤተክርቲያኗ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዳንኤል ትመራለች፤ቅዱስነታቸውም የምእመናንን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጥቅሞችን ከማስጠበቅ አኳያ የላቀ አገልግሎት እየፈጸሙ መሆናቸውን ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል፡፡   

ለገዳማቱ መንፈሳዊ ጉብኝት ባለቤቱ ማነው?

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 932
  • መልዕክት

ብዙም ዘመናዊ መጓጓዣ ባልነበረበት እንደዛሬው ማስታወቂያ በማይነገርበት በጥንቱ ዘመን አባቶቻችን ባሕር አቋርጠው፣ ተራራ ወጥተው እና ወርደው የብዙ ቀናት አሊያም ወራት መንገድ በእግራቸው ተጉዘው ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም ፣ ከበዓሉ በረከት ለመሳተፍ ወደ ተለያዩ መንፈሳዊ ቦታዎች መንፈሳዊ ጒዞዎችን ሲያደርጉ ኖረዋል።በዚህ መንፈሳዊ ጉዞም የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያድግ አድርገዋል፤ ወንጌል እንዲስፋፋ የራሳቸውን አስተዋጽኦም አበርክተዋል።ለዚህም በሐዋ. ሥራ ምዕራፍ ፰ ላይ የምናገኘው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አንዱ ምሳሌ ነው።

ዛሬ ከዚያ በተለየ መልኩ መንፈሳዊ ጉብኝቶች ዘመኑን በዋጀ መልኩ በማስታወቂያ ታጅበው ለምእመናት ይደርሳሉ።ምእመናን መጓጓዣ ከማይገባባቸው  ቦታዎች በስተቀርም ዘመኑ ባመጣው መጓጓዣ ይገለገላሉ።የመንፈሳዊ ጉዞ ማስታወቂያዎች እንደ አሸን በፈሉበት በዚህ ዘመን ከየትኛው ቤተ ክርስቲያን (ገዳም) ልሂድ የሚለው ብዙም አሳሳቢ አይደለም።የማስታወቂያዎቹ ዓይነቶችም እንደ ባሕሪያቸው የተለያዩ ናቸው።

ከእነዚህ ብዛት ያላቸው ማስታወቂያዎች በተለይ ‹‹ዘወትር እሑድ ወደ . . . ገዳም››  የሚል ማስታወቂያ በየቦታው ማየት እየተለመደ መጥቷል። የቤተ ክርስቲያንን ውጫዊ ቅጽሮች፣  የአውቶብስ ፌርማታዎች ፣ የመንገድ ዳር አጥሮች እንዲሁም የከተማ ታክሲዎች ባጠቃላይ የትራንስፖርት መጓጓዣዎች  በጉዞ ማስታወቂያዎች የተሞሉ ናቸው።ከዚህ አለፍ ሲልም ጉዞው የሚደረግበትን ቦታ የሚያስተዋውቁ በራሪ ወረቀቶች በየመንገዱ ማየት የተለመደ ነው።

Read more: ለገዳማቱ መንፈሳዊ ጉብኝት ባለቤቱ ማነው?

የአክራሪ እስላም እኩይ ድርጊትና የክርስቲያኖች የሕልውና ፈተና ክፍል ሁለት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1068
  • ሪፖርታዥ

የተወደደዳችሁ አንባብያ የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ በፊት በነበረው እትም ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ቀጣዩንና ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ እነሆ፦

የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስቀመጠው ትርጒም መሠረት አክራሪ እስላም የሚለው ሐረግ ከሁለት ቃላቶች የተገኙ ሲሆን ትርጒሙም “የኃይል ርምጃንና ጥቃትን እንደ ስልት በመጠቀም የራሱን ሃይማኖትና ፍልስፍና ሌሎች እንዲቀበሉ የሚያስገድድ ኃይል ነው” ይላል።የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ በዓለም ላይ መቼ እንደተጀመረ በውል የሚታወቅ ባይሆንም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑን ግን መገመት አያስቸግርም።የአክራሪ እስልምና እኩይ እንቅስቃሴ መላውን ዓለም ያዳረሰ ቢሆንም የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራትን ያህል ግን እንቅስቃሴው የተስፋፋበት የዓለማችን አካባቢ የለም።አንዳንድ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በተለይ ሶርያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ሳውዲ ዓረቢያ፣ ኢራንና ሌሎች ሀገራት የአክራሪ እስልምና እኩይ ተግባር መዳረሻ ከሆኑ ቆይተዋል። በተለይ በሶሪያና ኢራቅ የሚንቀሳቀሰው ራሱን “አይ ኤስ” ብሎ የሚጠራው እስላማዊ የሽብር ቡድን በአካባቢው በርካታ ውድመት አድርሷል። በነዚህ ሀገራት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ለሞት፣ለስደትና ለከፋ እንግልት መዳረጋቸውን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መግለጧን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነም የሽብር ቡድኑ በክርስቲያኖች ላይ በሰነዘረው ተደጋጋሚ ጥቃት በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል፣ሀብት ንብረቶቻቸው እንዳልነበረ ሆነዋል፤ ይህ በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያኑ ለከፋ የሥነ ልቡና ጫና ተዳርጓል።በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ሲገድሉ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ያለና የሽብር ቡድኑ እንቅስቃሴ የተዳከመ ቢሆንም ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ክርስቲያኖች ግን ከተሰደዱበት ሀገር ወደ አካባቢያቸው አልተመለሱም፤ የወደመባቸው ሀብትና ንብረትም አልተተካላቸውም።

Read more: የአክራሪ እስላም እኩይ ድርጊትና የክርስቲያኖች የሕልውና ፈተና ክፍል ሁለት

‹‹የቄስ መቃብሩ የሚሳምበት ጊዜ ይመጣል የሚባለው ሰው አልቆ አይደለም›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ክፍል ሁለት

Details
Written by: መጽሐፈ ሲራክ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1533
  • ቤተ አብርሃም
‹‹የቄስ መቃብሩ የሚሳምበት ጊዜ ይመጣል የሚባለው  ሰው አልቆ አይደለም›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ክፍል ሁለት

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ በፊት በነበረው እትም ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ቀጣዩን ክፍል ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡                                                                            

በዚያ ዓመት ነሐሴ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ደብረ ሊባኖስ አልሄዱም ነበር መርካቶ ደብረ አሚን መጥተው ገድለ ተክለ ሃይማኖትን ጥሩ አድርጌ ሳነብ ስተረጉም ፣ ሳስተምር ደስ ብሎአቸው አተኩረው እያዩኝ ይሰሙኝ ነበርና ታቦቱ እንደገባ አስጠርተው ‹‹ደብዳቤ ሳይደርስ ከዚህ እንዳትሄድ›› አሉኝ ፤እኔም የመተሐራውን ሐሳባቸውን እንደቀየሩ ገባኝ።‹‹ድሮስ ያለ ደብዳቤ እንዴት እሄዳለሁ?›› አልኩኝ።በዚያው ወደ መተሐራ መመለሴ ቀረ ማለት ነው። 

ደብረ አሚን አለቃ ሁኜ እያገለገልኩ ሳለ  ጻድቁ የተሰጣቸው ቃል ኪዳን ነው ለምን ፀበል አላጠምቅም ብዬ ገድላቸውን እያነበብኩ ምእመናንን ማጥመቅ ጀመርኩ እንዲሁ እግዚአብሔር ነው ያነሳሳኝ።ካህናቱም በተራ እንዲገቡ አደረግሁ በኔ የመጣ ጸጋ አይደለም የጻድቁ ነው አልኳቸው እነሱም ደስ ብሎአቸው ያጠምቁ ነበር።ደብረ አሚን ፱ ዓመት በልቅና ካገለገልኩ በኋላ በ፲፱፻፸፱ ዓ.ም ጵጵስና ውድድር ውስጥ ገብተሀል የሕይወት ታሪክህን አምጣ አሉኝ የሕይወት ታሪኬን ጽፌ አስገባሁ ውድድሩን አልፌ መዓረገ ጵጵስናው ተሰጠኝ ወዲያው ወደ ወላይታ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ ሆኜ በመሄድ አንድ ዓመት አገለገልኩ።የሚገርመው ብዙ ጊዜ ለአገልግሎት የምመደብባቸው ቦታዎች የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነበር።እነሱም የተክለ ሃማኖት ልጅ ነው እያሉ ነበር ወደ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ይልኩኝ የነበረው።

Read more: ‹‹የቄስ መቃብሩ የሚሳምበት ጊዜ ይመጣል የሚባለው ሰው አልቆ አይደለም›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ክፍል ሁለት

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያሉ ጥንታዊ ገዳሞቻችን አስቸኳይ ጥበቃና ክብካቤ ይፈልጋሉ! ክፍል ሁለት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1037
  • ፍሬ ከናፍር
በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያሉ ጥንታዊ ገዳሞቻችን  አስቸኳይ ጥበቃና ክብካቤ ይፈልጋሉ! ክፍል ሁለት

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል። በጥሞና ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው። 

ግብጻውያኑ ጳጳሳትም ሆኑ መነኮሳት በእኛ ገዳማትና መነኮሳት ላይ የሚፈጸሙትን አረመኔያዊ ተግባር ለተመለከተ ክርስቲያን መሆናቸውን ይጠራጠራል። በጣም ጨካኞች፤ የራሳቸውን እንጂ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜትና ፍላጎት የማያከብሩ ዕብሪተኞች ናቸው። በገዳማችን ውስጥ በብዛትና በኃይል እየገቡ “አንወጣም” በማለት ለመውረር ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት በአካባቢው  የፀጥታ ኃይልና በልጆቻችን በሳልነት ወረራውን ማካሄድ ሳይችሉ ቀርተዋል።ምንም እንኳን ኃይልና ብዛት ቢኖራቸውም ከሰው ኃይል የእግዚአብሔር ኃይል ይበልጣልና ምስኪኖቹና በቁጥር አናሳ የሆነው በመጨረሻ አሸንፈን ጠላቶቻችን አፍረው ተመልሰዋል። በዚህም ምክንያትም ገዳማዊ ርስቶቻችንን ማስከበር ችለናል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገዳሞቻችን እየተፈጸመ ያለው ችግር ዘመን የማይፈታው እየሆነ መጥቷል።በዓላት በቀረቡ ቁጥር ዕብሪተኛ ግብጻውያን “የሃይማኖት አባቶችና ተከታዮቻቸው” ትንኮሳ ይፈጽሙብናል። እግዚአብሔር ራሱ መፍትሔ እስካላመጣ ድረስ በግብጻውያኑ እየተፈጸመብን ያለው ጥቃት የሚቆም ወይም የሚቀንስ አይመስለኝም። ለጆሮ የሚከብዱ ለዓይን የሚያስጨንቁ በደሎች ተፈጽመውብናል። የፈረሱ ገዳማትን የመጠገን፣ የማደስና የመንከባከብ  መብታችን ተነጥቆ ስንገፋ ቆይተናል።

Read more: በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያሉ ጥንታዊ ገዳሞቻችን አስቸኳይ ጥበቃና ክብካቤ ይፈልጋሉ! ክፍል ሁለት

የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ማርቶማ ፓውሎስ ፪ኛ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1428
  • አጫጭር ዜናዎች
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ማርቶማ ፓውሎስ   ፪ኛ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቶማ ፓውሎስ ፪ኛ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በተወለዱ በ፸፭ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ኦርቶዶከስ ኮግኔት ፔጅ አስነበበ፡፡ 

ቅዱስነታቸው ከጥር ፳፻፲፫ ዓ.ም ጀምሮ በቅዱስ ጎርጎርዮዎስ ፓአሩማላ ሆስፒታል የካንሰር ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ባሉበት ሁኔታ ጤናቸው አሳሳቢ ደርጃ ላይ ሲደርስ በመተንፈሻ መሣሪያ ሲታገዙ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ዘገባው አመልክቶ ሥርዓተ ቀብራቸውም ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በመንበረ ፕትርክናቸው ተፈጽሟል፡፡ 

ቅዱስነታቸው ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን ከሕዳር ፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም ጀምሮ ከቅዱስ ማርቶማ ዲዳይሞስ አንደኛ ቀጥሎ በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ፓአሩማላ ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል።

በተያያዘ ዜና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን  ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቶማ ፓውሎስ ፪ኛ ከዚህ ዓለም ድካም ዕረፍት በመለየታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን በደብዳቤ ገልጠዋል፡፡ 

Read more: የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ማርቶማ ፓውሎስ ፪ኛ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

የዓለም ብርሃናት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ

Details
Written by: እህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 06 August 2021
Hits: 1780
  • የሕፃናት ዓምድ

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች! እንደምን ከረማችሁ? ደኅና ናችሁ? የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!!   

ልጆች! ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ሐምሌ ፭ ቀን በየዓመቱ መታሰቢያቸው ስለሚደረገው እና ስለሚከበረው ስለ ሁለቱ የቤተ ክርስቲያን ብርሃናት እና ሰማእታት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ ነው፤መልካም ንባብ ይሁንላችሁ!    

ልጆች! ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በዓለም ዞረው በማስተማር በሰማእትነት ያረፉት በዓላዊው ንጉሥ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ነው።የነዚህን ሁለት ሰማዕታት ታሪክ እንደሚከተው በየተራ እናቀርብላችኋለን።ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ

ልጆች! ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ሲሆን አባቱ ከነገደ ሮቤል እናቱ ደግሞ ከነገደ ሰምዖን የተገኙ ናቸው።ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓሣ ሲያጠምድ በጥብርያዶስ ባህር ዳር አግኝቶት ለሐዋርያነት እንዲሆን ጠርቶታል።ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የቀድሞ ስሙ ‹‹ስምዖን›› ሲሆን ጌታችን ለሐዋርያነት አገልግሎት ሲመርጠው ‹‹ጴጥሮስ›› ብሎ ጠርቶታል።

Read more: የዓለም ብርሃናት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ

Page 3 of 19

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት