ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ስምዓ ጽድቅ

ገዳማትን ከጊዜያዊ ድጋፍ የማውጣት አስፈላጊነት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1382
  • ሪፖርታዥ
ገዳማትን ከጊዜያዊ ድጋፍ የማውጣት አስፈላጊነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት ባለቤት ናት።  በመላ ሀገሪቱ በርካታ ጥንታውያን ገዳማት የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ገዳማት ውስጥ የበቁና ዓለምን የናቁ አባቶችና እናቶች በአንድነት ተሰባስበው ገዳማዊ ሕይወትን ይመራሉ።  መታረዝ፣ መራብ፣ መጠማትና መውጣት መውረድ ለእነሱ የዘወትር ክብራቸው ነው።  ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው ሕይወትን በመምራት የክርስቶስን መንግሥት ይናፍቃሉ።  ይሁን እንጅ እነዚህ ገዳማውያን የሚኖሩባቸው አንዳንድ ገዳማት በከፋ የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ችግር ውስጥ ይገኛሉ፤ ቢሆንም ገዳማቱ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ቤተ ክርስቲያን ከሞላ ጎደል ያቅሟን እያደረገች ትገኛለች።  ከአቅም በላይ የሆነውን ደግሞ በጎ አድራጊ ምእመናንን በማስተባበር ገዳማቱ በሚደገፉበት ሁኔታ ላይ  ስትሠራ ቆይታለች።   

በዚህ ረገድ አንዳንድ ገዳማት ከችግራቸው ወጥተዋል፤ በርካቶቹ አሁንም ድረስ በከፍተኛ ችግር ወስጥ ይገኛሉ።  የገዳማቱን ችግር ለመፍታት በማኅበረ ቅዱሳን በኩል በርካታ ስልቶች ተነድፈው ወደ ሥራ ከተገባ ዓመታት አልፈዋል።  ማኅበሩ ከአባላቱ ከሚያገኘው ገቢ በተጨማሪ በጎ አድራጊዎች ምእመናንን በማስተባበር ፕሮጀክት ቀርጾ ገዳማቱን ሲደግፍና ሲያግዝ ቆይቷል።  የዚህ በጎ ተግባር ማሳያ ከሆኑት አንዱ ፈለገ ጥበብ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ  ለማኅበሩ  በስጦታ የሰጡትን “እመጓ” የተሰኘውን መጽሐፍ በመሸጥ በገቢው የሰባት ያህል ገዳማት ፕሮጀክቶች ፍጻሜያቸውን እንዲያገኙ አድርጓል።  

ከመጽሐፉ ሽያጭ የተገኘው ከ፬.፰ ( አራት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን ብር በላይ ለሰባት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ መሆኑንና ፕሮጀክቶቹ መጠናቀቃቸውን አስመልክቶ እንዲሁም ለፈለገ ጥበብ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ዕውቅና ለመሥጠት ጥር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒሰን ሆቴል  በተዘጋጀው መርሐ ግብር ሊቃውንተ 

ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ከተገኙት የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን በትምህርት ሚኒስትርነት እንዳገለገለች አስታውሰው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ ገማትን ከጊዜያዊ ድጋፍ በማውጣት ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ ሊፈጠርላቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።  ዶ/ር ፍሬው አክለውም ፈለገ ጥበብ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ “እመጓ” የተባለውን መጽሐፍቸውን ለቤተክርስቲያን በሥጦታ በማበርከት ከመጽሐፉ ሽያጩ የተሰበሰበው ገቢ ለሰባት የተለያዩ ገዳማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ  እንዲሆን ማድረጋቸው ለቤተ ክርስቲያን፣ ለምእመናንና ለመንግሥት ትልቅ የቤት ሥራ የሠጠ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል። 

ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት ከመንፈሳዊ የዕውቀት ተቋማት ጋር ተለያይተው ሥራ መጀመራቸው አሁን በሀገራችን ለምናየው ምስቅልቅል መንሥኤ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ ለዚህ ሀገራዊ ችግር መፍትሔ ለመስጠትም ሀገራዊ  ዩኒቨርሲቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሀገር በቀል ዕውቀት ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው  የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲም ለወደፊቱ ከገዳማት ጋር በጋራ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል። 

ሌላው በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ደራስያን ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ፈለገ ጥበብ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውን በስጦታ በመለገስ የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት እንዲረዱበት ማድረጋቸው የሚያስመሰግንና ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው ያሉ ሲሆን መጽሐፉ እጅግ ተነባቢ በመሆኑ ከንባብ ባህል ርቆ የቆየውን ትውልድ ወደ ንባብ ባህል እንዲመለስ ያደረገ መጽሐፍ እንደሆነም አስረድተዋል። 

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መላኩ አላምረው በበኩላቸው “አንዳንድ መጻሕፍት የጥላቻ ሐውልትን የሚተክሉ ሲሆኑ እንደፈለገ ጥበብ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ዓይነቱ መጽሐፍ ደግሞ ለአንባብያን የሥጋና የመንፈስን ዕውቀት ከመጨመራቸው ባሻገር የሚለካ መልካም ውጤትም ያስገኛሉ” ብለዋል።  በሀገራችን በአብዛኛው ለቱሪስት መስህብነት የሚያገለግሉት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት እንደሆኑ የጠቆሙት ኃላፊው ገዳማቱ የጎብኝዎቻቸው ቁጥር እንዲጨምርና በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ሥራ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል።  

Read more: ገዳማትን ከጊዜያዊ ድጋፍ የማውጣት አስፈላጊነት

“መንፈሳዊ የቱሪስት መዳረሻዎች የትውልዱን ሞራል ከመገንባት ባሻገር መንፈሳዊ ርካታን የሚሰጡ ናቸው” - ፈለገ ጥበብ ደ/ር አለማየሁ ዋሴ (የእመጓ መጽሐፍ ድራሲ)

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 798
“መንፈሳዊ የቱሪስት መዳረሻዎች የትውልዱን ሞራል ከመገንባት ባሻገር መንፈሳዊ ርካታን የሚሰጡ ናቸው”                                               -  ፈለገ ጥበብ ደ/ር አለማየሁ ዋሴ (የእመጓ መጽሐፍ ድራሲ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መካናትና የአደባባይ በዓላቷ ናቸው።  በዚህም ሀገርና መንግሥት ተጠቃሚዎች ናቸው።  በተለይ መንግሥት ከቱሪዝም ዘርፍ የሚያገኘው ገቢ ቀላል አይደለም።  ነገር ግን በአብዛኛው የገቢ ምንጭ የሆኑትን ዘመን የጣላቸውንና ጊዜ  የረሳቸውን ገዳማትና አድባራት በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ፤ ከጊዜ ብዛት የፈረሱና የተጎሳቆሉት ደግሞ እንዲጠገኑ የማድረግ ተግባር ውስጥ ሲገባ አይስተዋልም።  ለከተሞችና ለገጠር ቀበሌዎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ በሚደረግበት ጊዜ እንኳ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶችን  ያገለለ እንደሆነ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ በቅርቡ ባሕር ዳር በተዘጋጀ መርሐ ግብር ላይ ካቀረቡት ሪፖርት ማርጋገጥ ተችሏል።  ለምሳሌ በቅርቡ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወቅት በሽታውን ለመከላከል የሚያስፈለጉ ግባአቶችንና ሕክምናዎችን የአብነት ተማሪዎች ማግኘት አልቻሉም።  የአብነት ተማሪዎች የሀገሪቱ ዜጋ አንድ አካል ሆነው ሳለ በመንግሥት ከሚቀርቡ ድጋፎችና ማኅበራዊ አግልግሎቶች ውጭ ሲደረጉ ቆይተዋል።   

ለገዳማቱና አድባራቱ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ሳያሟሉ ከቱሪዝም ሀብት የሚገኘውን ገቢ ብቻ መሰብሰብ መንግሥትንና ሀገርን ውጤታማ አያደርግም።  መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን እያደረገ ያለው ድጋፍ አናሳ ወይም ጭራሽ የሌለ መሆኑን የተረዳችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የገንዘብ አቅም ካላት በራሷ ከሌላት ደግሞ ልጆቿን አስተባብራ በጊዜ ብዛት የወደቁ ገዳማትን ጠግና የዕለት ቀለብ የሌላቸውን ደግሞ የዕለት ቀለብ ሰፍራ ገዳማዊ ሕይወት እንዲመሩ አድርጋለች።  ከከተማ የራቁ ገዳማትና አድባራት አቅም በፈቀደ ሁሉ የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስትሠራ ቆይታለች።

Read more: “መንፈሳዊ የቱሪስት መዳረሻዎች የትውልዱን ሞራል ከመገንባት ባሻገር መንፈሳዊ ርካታን የሚሰጡ ናቸው” - ፈለገ ጥበብ ደ/ር አለማየሁ ዋሴ (የእመጓ መጽሐፍ...

አስተርእዮ ማርያም

Details
Written by: በእህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1428
  • የሕፃናት ዓምድ
አስተርእዮ ማርያም

የእግዚአብሔር ልጆች! እንደምን ከርማችኋል? በእግዚአብሔር ጥበቃ በሰላምና በጤና እንደቆያችሁን ተስፋ እናደርጋለን፤ በቤታችሁ ሆናችሁ ትምህርታችሁን በንቃት እየተከታተላችሁ ነው? በጣም ጎበዞች! በመንፈሳዊም በሥጋዊም ዕውቀት ማደግ ይኖርባችኋልና በርቱ! 

ልጆች! ዛሬ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት ታሪክ ይዘንላችሁ ቀርበናልና ተከታተሉን!

ልጆች! በመጀመሪያ ‹‹አስተርእዮ›› ማለት መገለጥ ማለት ነው። ‹‹አስተርእዮ›› ቃሉ ‹‹አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ›› ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው።  ልጆች! ጌታችን መድኃኒታችን ኢሱስ ክስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት (የታየበት) አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ዋዜማ ጊዜ ‹‹ዘመነ አስተርእዮ›› ይባላል።

Read more: አስተርእዮ ማርያም

የቤተ ክርቲስያን አብያተ መጻሕፍት ነገር

Details
Written by: ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1060
  • ትዝብት

የኢትዮጵያ ጥንታዊም ሆነ ዘመናዊ ታሪኮች የሚጠኑት በአመዛኙ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ምንጭ እየተደረጉ ነው።  የሀገራችንም የባህል፣ የትምህርት፣ የማኅበራዊ እሴቶች ቤተ መዛግብት ሆና ስታገለግል የኖረችው ቤተ ክርስቲያን ነች።  ስለዚህ የሀገራችንና የውጪ ሀገር ሊቃውንት የጥናት ማእከል ቤተ ክርስቲያንና የቤተክርስቲያን ሀብቶች ናቸው።  በተለይ የቤተ ክርስቲያን የጽሑፍ ሀብቶች እጅግ ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ናቸው።  ቅርስ ከመሆናቸውም አልፎ ለጥናት ምርምር ዋነኛ የመጀመሪያ ደረጃ ምንጮች ናቸው።   

እነዚህ መጻሕፍት በየገዳማቱና አድባራቱ ዕቃ ቤቶች በክብር ተቀምጠው እንደሚገኙ ይታወቃል፤ ሌሎች ደግሞ ከቀደሙ ዘመናት ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች/በምርኮና በዝርፊያ/ ከሀገር ወጥተው የሌሎች ሀገራት ሙዚየሞችና አብያተ መጻሕፍት ማክበሪያ ሆነዋል።  ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ደቀ መዛሙርት ሳይቀሩ ለምርምርና ጥናት የሚፈልጓቸውን መጻሕፍት በቀላሉ ማግኘት እንዳይችሉ አድርጓል።  በአንድ በኩል በየገዳማቱና አድባራቱ መጻሕፍት መቀመጣቸው የማይጎዳ ሆኖ ለጥናትና ምርምር ግን በቀላሉ የማይገኙ፣ የማይፈቀዱ ሆነው ይታያሉ።  በውጪ ሀገራት ያሉት የገንዘብና የውጪ ጉዞ ሂደት ለማይቀናቸው ተመራማሪዎች በቀላሉ የሚገኙ አይደሉም። 

Read more: የቤተ ክርቲስያን አብያተ መጻሕፍት ነገር

ጥቅም ፍለጋ የገባሁበት ትዳር መውጫ አሳጥቶኛል

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1214
  • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ

ውድ የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጆች እንደምን ሰነበታችሁ ስሜ ወለተ ገብርኤል ይባላል የምኖረው አሜሪካን ሀገር ሲሆን እድሜዬ ወጣት ከሚባሉት ውስጥ ነው።  በዓለማዊ ትምህርት ሁለተኛ ዲግሪ አለኝ በልጅነቴ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አድጌያለሁ ያቺ እርሾ ናት ወደ እናንተ እንድጽፍ ያነሳሳችኝ።  ወደ አሜሪካን ሀገር የሔድኩት ዲቪ የደረሰው የድሮ የትምህርት ቤት የክፍል ጓደኛዬን አግብቼ ነው።  ያገባሁት አሜሪካን ሀገር ለመሄድ እንጂ የምወደው እና ትዳር መስርቼ አብሬው ለመኖር የምፈልገው የምወደው ሌላ የልጅነት ጓደኛ አለኝ።  ያገባሁት ከዚህ ሀገር እንድወጣ ብቻ እንደሆነ ልቤ ቢያውቅም በተቃራኒው አግብቶ የወሰደኝ የክፍል ጓደኛዬ ግን ዛሬም ድረስ የእውነት ጋብቻ ከኔ ጋር እንደፈጸመ ነው የሚያውቀው።  እሱን ፈትቼው ፍቅረኛዬን አግብቼ ወደ አሜሪካን ሀገር ለመውሰድ እቅድ አለኝ ይህንንም ከፍቅረኛዬ ጋር ቤተ ክርስቲያን በመሄድ እንደማልከዳው ነገሮች ሲመቻቹ ልጁን ፈትቼ እሱን በማግባት እንደምወስደው ቃል ገብቻለሁና ነው።  ውድ የስምዐ ጽድቅ አዘጋጆች አሁን እያስጨነቀኝ ያለው እንደ እውነተኛ ሚስቱ የሚያስበኝ የአሜሪካው ባለቤቴ እንድወልድ ይፈልጋል እኔ ደግሞ ገና የማገባውና የምጠብቀው ሰው ስላለ ይህንን መፈፀም አልችልም።  እውነቱን ነግሬው ለመለያየት እጅግ ተቸግሬአለሁ።  ምክንያት ፈልጌ ልጣላው ሁሉ ብዙ ሞከርኩ ነገር ግን ለማደርግበት ክፉ ነገር ሁሉ ይቅርታ እያደረገ ያልፈኛል።  ኢትዮጵያ ያለው ፍቅረኛዬ ደግሞ የፍቺዬን ቀን በጉጉት እየጠበቀ ነው።  የኔም አካል አሜሪካን ይሁን እንጂ ልቤ ኢትዮጵያ ካለው ፍቅረኛዬ ጋር ነው።  በዚህ ምክንያት ፍርሃቴ ጨምሮ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መጸለይ ሁሉ አቁሜያለሁ።  ጥቅም ፍለጋ እንደ ቀልድ የገባሁበት ነገር መውጫ አሳጥቶ እንቅልፍ ነስቶኛልና ከዚህ ጭንቀት እንዴት ልውጣ? እባካችሁ ከጭንቀቴ የምገላገልበትን መንገድ ጠቁሙኝ። 

Read more: ጥቅም ፍለጋ የገባሁበት ትዳር መውጫ አሳጥቶኛል

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም ክፍል ሁለት

Details
Written by: መጽሐፈ ሲራክ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1157
  • ቤተ አብርሃም
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ  ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም                                                                    ክፍል ሁለት

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ በፊት በነበረው እትም ላይ ማቅረባችን ይታወሳል።  ቀጣዩንና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። 

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከ፲፱፻፺ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ፳፻ ዓ.ም ድረስ ‹‹በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ተመድበው ጥንታውያን ገዳማትን አስተዳድረዋል›› በሚለው ዐረፍተ ነገር የዓ.ም ስሕተት አለበት።  ብፁዕነታቸው በኢየሩሳሌም የቆዩት ለ፲ ዓመት ሳይሆን ከ፲፱፻፺ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ለ፫ ዓመት ከ፭ ወር ነው።  ቀሪውን ማለትም ከ፲፱፻፺፫ ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ እስከ ፳፻ ዓ.ም ድረስ ያለውን ጊዜ የቆዩት ደግሞ አሜሪካን ሀገር መሆኑን እየገለጽን ለተፈጠረው ስሕተት ይቅርታ እንጠይቃለን።  

ብፁዕነታቸው የመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በሩሲያና በአሜሪካን ተምረው እዚያው ኮሌጅ ተመድበው የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናትን ታሪክ በማስተማር ላይ ነበሩ።  በ፲፱፻፸ ዓ.ም ለይፋዊ ጉብኝት እና ስብሰባ ወደ ሩሲያ በሄዱት ሦስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጥሪ እንደተደረገላቸው አውስተናል።  በጊዜው የቅዱስነታቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት የመጡት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር)ወቅቱ በ፲፱፻፸ ዓ.ም ቀይ ሽብር የሚካሄድበትና ብዙ ሰው የሚገደልበት ወቅት ስለነበር በተለይም በሀገራችን ታላቅ ሕዝባዊ ቀውስ ስለነበር ሰዎች እዚያው እንዲቀሩ ቢለምኗቸውም የቅዱስ ፓትርያርኩን ‹‹ሀገርህ ትፈልግሃለች ›› ጥሪ ችላ ብለው ጥሪያቸው ማርኳቸው ወደ ሀገር እንደተመለሱ የሕይወት መቅረት እንዳልቻሉ ይልቁንም አባታዊ ፍቅራቸውና ታሪካቸው ይናገራል።   

Read more: ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም ክፍል ሁለት

የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር የመልካም ሥራ ተምሳሌት መሆኑ ተገለጠ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 09 February 2021
Hits: 1097
  • አጫጭር ዜናዎች
የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር የመልካም ሥራ ተምሳሌት መሆኑ ተገለጠ

የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን እያበረከተ ባለው አስተዋጽኦ የመልካም ሥራ ምሳሌ መሆኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጡ።  

ቅዱስነታቸው ይህንን የገለጹት የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የሥራ ባልደርቦቻቸው ለቤተ ክርስቲያን ልማትና ሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀላቸው የምስጋናና የዕውቅና መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልእክት ነው።  

ቅዱስነታቸው በጽሕፈት ቤታቸው የጋበዟቸውን እንግዶች ባነጋገሩበት ወቅት የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አድንቀው ይህ መልካም ሥራ ለሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አርአያ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።  ‹‹ሃይማኖታችን የተለያየ ቢሆንም ፍቅራችንና አንድነታችንን አያሳሳውም ኢትዮጵያዊነታችንንም አያጠፋውም›› በማለትም አክለዋል።   

እንደ ቅዱስነታቸው ገለጻ ሀገራችን የጋራ እስከሆነች ድረስ ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ በጋራ በአንድነትና በፍቅር ሊኖሩ ይገባል።  መገፋፋትና የርስ በርስ ግጭት ውስጥ መግባትን አስወግዶ ለሀገር ልማትና እድገት መሥራት ያስፈልጋል።  የሀገራችንን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር የምንጠብቀው በሃይማኖት ልዩነት፣ በዘርና በቀለም ሳንለያይ ከሆነ ብቻ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር የሰላምና የልማት ምሳሌ መሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ደስ ሊለው ይገባል፤ በሀገራችን ያሉ ሁሉም የፖለቲካ አመራሮች የድሬ ደዋን የመልካም ሥራ ምሳሌነት በመውሰድ ለእውነትና ለሀገር አንድነት አጥብቀው እንዲሠሩ መክረዋል።  

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ኃላፊ አፈ መምህር አባ ገ/ሥላሴ ጌትነት በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ተወርሰው የተመለሱ የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች እንዳሉ ጠቅሰው ከውርስ ከተመለሱት ቦታዎች መካከል በአንዱ ላይ ለገቢ ማስገኛ የሚውል ሕንፃ ለመሥራት ታኅሣሥ ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሠረት ድንጋይ እንዳስቀመጡ ተናግረዋል።  

የድሬ ደዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ማትያስ በቀለ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በድሬ ደዋ ሀገረ ስብከት ላለፉት ሦስት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ሁከትና ብጥብጥ ውሥጥ በመቆየቱ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በነፃነት ሥርዓተ አምልኳቸውን ማከናወን መቸገራቸውንና የአደባባይ በዓላትንም በሥጋት ያከብሩ እንደነበር ጠቅሰው፤ “አሁን ያለው የከተማ አስተዳደር አመራር ቁርጠኛ በመሆኑ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሰላምና በልማት ላይ ተቀራርቦ እየሠራ ነው” ብለዋል።  

ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም “የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር በተለይ ዘንድሮ ፴ ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ለአደባባይ በዓላት ማክበሪያነት እንዲውል ከመስጠቱ ባሻገር የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ያልነበራቸው የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ሁሉ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲኖራቸው አድርጓል›› ብለዋል።  

ሀገረ ስብከቱ የመካነ መቃብር እጥረት እንዳለበት ለከተማ አስተዳደሩ ባቀረበው ጥያቄ መሠረትም በቅርቡ ለመካነ መቃብር የሚውል ተጨማሪ መሬት እንደሚሰጥ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ “ሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር በመማር መንግሥትና የእምነት ተቋማት በጋራ መሥራታቸው ለሀገር ሰላምና ልማት ሊኖረው የሚችለውን ድርሻ ሊገነዘቡ ይገባል” ብለዋል።  

በዚሁ የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሕመድ መሐመድ ቡህ ከተማ አስተዳደራቸው ለቤተ ክርስቲያን ባበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጠው ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸው ዕውቅና ለበለጠ መልካም ሥራ እንዲነሳሱ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል።  

“ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን የኪነ ሕንፃ ጥበብ እድገት ያበረከተቻቸውን አስተዋጽኦ ያደነቁትና ለተደረገላቸው መስተንግዶና አቀባበል እንዲሁም ለተሰጣቸው የዕውቅና ሽልማት ምስጋናቸውን ያቀረቡት የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ልዩ አማካሪና የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራት ገብረየስ ናቸው። 

 

‹‹ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች የሀገር መሠረቶች በመሆናቸው ተጠብቀው ለትውልድ ሊተላለፉ ይገባል››                             ብፁዕ አቡነ አብርሃም  (የባሕ ርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 23 January 2021
Hits: 833
‹‹ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች የሀገር መሠረቶች በመሆናቸው ተጠብቀው ለትውልድ ሊተላለፉ ይገባል››                                      ብፁዕ አቡነ አብርሃም  (የባሕ ርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

ገዳማትና የአብነት  ትምህርት ቤቶች የሀገር መሠረቶች በመሆናቸው ጠብቆና ተንከባክቦ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የባሕ ርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገለጹ፡፡

ብፁዕነታቸው ይህንን የተናገሩት ‹‹የእመጓ ፍሬዎች›› በሚል ስያሜ በማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ከእመጓ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ የተከናወኑ ሰባት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን አስመልክቶ ጥር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በባሕ ርዳር ዩኔሰን ሆቴል በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ነው፡፡

የገዳማትን ችግር ለመፍታት ቤተ ክርስቲያንን ብቻ ባለድርሻ ማድረግ ተገቢ እንዳልሆነ ያነሡት ብፁዕነታቸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያናቸው በእርጅናና በልዩ ልዩ ምክንያቶች የፈረሱ ገዳማት እንዲታደሱና የዕለት ጉርስ የሌላቸው ቀለብ አግኝተው የተጠናከረ ገዳማዊ ሕይወት እንዲመሩ መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ብፁዕነታቸው አያይዘውም ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማት ላይ እየሠራ ያለው መልካም ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው “ከዚህ በፊት ብዙ ሠርቷል፤ ብዙም እየሠራ ነው፤ወደፊትም ብዙ እንደሚሠራ እናምናለን›› ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ደራስያን ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን “ፈለገ ጥበብ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውን በስጦታ በመለገስ የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው ገዳማት እንዲረዱበት ማድረጋቸው የሚያስመሰግንና ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው” ያሉ ሲሆን መጽሐፉ እጅግ ተነባቢ በመሆኑ ከንባብ ባህል ርቆ የቆየውን ትውልድ ወደ ንባብ ባህል እንዲመለስ ያደረገ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ ዲ/ን አንድነት ተፈራ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባቀረቡት ሪፖርት የአብነት ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎቸቸው እንዲሁም ገዳማዊያን ገዳማት ማንኛውም ዜጋ ከመንግሥት የሚያገኘውን ማኅበራዊ አገልግሎት እያገኙ ባለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን አስተባብራ የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋማትንና መሠረተ ልማቶችን ተደራሽ ታደርጋለች ብለዋል፡፡ 

የእመጓ መጽሐፍ ደራሲ ፈለገ ጥበብ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በዕለቱ ባስታለፉት መልእክት አብዛኛው የቱሪስት መዳረሻዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀብቶች እንደሆኑ አስረድተው እነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች የትውልዱን ሞራል ከመገንባት ባሻገር መንፈሳዊ ርካታን የሚሰጡ ቦታዎች ናቸው ካሉ በኋላ የገዳማቱን ገቢ በመጨመር ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ 

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መላኩ አላምረው በበኩላቸው በሀገራችን በአብዛኛው ለቱሪስት መስህብነት የሚያገለግሉት ጥንታውያን ገዳማት መሆናቸውን ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት  የጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምርና ገዳማቱ በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ   የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት 

Details
Written by: በእህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1094
  • ፍሬ ከናፍር
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ    የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን››  -              	ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ                    ክፍል ሁለት 

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በጥሞና ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ በቃለ ወንጌል በእምነታቸው እንዲጸኑ በማድረግ በሀገረ ስብከቱ እንደ እቅድ የተያዘ ነገር አለ?  እየተሠራ ነው?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ አዎን እነዚህን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በተለየ መልኩ ተይዞ እየተሠራ ነው፡፡ አደራጅቶ በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል የሚመራ ቡድን/ልኡክ አለ ይህን ልኡክ፣ ማኅበራትን በማቀናጀት ሰፋፊ ጉባኤያትን እየሠራን ነው፡፡ በእቅድም ይዘን ለመሥራት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ አሁን በቅርቡም ከአዲስ አበባ ዘማርያን እና ሰባክያነ ወንጌልን በመጋበዝ  በመቻራ ወረዳ ላይ ታላቅ ጉባኤ አዘጋጅተናል፡፡ በቀጣይም ከአብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤ ጋር በመነጋገር እንደዚህ ዓይነቱን የማጽናናት ሥራ በሌሎችም ወረዳዎች አጠናክረን የመቀጠል እቅድ ነው ያለን፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ ቤተ ክርስቲያን የሚቃጡባትን መሰል ጥቃቶች ለመመከት ምን ማድረግ  አለባት?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ ስለ ቀጣይ ቤተ ክርስቲያን ሥራ ስንነጋገር በመጀመሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብለን እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ከማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ትልቁና የመጨረሻው ሥልጣን ሰጪና ወሳኝ አካል ነውና፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረቡለትን ሪፖርቶች በመረጃ በመያዝ ከሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር ቀርቦ በመነጋገር እነዚህ ችግሮች መስመር የሚይዙበትን መፍትሔ በማምጣት መመሪያዎችን በተዋረድ ወደታች ሊያወርድልን ይገባል፡፡ 

Read more: ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት

‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ   የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት 

Details
Written by: በእህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 990
  • ፍሬ ከናፍር
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ    የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን››  -              	ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ                    ክፍል ሁለት 

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በጥሞና ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ በቃለ ወንጌል በእምነታቸው እንዲጸኑ በማድረግ በሀገረ ስብከቱ እንደ እቅድ የተያዘ ነገር አለ?  እየተሠራ ነው?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ አዎን እነዚህን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በተለየ መልኩ ተይዞ እየተሠራ ነው፡፡ አደራጅቶ በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል የሚመራ ቡድን/ልኡክ አለ ይህን ልኡክ፣ ማኅበራትን በማቀናጀት ሰፋፊ ጉባኤያትን እየሠራን ነው፡፡ በእቅድም ይዘን ለመሥራት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ አሁን በቅርቡም ከአዲስ አበባ ዘማርያን እና ሰባክያነ ወንጌልን በመጋበዝ  በመቻራ ወረዳ ላይ ታላቅ ጉባኤ አዘጋጅተናል፡፡ በቀጣይም ከአብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤ ጋር በመነጋገር እንደዚህ ዓይነቱን የማጽናናት ሥራ በሌሎችም ወረዳዎች አጠናክረን የመቀጠል እቅድ ነው ያለን፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ ቤተ ክርስቲያን የሚቃጡባትን መሰል ጥቃቶች ለመመከት ምን ማድረግ  አለባት?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ ስለ ቀጣይ ቤተ ክርስቲያን ሥራ ስንነጋገር በመጀመሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብለን እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ከማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ትልቁና የመጨረሻው ሥልጣን ሰጪና ወሳኝ አካል ነውና፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረቡለትን ሪፖርቶች በመረጃ በመያዝ ከሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር ቀርቦ በመነጋገር እነዚህ ችግሮች መስመር የሚይዙበትን መፍትሔ በማምጣት መመሪያዎችን በተዋረድ ወደታች ሊያወርድልን ይገባል፡፡ 

Read more: ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት

‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ   የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት 

Details
Written by: በእህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1093
  • ፍሬ ከናፍር
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ    የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን››  -              	ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ                    ክፍል ሁለት 

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በጥሞና ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ በቃለ ወንጌል በእምነታቸው እንዲጸኑ በማድረግ በሀገረ ስብከቱ እንደ እቅድ የተያዘ ነገር አለ?  እየተሠራ ነው?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ አዎን እነዚህን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በተለየ መልኩ ተይዞ እየተሠራ ነው፡፡ አደራጅቶ በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል የሚመራ ቡድን/ልኡክ አለ ይህን ልኡክ፣ ማኅበራትን በማቀናጀት ሰፋፊ ጉባኤያትን እየሠራን ነው፡፡ በእቅድም ይዘን ለመሥራት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ አሁን በቅርቡም ከአዲስ አበባ ዘማርያን እና ሰባክያነ ወንጌልን በመጋበዝ  በመቻራ ወረዳ ላይ ታላቅ ጉባኤ አዘጋጅተናል፡፡ በቀጣይም ከአብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤ ጋር በመነጋገር እንደዚህ ዓይነቱን የማጽናናት ሥራ በሌሎችም ወረዳዎች አጠናክረን የመቀጠል እቅድ ነው ያለን፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ ፦ በቀጣይ ቤተ ክርስቲያን የሚቃጡባትን መሰል ጥቃቶች ለመመከት ምን ማድረግ  አለባት?

ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ፦ ስለ ቀጣይ ቤተ ክርስቲያን ሥራ ስንነጋገር በመጀመሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብለን እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ከማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ትልቁና የመጨረሻው ሥልጣን ሰጪና ወሳኝ አካል ነውና፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረቡለትን ሪፖርቶች በመረጃ በመያዝ ከሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር ቀርቦ በመነጋገር እነዚህ ችግሮች መስመር የሚይዙበትን መፍትሔ በማምጣት መመሪያዎችን በተዋረድ ወደታች ሊያወርድልን ይገባል፡፡ 

Read more: ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን›› - ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ክፍል ሁለት

የጥምቀት በዓል   

Details
Written by: ቀሲስ ዘክርስቶስ ጸጋዬ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1556
  • የሕፃናት ዓምድ

የተወዳዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ሕፃናት! እንደምን ከርማችኋል? በእግዚአብሔር ቸርነት በሰላምና በጤና እንደቆያችሁን ተስፋ እናደርጋለን፤ ትምህርታችሁን በንቃት በመከታትል በመንፈሳዊም በሥጋዊም ዕውቀት ማደግ ይኖርባችኋልና በርቱ!

ልጆች! ዛሬ ስለጥምቀት በዓል እናስተምራችኋለንና በጥሞና ተከታተሉ! 

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ዕለት የምናከብረው በዓል የጥምቀት በዓል ይባላል፡፡ ጥምቀት የሚለው ቃል ‹‹ተጠምቀ፣ ተጠመቀ›› ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጕሙም በውኃ ‹‹መነከር፣ በገዛ እጁ ወይም በሰው እጅ ሥርየት ወይንም ልጅነት ለማግኘት መጠመቅ›› ማለት ነው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፭፻፪) ጥምቀት በተቀደሰ ውኃ መጠመቅ ማለት ነው፤ ይኸውም ቀሳውስት በጸሎት ሥርዓት ከቀደሱት በኋላ ምእመናንን (ክርስቲያኖችን) በተቀደሰው ውኃ ያጠምቋቸዋል፡፡ ካህናቱ ሕዝቡን ጸበል ከረጩ በኋላ ልዩ ልዩ ሥርዓቶች ይደረጋሉ፤ ከዚያም ታቦታቱ ከድንኳን ወጥተው ወደ የመጡበት ቤተ ክርስቲያን ይሔዳሉ፡፡ ‹‹ጥሩ ውኃንም ረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ትጠራላችሁ›› (ሕዝ. ፳፮፥፳፭) ተብሎ እንደተነገረው፡፡ ውኃ ለሰው ልጆች በሙሉ አስፈላጊ ነው፤ ያለ ውኃ መኖር አይቻልም፡፡ ጥምቀትም ለሁሉም የሚያስፈልግ በመሆኑ ያለ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይቻልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ውኃ መልክ ያሳያል፤ መልክ ያለመልማል (ያጠራል)፡፡ ጥምቀትም መልክአ ነፍስን ያሳያል፤ መልክአ ነፍስን ያለመልማልና (ያጠራልና) ጌታችን  በውኃ ተጠመቀ፡፡

Read more: የጥምቀት በዓል

Page 10 of 19

  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት