- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1483
ውድ የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጆች! እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ድኅና ነኝ። ስሜ ገብረ ትንሣኤ ይባላል የ፵፭ ዓመት ጎልማሳ ነኝ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ፈተና የሆነብኝን ነገር ላካፍችሁ ወደ እናንተ ጻፍኩ። ነገሩ እንዲህ ነው እኔ እና ባለቤቴ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ቊርባን ከተጋባን ዐሥር ዓመት ሆነን ነገር ግን ቤታችን በልጅ አልተባረከም። የሞላ ሀብት ቢኖረንም እስከዛሬ ድረስ ልጅን መውለድ አልቻልንም። የመጀመሪያዎቹን ሦስት ዓመታት እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ጠበቅን ምንም ነገር የለም።
በመሀል እኔ እንድንመረመር ለባለቤቴ ጥያቄ አቀረብኩና ወደ ሆስፒታል ሄድን ስንመረመር እኔ መውለድ እችላለሁ እርሷ መውለድ አትችልም(መሀን ናት)። ይህ ውጤት ግን ለቤታችን ሰላምን ይዞ አልመጣም በመሀከላችን የነበረው ፍቅር እየቀዘቀዘ ከመሄዱም በላይ ዘወትር በረባ ባረባው መጨቃጨቅ ሥራችን ሆነ። ለዚህ ደግሞ ትልቁን ድርሻ የምትወስደው የትዳር አጋሬ ናት። በሆነ ባልሆነው ይከፋታል ሲያሻት ታኮርፈኛለች። በስሕተት ስለ ወለዱ ሰዎች ካወራሁ ወይም ከጓደኞቼ ጋር አምሽቼ ከገባሁ ‹‹እኔ መውለድ ስለማልችል ጠልተኸኝ ነው፤ የምትወልድ ማግባት ትችላለህ ›› እያለች ወደ ውጪ እንዳይ ትገፋኛለች። እኔ መፋታት ኃጢአት ነው ብዬ አስባለሁ ፤ነገር ግን በየዕለቱ በዚህ ምክንያት ቤቴ መግባት እስኪያስጠላኝ ደርሻለሁ።
- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1258
በረጅም ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር እድገት ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። በመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ያላት አስተዋጽኦ የሚነሣው ምእመናን እንደ ሀገር ዜጋ ከሚኖራቸው ታማኝነትና ባለ አደራነት ነው። ይህም የሚሆነው ከሀገር መሪዎችና ባለ ሥልጣናት ጀምሮ እስከ ተርታው ኗሪ ድረስ እንደ ባለ ሀገር በማሰብ ስለሚኖሩ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ያላትን የማኅበራዊ አገልግሎት ድርሻ መሠረት ያደረገ ነው።
ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፤ ትመክራለች፤ በግብረገብ ታንጻለች፤ ለበጎ አድራጎት እንዲነሣሡ ዜጎችን ታነቃቃለች፤ ለሥራ እንዳይለግሙ ታተጋለች፤ ለነጻነትና ፍትሕ እንዲቆሙ ታጠነክራለች፤ የጥበብ ምንጭ ትሆናለች፤ ምእመናን በመንግሥት የሥራ ዘርፎች ሁሉ ታማኝ ሆነው እንዲያገለግሉ ታሳስባለች፤ ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ አስተዋጽኦዎችን በማድረግ ኢትዮጵያ ሀገር ሆና የቆመችበትን ሁኔታ ፈጥራለች። ዛሬም ሆነ ወደፊት ልጆችዋን አሳልፋ ለሀገራዊ ህልውናዋ ትሠራለች።
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገርን ችግር ሁሉ ተሸክማ ኢትዮጵያን ብዙ ዘመን አሻግራለች። በሀገር የሚመጣን መከራ ሁሉ በግንባር ቀደምትነት የመከራ ተካፋይ ስትሆን ኖራለች። በዚህም ለልጆቿ መጠለያ ከለላ በመሆን ዘመናትን አሳልፋለች። ስለልጆቿም ራሷን አሳልፋ ሰጥታለች። ይህ መከራም ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም የሚሆንባት ነገም የሚከተላት ነው። ለዚህ ምስክሩ ደግሞ የዛሬው ትውልድ በገጠመው ፈተና ውስጥም የመከራውን ሁሉ ቀንበር ተሸካሚ ሆና መገኘቷ ነው።
አሁንም ኢትዮጵያ በጭንቅ ውስጥ ያለች ሀገር ሆናለች። ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ግጭት፣ በውጪ ኃይሎች ወረራ እና በሌሎችም ውስብስብ ችግሮች ተተብትባለች። ሰይጣን ኢትዮጵያን ባለ በሌለ ኃይሉ የከበባት ይመስላል። ዘረኝነት፣ ጭካኔ፣ ድንቁርና ዜጎችን እያጠቁ ነው።
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1035
መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሊካሄድ የአንድ ወር ያህል ጊዜ ብቻ ቀርቶታል። ምርጫ ቦርድም የጊዜ ሰሌዳ ነድፎ በቅደም ተከተል የሚካሄዱ ፕሮግራሞችን እያካሄደ ይገኛል። በአንደ ጎኑ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየው ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የእርስ በርስ ግጭትን በሌላ በኩል የምርጫ ፕሮግራምን ተሸክማ ወደፊት ለመራመድ እየሞከረች ያለችበት ሰዓት ላይ ነው ያለነው።
ከአጠቃላይ ሕዝቧ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመን በመሆነባት ሀገራችን እንደ አንድ ባለመብት ዜጋም ሆነ ከነገው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥቅም አንፃር ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚወክላትና በፓላማ ስለሚወሰነው ጉዳይዋ ድምጽ የሚሆናት ተመራጭ ሊኖራት ይገባል።
ይህንንም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በየካቲት ፳፻፲፫ ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ጸድቆ የወጣውን መመሪያና በመመሪያው ስለተካተተው የአባላት የፖለቲካ ተሳትፎ፣ መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ውብሸት ኦቶሮ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሊቪቭን ጋር ባደረጉት ቆይታ በምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለአባላት፣ እንዲሁም በቅርብ ማኅበሩን ለሚከታተሉ የተለያዩ አካላት በቅርቡ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ማብራሪያው ሙሉ ሐሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል።
- Details
- Written by: መጽሐፈ ሲራክ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1576
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዕማድ ሆነው ሲያገለግሏት የኖሩ እና የሚኖሩ የብዙ ሊቃውንት መምህራን ባለቤት ናት። እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በልጅነት ሕይወታቸው ከቤተሰቦቻቸው እና ከቀዬአቸው ርቀው በመሄድ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ብዙ ዋጋ ከፍለው ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። በአብነት ትምህርት ቤት ሕይወታቸው ከራሳቸው አልፈው ወንበር በመዘርጋት ብዙዎችን የቤተ ክርስቲያን ልጆች በማፍራት አገልግሎቱ እንዲቀጥል ወርቃማ አሻራቸውን ያሳረፉ ብዙዎች ናቸው። በነበራቸው የአገልግሎት ዘመናት ሁሉ ደሞዝ ሳይቆረጥላቸው፣ ቀለብ ሳይሰፈርላቸው ቤተ ክርስቲያንን በትሩፋት ሲያገለግሉ ኖረዋል።
በተሰጣቸው የዕድሜ ዘመን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ሥርዓት እና ትውፊት አስጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር ሊቃውንቶቻችን ዘመን የማይሽረው ሥራ ሲሰሩ ኖረዋል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት፣ በሥነ ምግባር፣ በትውፊቱ ጠንካራ ሆና እንድትቀጥል፤ ዘመን አመጣሹን ማዕበል ሁሉ ተቋቁማ እንድታልፍ ገና ከጥዋቱ ጠንካራ የሃይማኖት መሠረት ጥለዋል። ቤተ ክርስቲያን በመምህራን ለምልማ እንድትታይ የተጉ፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚረከብ ጠንካራ ትውልድ ሲቀርጹ የኖሩ ሊቃውንቶቻችን የአብነት ትምህርት ቤቱ ምሰሶ ሆነው አልፈዋል።
ከእነዚህ የቤተ ክርስቲያን ብርቅዬ ሊቃውንት መካከል አንዱ የሆኑትን አለቃ ኅሩይ ተ/ሃይማኖትን የሕይወት ታሪክ ለ‹‹ቤተ አብርሃም›› በሚሆን መንገድ አዘጋጅተነዋል ተከታተሉን።
- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1120
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የስድስት ወር የሥራ አመራር ጉባኤውን ከሚያዚያ ፩ እስከ ሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም አካሄደ።
ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር የተወከሉ የማዕከላት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኝተዋል። በጉባኤውም የሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ፣ የኤዲቶሪያል ቦርድ ማስተባበሪያ፣ የኦዲት አገልግሎት ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የስድስት ወር የሥራ አመራር ቃለ ጉባኤም ጸድቋል።
በቀጣይ ቀናትም የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ አገልግሎት ተግዳሮትና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ ስልታዊ ዕቅድ ማሻሻያ፣ የተቋማዊ ለውጥ መነሻ ሐሳቦች እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መነሻ ሐሳብ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተነሥተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ማኅበሩ ስልታዊ ዕቅድ ከጀመረ አራተኛ ዓመት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የማኅበሩ ዋና ጸሓፊ አቶ ውብሸት ኦቶሮ የስልታዊ ዕቅዱ አጠቃላይ ይዘት ስድስት ወሳኝ ጉዳዮችን፣ ፳፱ ግቦችን ፪፻፳፫ ስልቶችና አመላካቾች የተካተቱበት እደሆነ፤ የስልታዊ ዕቅዱ ዋና እሳቤም ከአጋር እና ከተባባሪ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ እንዲሁም የሰው ኃይል ልማት ላይ እንደሚያተኩርም ገልጸዋል።
በጉባኤው መዝጊያም የማኅበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ችግሩ እጅግ እየተወሳሰበ መምጣቱን ገልጸዋል። አክለውም የማኅበሩ አባላት ከወትሮ በተለየ መልኩ ሱባኤ ገብተው ጸሎት በማድረግ እንዲሁም በማስተማር እና በመምከር ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1077
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳስ ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ሃይማኖትን መሠረት የደረጉ ጥቃቶች ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ላደረጉት ጸሎት እና ድጋፍ ለሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል ሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም የምስጋና ደብዳቤ መላካቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል።
ቅዱስነታቸው የምስጋና ደብዳቤውን የላኩት የሞስኮና የመላው ሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ምእመናን መገደላቸውን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኀዘን መግለጫ እንዲሁም የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድጋፍ እንደሚያደርጉ የሚገልጽ ደብዳቤ መላካቸውን ተከትሎ ነው።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉት ጥቃቶች በዋነኝነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን በምስጋና ደብዳቤያቸው ላይ አክለው ገልጸዋል።
የሞስኮና የመላው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል በየካቲት ወር ፳፻፲፫ ዓ.ም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኀዘን መግለጫ ደብዳቤ መላካቸውን አስመልክቶ መዘገባችን ይታወሳል።
- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1005
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን በመጎብኘት የመቊረቢያ አልባሳትንና የጸሎት መጻሕፍትን ለገሱ።
የጉብኝት ጉዞው አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግሩም አሥራት ‹‹የታመሙትን መጠየቅ፣ የተቸገሩትንም መርዳት ግዴታችን ነውና ለአረጋውያኑና ለአእምሮ ሕሙማኑ ከቁሳዊ ድጋፍ ባሻገር መንፈሳዊ ድጋፍ ልናደርግላቸውው ይገባል›› ብለዋል። አስተባባሪው አክለውም ‹‹በቃል የምናስተምረውን በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል›› ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም የቀሩትን የማኅበረ ቅዱሳንን አባላት በማሳተፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በማዕከሉ የተገኙት የማኅበሩ መደበኛ አገልጋይ ቀሲስ ይግዛው መኮንን በበኩላቸው ‹‹መስማት ማየትን አይተካውም የምንሰማውና የምናየው የተለያየ ነው ፤ እኔ እስከዛሬ ስለ ማዕከሉ ሳልሰማ ቀርቼ አይደለም ፤ ነገር ግን በፊት ከነበረኝ አመለካከት ዛሬ ብዙ ነገር ተምሬአለሁ ፤ መማር ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገር ለማድረግ ወስኛለሁ፤ ስዚህ ሌሎቻችንም በአካል መጥተን ማዕከሉን አልናይ ይገባል።›› ብለዋል።
አረጋውያኑም የማኅበሩ አገልጋዮች ማዕከሉ ድረስ በመሄድ ስላደረጉላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን የማዕከሉ መሥራች ክቡር ዶክተር ብንያም በለጠም ‹‹አረጋውያኑን እና የአእምሮ ሕሙማኑን ስለጠየቃችኋቸው፣ ድጋፍም ስላደረጋችሁላቸው ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ›› ያሉ ሲሆን በመቀጠልም ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶች መጥተው እንዲረዱን እንዲሁም ፹፩ ፷፩ ላይ OK ብለው በእጅ ስልካቸው ላይ በመላክ እና አንድ ብር በመስጠት ጎዳና ላይ የወደቁ ወገኖቻችንን እናነሳ ዘንድ በእናንተ በኩል አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉል›› ሲሉ መልእክታቸውን አስተላለፈዋል።
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1510
የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው።
ስምዐ ጽድቅ፡- በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሚኙት ‹‹የቅባት እምነት›› አራማጆች በርስዎ ሀገረ ስብከት ላይ ያደረሱት ተፅእኖ ካለ ቢገልጹልን?
ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፡- ሀገረ ስብከታችን ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ቀሳጥያኙ በተለይም በደጋ ዳሞት በኩል እየገቡ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሊከፋፍሉና ባዕድ አስተምህሯቸውን ሊያስፋፉ ሲሞክሩ ጥብቅ ቁጥጥርና ክልከላ በማድረግ በአካባቢው እንዳይንቀሳቀሱ ስናደርግ ቆይተናል። የአካባቢው ምእመናንም ሆኑ ካህናቱ ችግሩን በደንብ የተረዱ፣ እምነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸውና ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና በመገመት በሀገረ ስብከታችን ከሙከራ የዘለለ የተጠናከረ እንቅስቃሴ አያድርጉም። በሀገረ ስብከታችን ውስጥ ሰርገው በሚገቡበት ወቅት በተቆጡ ምእመናንና አገልጋዮች አማካይነት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ እኔም ምእመናንና ካህናትን በመሰብሰብ ችግር ሳይፈጠር በዓይነ ቁራኛ ብቻ ተከታትለው በሰላም እንዲወጡ የማድረግ ሥራ ብቻ እንዲሠሩ እነግራቸዋለሁ። አልፎ አልፎ ወደ ሀገረ ስብከታችን በሚመጡበት ወቅት በምእመናን በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት አፍረውና ተሸማቅው ይመለሳሉ።
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1003
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በተፈጸመ ጥቃት ለተፈናቀሉ የአጣዬ ከተማና አካባቢው ምእመናን የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቃዐጥበብ አባቡ አስታወቁ፡፡
በቅርቡ በአጣዬ ከተማና አካባቢው የጥፋት ኃይሎች በፈጸሙት ዘርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ አስከፊ ጉዳት እንደደረሰ ሥራ አስኪያጁ ገልጠዋል፡፡ በተፈጸመው ጥቃት ሀብት ንብረት እንደወደመና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ሕይወት እንደጠፋ ያስረዱት ሥራ አስኪያጁ በጥቃቱም እስካሁን ድረስ ከሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ በላይ ምእመናን ተፈናቅለው በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያዎች እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
ከጥቃቱ የተረፉ ምእመናን በደብረ ብርሃን፤ በደብረ ሲናና በመሐል ሜዳ ከተሞች ጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ የገለጡት ሥራ አስኪያጅ ሀገረ ስብከቱም አቅም የፈቀደውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአጣዬ ከተማና አካባቢው አክራሪዎች ባደረሱት ጥቃት ምክንያት በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዘገበ ሲሆን ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚሠራው ሥራ ላይ ሀገረ ስብከታቸው በቀጣይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡
ሀገረ ስብከቱ በተለይ በመሐል ሜዳ ተፈናቅለው ለሚገኙ ምእመናን አስቸኳይ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ያስረዳው ዘገባው ድጋፍ የተደረገላቸው ምእመናንም ለተደረገላቸው ድጋፍ ማመስገናቸውን አስረድቷል፡፡
ሰሞኑን በሚከበረው የትንሣኤ በዓል ወቅት ምእመናን በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ምእመናን ጋር በጋራ በማክበር ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል፡፡
በአካባቢው ተመሳሳይ ችግር ድጋሚ እንዳይከሰት ሀገረ ስብከታቸው ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መሆኑንን ብፁዕነታቸው አንስተው በሌሎች አካባቢዎች በጊዜያዊ መጠለያ ላሉ ምእመናን ጭምር አስቸኳይ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውንም ዘገባው አስረድቷል፡፡
- Details
- Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1054
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገርን በሚመለከት ማንኛውም ጉዳይ ላይ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች። ተደጋግሞ እንደሚጠቀሰው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የማስታወቂያ ሚንስቴር፣ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሆና ሀገርን እና ሕዝብን ስታገለግል ኖራለች። ኦርቶዶክሳውያን ልጆቿም ከቤተ መንግሥት ጀምሮ እስከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ድረስ በሀገራችን በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት፣ በአማካሪነት እንዲሁም በዲፕሎማትነት ሲያገለግሉ ኖረዋል። እነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ላይ ለነበራት ከፍተኛ ሥፍራ እና ተሰሚነት ማሳያዎች ናቸው።
በሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ተቋማትም ሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የኋላ ታሪካቸው ሲታይ የቤተ ክርስቲያን አሻራ ያረፈባቸው ናቸው። በእምነት ተከታዮቿ ብዛት የሀገራችን ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሸፍን ምእመን ያላት ክርስቶሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ክብርና ተሰሚነት የነበራት፣ ታላቅ ቦታም የሚሰጣት ተቋም ነበረች። እንደዛሬው ሳይሆን በዚህ ወቅት በታላቁ የጾመ ሁዳዴ የመገናኛ ብዙኃኑ ሳይቀር ስለመንፈሳዊ ነገር የሚሰብኩ፣ በዘፈን ፈንታ የበገና መዝሙር የሚሰማባቸው ነበሩ።
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 976
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ መጠነ ሰፊ የሆነ የአካል፣የንብረት፣የሥነ ልቡናና የኢኮኖሚ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ጥቃቱን በአብዛኛው የሚፈጽሙት በሃይማኖት ስም የተደራጁ አክራሪ ቡድኖች ናቸው። በተለይም በአንዳንድ የኦሮምያ ክልል ከተሞች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የማያቋርጥ ውድመትና ጭፍጨፋ ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ አሁንም እያደረሱ ይገኛሉ። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ጽንፈኛ አክራሪ ኃይሎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጭምር ሳይቀር የስንቅና ትጥቅ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
ለአክራሪ ጽንፈኛ ኃይሎች የስንቅና ትጥቅ የሚያቀርቡትም ሆነ የአክራሪዎቹ ዋና ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ማዳክም ሕዝበ ክርስቲያኑን ደግሞ ቢችሉ እነርሱ ወደሚፈልጉት እምነት መውሰድ ካልሆነ ደግሞ መግደል፣መዝረፍ ማፈናቀል እንዲሁም ሕይወታቸውን በስጋትና በሰቀቀን እንዲገፉ ማድረግ ነው። የመጨረሻ ሕልማቸውም ወድቃ የማትወድቀውን ቤተ ክርስቲያንን ገፍተው መጣል ነው። ይህንን ተግባር ላለፉት አርባና ኀምሳ ዓመታት ይፈጽሙት እንደነበረ ቢታወቅም በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ መልኩንና ዓይነቱን እየለዋወጡ በቤተ ክርስቲያንና በምእመና ላይ ዘመን የማይሽረው ትውልድ የማይረሳው በደል ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ አሁንም እያደረሱ ይገኛሉ።
- Details
- Written by: መጽሐፈ ሲራክ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1281
የተወደዳችሁ አንባብያን በዛሬው የቤተ አብርሃም ዐምድ ዝግጅታችን ይዘንላችሁ የቀረብነው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አገልጋይ ካህን የሆኑትን ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንንን ነው። ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን በ ፲፱፻፷፰ ዓ.ም ወደ ካቴድራሉ መጥተው ማገልገል ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ሲሰጡ ቆይተዋል አሁንም እየሰጡ ነው። ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ምእመናን እንዲበዙ ወደ ተለያየ ቦታ በመዘዋወር ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸዋል፤ አሳድሰዋል። በተቀጠሩበት ደብር በቅስና፣ የሰበካ ጉባኤ አባል በመሆን፣ እንዲሁም ለመንፈሳዊ ሥራ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በመግባት አገልግለዋል።
በሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ስም ሲሠራ የነበረውን አደባባይ የተለያዩ ምእመናንን በማስተባበር አሠርተዋል። በካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ናቸው። ዛሬም ድረስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን የሚጠቅም ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ።
Read more: ‹‹ምእመናን በእምነታቸው እንዲጸኑ እኛ ካህናት ትጉህ እረኛ ልንሆን ይገባል›› - ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን