ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ስምዓ ጽድቅ

በዓል እና ባህል  

Details
Written by: በኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1406
  • ትዝብት

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት  በርካታ መንፈሳዊ በዓላት አሉ፡፡ እነዚህም በዓላት በየሀገሩ፣ በየወገኑ፣ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሥርዓት መሠረት ይከበራሉ፡፡ ለምሳሌም በዓለ ልደት፣ በዓለ ጥምቀት፣ በዓለ ሆሳዕና ወዘተ በተለያየ ቀን፣ በተለያየ ሥርዓት፣ በተለያየም የባህል ዐውድ ውስጥ ይከበራሉ፡፡ የግብጹን ከኢትዮጵያ፣ የሶርያውን ከአርመን የሚለየው ብዙ ሥርዓት ሊኖር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ የበዓሉን ማእከልና ዓላማ ግን አንድ ነው እርሱም የበዓሉ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ማመስገን ነው፡፡ 

አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስን በበዓሉ በመስበክ፣ በማክበር፣ በበዓሉም መባረክን በመፈለግ በኩል አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ዓላማ ስላላቸው የአንድ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ መሆናቸውን ይመሰከራሉ፡፡

በዓላት የሚከበሩበት የባህል ዐውድ ግን ከበዓሉ ዓላማ በላይ ከዋለ፣ በበዓሉ ዕለት ከሚነበበው ወንጌል፣ ከሚነገረው ተኣምር፣ ከሚሰበከው ስብከት በላይ በዓሉን ለማድመቅ ተብለው የገቡ በየጊዜው የዳበሩና እየተጨመሩ ያሉ አላባዎች ከገነኑ፤ የበዓሉም ዓላማ የበዓሉን የአከባባር መንገድና ጌጣጌጦች ማንገሥ ላይ ካተኮረ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ያለውን የበዓል መንፈስ እጅግ እያራራቀው፣ ሌላው ቀርቶ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንኳን በዓሉ ልዩ ልዩ ባህል ባላቸው ማህበረሰቦች መካከል መራራቅን ሊያስከትል ይችላል፡፡

Read more: በዓል እና ባህል

‹‹ በደረሰብኝ ተደጋጋሚ ችግር ሰዎችን ጠላሁ››

Details
Written by: ማኅበረ ቅዱሳን
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1469
  • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ

ይድረስ ለምሥጢሬን ላካፍላችሁ አዘጋጆች፤ እንደምን ከረማችሁ? ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁንና ይህን ጽሑፍ ወደ እናንተ ለማድረስ አብቅቶኛል፡፡ እናም ችግሬን ትጋሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ፡፡  

በጎልማሳነት ዕድሜ ላይ እገኛለሁ፤ ዛሬ ላይ ሆኜ የትናንት ሕይወቴን ሳስብ እጅግ ይከፋኛል፤ ብዙ ችግርና መከራም ያሳለፍኩ ሰው በመሆኔ ኑሮዬ መራር ነው፡፡ በተለይም ከወጣትነት ዕድሜ ጅማሮ እስከ አሁን ድረስ በተደጋጋሚ ግፍና በደል ደርሶብኛል፤ ሰዎች የእኔን ፍላጎት ከመጋፋት ጀምሮ በተለያየ መንገድ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡ የቅርብ ሰዎች በመሆናቸውም ጉዳቱን እጥፍ አድርጎታል፤ ከዚያም ባሻገር አካላዊ ጥቃትን ያደረሱብኝ እነዚሁ ሰዎች በሕይወቴ ትልቅ የቁስል ጠባሳ አሳርፈውበታል፡፡ ምክንያት ለሌለው ነገር ወንድን ለማጥቃት በሚጠቀሙበት ጉልበትም ደብድበውኛል፤ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ነበር፤ እንደዚህ አድራጊዎቹም አብሬአቸው ያደኩና የኖርኩ መሆኑ ችግሩን የባሰ የከፋ አድርጎብኛል፡፡ ይህ ሲደጋገምም የማንነት ጥይቄም አስነስቶብኝ ነበር፤ እነርሱንም ቤተሰቦቼ ብዬ ማሰብ እስኪያቅተኝ ድረስ አስጨነቀኝ፤ ድፍረት አግኝቼም በጠየኳቸው ጊዜ ተገቢውን ምላሽ ሳይሰጡ አስተባብሎ ማለፍን መረጡ፡፡ 

Read more: ‹‹ በደረሰብኝ ተደጋጋሚ ችግር ሰዎችን ጠላሁ››

ዘመኑን መዋጀት ተገቢ ነው

Details
Written by: በዝግጅት ክፍሉ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1247
  • ርዕሰ አንቀጽ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ ከምታከብራቸው በዓላት ውስጥ አንዱ የጥምቀት በዓል ነው፡፡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ምእመን የሚሰበሰብበት ፣ የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚከወኑበት ከዋዜማው (ከከተራው) ጀምሮ እስከ ዕለቱ የጥምቀት በዓል ድረስ አገልግሎቱ በሰፊው የሚሰጥ ከሌሎቹ የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሁሉ ለየት ባለ ሁኔታ የሚከበር በዓላችን ነው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ፣ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን  ወጥተው ወደ ተዘጋጀላቸው ማደሪያ በመሄድ የሚከበር ታላቅ በዓላችን ነው፡፡ 

የጥምቀት በዓል ምእመናን በብዛት የሚገኙበትና የሚከበር ብቻ ሳይሆን በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች (ቱሪስቶች) የሚታደሙበት ታላቅ የአደባባይ በዓላችን ጭምርም ነው፡፡ ይህ  ሕዝብ በብዛት የሚሳተፍበት ታላቅ በዓል ሃይማኖታዊ ዕሴቱን ፣ ባሕላዊ ወጉን በጠበቀ መልኩ ሲከናወን መቆየቱ ዓለም አቀፍ ትኩረትን በመሳቡ በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ለመመዝገብ የበቃ እንዲሁም ለኢትየጵያውያን በተለይም ለኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ጭምር ታላቅ ኩራትም ነው፡፡ 

Read more: ዘመኑን መዋጀት ተገቢ ነው

“የጥምቀት በዓል ለሀገራችን አንድነት ታላቅ ምሳሌ ነው” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1111
  • አጫጭር ዜናዎች
“የጥምቀት በዓል ለሀገራችን አንድነት ታላቅ ምሳሌ ነው”                                                        ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

‹‹ የጥምቀት በዓል ለሀገራችን አንድነት ታላቅ ምሳሌ ነው›› ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥር ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በጃንሜዳ በተከበረው የከተራ በዓል ላይ ተናገሩ፡፡ 

ቅዱስነታቸው አያይዘውም ‹‹ይህ በዓል  በዩኒስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ እና ብዙ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚሳተፉበት በዓል ነው›› ብለዋል፡፡ በዓሉ በክርስትናችንና በእምነታችን ምን ያህል ጠንካራ እንደሆንን የምንገልጽበት ታላቅ በዓል በመሆኑ ምእመናን በአንድነት እና በፍቅር ሆነው ማክበር እንደሚገባቸው ጭምር አሳስበዋል፡፡

በዚሁ ታላቅ በዓል ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ “የጥምቀት በዓል የመልካችን ሰሌዳ የገጽታችን መገንቢያ ነው” ሲሉ  ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል፡፡

የገጽታችን መገንቢያና የታሪካችን መንገሪያ  የሆነውን የጥምቀት በዓል ማጉላትና መጠበቅ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚጠበቅ ያነሱት ከንቲባዋ “የጥምቀት በዓል በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ ቅርሱ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ ሆኗል” ብለዋል፡፡

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ ልዩ በህል፣ቋንቋ፣ማንነትና ቀለም ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሰባስበው በአንድ ላይ በዓሉን ማክበራቸው የጥምቀትን በዓል ልዩ ገጽታ አጎናጽፎታል፡፡ ነገር ግን ልዩነታችንን ምክንያት አድርገን ጫፍ ለጫፍ  ቆመን ሀገር መገንባት፣ እግዚአብሔርን ማምለክና በዓላትን በነጻነት ማክበር አንችልም፡፡ 

የጥምቀት በዓል አንድነታችን የሚጠናከርበት፣ሰላማችን የሚረጋገጥበት እና ከፍቅር ስፍር የማንጎልበት በዓል ይሁን ሲሉም  ከንቲባዋ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ለበርካታ ዓመታት የበዓለ ጥምቀት ማክበሪያ ቦታ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው ጃንሜዳ የይዞታ ማርጋገጫ ካርታ ተሠርቶ ለቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድርን የጠየቁ ሲሆን ቦታውንም ለማልማትና ምቹ ለመድረግ ቤተ ክርስቲያን ዝግጁ መሆኗንም በዕለቱ አስታውቀዋል፡፡ 

 

በጥምቀታችን እንድመቅበት በተሰጠን እንወቅበት 

Details
Written by: ዲ/ን አሻግሬ አምጤ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1307
  • ሪፖርታዥ

ኢትዮጵያውያን በፍቅር አብረው እንዳይኖሩ የሚያደርጋቸውን ስስ ብልት እየፈለጉ ሲያጋጩ የነበሩ አሁንም በጥፋታቸው የቀጠሉ አካላት በመንግሥት መዋቅርም፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥ መኖራቸው አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው እውነታ ነው። ከመገለጫዎች አንዱም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአደባባይ በዓላት እንዳይከበሩ ምክንያት እየፈለጉ ማስተጓጎል፣ የሚደርስባቸውን መከራም ጆሮ ዳባልበስ ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን አድሎ የሚታይበት እኩይ ድርጊት እንዲታረም እና ወጥነት ያለው ሥርዓት እንዲሰፍን ስትጠይቅ ቆይታለች። የቅድመ አደጋ ስጋት ክትትልና መከላከል ሥርዓት እንዲዘረጋ እስከ መወሰን የደረሰችውም ለዚህ ነበር። ቅዱስ ፓትርያርኩ በጥቅምቱ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተከፈተበት ወቅት “ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ክርስቲያኖች ራሳችንን እናዘጋጅ!” በማለት የተናገሩትም በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው መከራ እየተባባሰ በመቀጠሉ ነው።

 ባለፈው ዓመት ማለትም በ፳፻፲፪ ዓ.ም ዩኒስኮ በዓለም ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ እንዲሆን ያደረገው የጥምቀት በዓል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የሚገልጥ ቢሆንም የኢትዮጵያውያን ሁሉ መለያችን መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። የቤተ ክርስቲያን የሆነው ነገር ሁሉ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መሆኑን ከተረዳን መጠበቅ የሚኖርብንም ሁላችን መሆናችንን መገንዘብ ይኖርብናል። ተባብረን መጠበቅ የሚገባን የኦርቶዶክሳውያንን መገለጫ ብቻ ነው እያልን አለመሆናችንም መታወቅ ይኖርበታል። በሃይማኖት ብንለያይም ያለችን አንድ አገር በመሆኗ ያላትን ሁሉ የመጠበቅ ኃላፊነትም ግዴታም ያለብን ኢትየጵያውያን በሙሉ ነን። የምንጠብቀው የራሳችን ሃይማኖት መገለጫ የሆነውን ብቻ ከሆነ የሌላው ሲወድም የማይገደን ከሆነ አገራችንን የልዩ ልዩ ባህል ባለቤት መሆኗን እየተቃወምን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል።

Read more: በጥምቀታችን እንድመቅበት በተሰጠን እንወቅበት

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም

Details
Written by: መጽሐፈ ሲራክ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 22 January 2021
Hits: 1310
  • ቤተ አብርሃም
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ  ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ላለፉት ፹ ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት አገልግለዋል፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው በሀገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም ከሀገር ውጪም እንጂ፡፡ በትምህርት ረገድም በሀገር ውስጥ እና በውጭው ዓለም ብዙ ዕውቀትን ገብይተዋል፡፡ በተለይ የአብነት ትምህርትን በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ቀስመዋል:: የአብነት ትምህርት ለመማር ወጥተው ወርደዋል ፣የትውልድ ሀገራቸውን ትተው፣ ከውሻ ተከላክለው ፣ ቁራሽ እንጀራ ለምነው ፣ ደበሎ ለብሰው ፣ ተርበው ተጠምተው ጸዋትወ መከራውን በመታገሥ ሁሉን በጸጋ ተቀብለዋል፡፡ ብዙ የሕይወት መሰናክሎችን አልፈው ለትልቅ ማዕረግ በቅተዋል፡፡  

የብፁዕነታቸውን የ፹ ዓመታት የሕይወት ጉዞ እና ሥራዎቻቸውን በሁለት ክፍል ለማቅረብ ወደድን የመጀመሪያውን ክፍል ከተወለዱበት ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ በጸሎትና በቡራኬ እንዲቆዩ እስከተወሰነበት ጥቅምት ወር ፳፻፲፫ ዓ.ም ድረስ ያለውን የሕይወታቸውን ገጽ ወይም ዜና ሕይወት እንደሚከተለው አቅርበነዋል መልካም ንባብ፦

Read more: ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ከ፲፱፻፴፫-፳፻፲፫ ዓ.ም

አጽዋማትንም ሆነ በዓላትን እንደ ቤተ ክርስቲያን እስተምህሮ

Details
Written by: ማኅበረ ቅዱሳን
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 1294
  • ርዕሰ አንቀጽ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩ ዐበይት በዓላት ውስጥ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አንዱ ነው። በዓሉ ከፋሲካ በዓል ቀጥሎ ከረጅም የጾም ወቅት በኋላ የሚከበር እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አባቶችም ሆነ በምእመናን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ፤ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት፣ ሰፊ ዝግጅት ተደርጎበት የሚከበር ትልቅ በዓል ነው። በቤተ ክርስቲያን ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ ሥርዓተ ማኅሌት ተጀምሮ በሥርዓተ ቅዳሴ የሚጠናቀቅ  ልዩ በዓል ነው። በምእመናንም ዘንድ ሁሉም እንደየአቅሙ በቤት ውስጥ ከሚደረገው የምግብ መጠጥ ዝግጅት ባሻገር በዓሉን በቤተ ክርስቲያን በመገኘት ከአባቶች ካህናት ጋር በመሆን በስብሐተ እግዚአብሔር የሚያከብረው ክርስቲያን ቁጥርም ቀላል አይደለም። 

ይሁን እንጅ በቤተ ክርስቲያን ልዩ ቦታ እና ክብር የሚሰጠው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከጊዜ ወደ ጊዜ ሃይማኖታዊ መልኩን፣ መንፈሳዊ ይዘቱን እና ታሪካዊ ክብሩን በለቀቀ መልኩ መከበር ከጀመረ ዘመናትን አስቆጥሯል። እንዲህ ዓይነቱን ፈር የለቀቀ ከመንፈሳዊነትም የተፋታ የበዓል አከባበር  ወደ መንፈሳዊ ይዘቱ ለመመለስ በየጊዜው በአባቶች ትምህርት ቢሰጥም በብዙዎቻችን ዘንድ በቸልታ ሲታይ ቆይቷል። በዚህ የሥርዓት መፋለስ ውስጥ ምእመናን ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ አባቶችም ተሳታፊ መሆናቸው ወይም ነገሩን በቸልታ ማየታቸውም የዐደባባይ ምሥጢር ከሆነ ቆይቷል።

Read more: አጽዋማትንም ሆነ በዓላትን እንደ ቤተ ክርስቲያን እስተምህሮ

“የአብነት መምህራኑ ምግባርና ሃይማኖትን እንጂ የተማሪን ሀገር ሲጠይቁ ሰምቼ አላውቅም” ክፍል አንድ

Details
Written by: መጽሐፈ ሲራክ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 1405
  • ቤተ አብርሃም
“የአብነት መምህራኑ  ምግባርና ሃይማኖትን እንጂ የተማሪን ሀገር ሲጠይቁ ሰምቼ አላውቅም”      ክፍል አንድ

የተወደዳችሁ አንባብያን በዛሬው የቤተ አብርሃም ዓምድ ዝግጅታችን የምናቀርብላችሁ በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የሐዲስ ኪዳን መምህር የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ መምህር አባ ወልደ ጊዮርጊስ ጸጋውን ነው።  በአሁኑ ሰዓት በገዳሙ ጉባኤ ዘርግተው እያስተማሩ ሲሆን በመምህርነት ዘመናቸው ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳትን እና መምህራንን አፍርተዋል። ዛሬ ያላቸውን የሕይወት ተሞክሮ እንዲያካፍሉን  እንግዳ አድርገናቸዋል እነሆ፦  

ስምዐ ጽድቅ፦ አባታችን ከእርስዎ ጋር ይህን ቃለ መጠይቅ እንድናደርግ ስለፈቀዱልን ከልብ እናመሰግናለን። የልጅነት ሕይወትዎን ይንገሩን? የት ተወለዱ? የእናትና የአባትዎ ስም ማን ይባላሉ?

አባ ወልደ ጊዮርጊስ ፦ አመሰግናለሁ የተወለድኩት ሐምሌ ፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ዕለቱ ዕለተ ማክሰኞ በሰሜን ጎንደር እንፍራዝ ከተማ ልዩ ስሙ ደብረ ገነት ማርያም በሚባል ቦታ ነው። እናቴ ወ/ሮ ጥሩዬ ዓለሙ አባቴ አቶ ጸጋው ተሻለ ይባላሉ። 

ስምዐ ጽድቅ ፦ ስለ አብነት ትምህርት ቤት የተማሪነት ሕይወትዎ ይንገሩን ምን ድረስ ተማሩ? 

Read more: “የአብነት መምህራኑ ምግባርና ሃይማኖትን እንጂ የተማሪን ሀገር ሲጠይቁ ሰምቼ አላውቅም” ክፍል አንድ

“የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን” ክፍል አንድ

Details
Written by: እህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 1530
  • ፍሬ ከናፍር
“የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ  የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን”  ክፍል አንድ

ሰኔ ወር ፳፻፲፪ ዓ.ም ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በአገልጋይ ካህናት እና በምእመናን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈጸም ቆይቷል። የተቀናጀ እና በእቅድ የተመራ ምእመናንን፣ አገልጋይ ካህናትንና ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ የጎዳ የጥፋት ዘመቻ በመካሄዱ ሰኔ ወርን አነሳን እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ያደረገ ጥፋት ከተጀመረ ሰነበተ። 

በተለይ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ በኋላ እዚህም እዚያም ይነሱ የነበሩ የጥፋት ቡድኖች በቅድሚያ መዳፋቸውን የሚያሳርፉት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው። ከነዚህ የጥቃት ዒላማ ከነበሩት ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ደግሞ አንዱ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ነው። በወቅቱ በሀገረ ስብከቱ የተፈጸመውን ቤተ ክርስቲያን፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተኮር የጥፋት ዘመቻ እና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ አነጋግረን እንደሚከተለው አቅርበናል ይከታተሉን። 

ስምዐ ጽድቅ፦ በቅድሚያ ሙሉ ስምዎትን ከየት እንደመጡና የአገልግሎት ድርሻዎትን ቢገልፁልን?

Read more: “የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር በዘላቂነት መፍታት ካልተቻለ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላናገኝ እንችላለን” ክፍል አንድ

የዝክራችን መልክ

Details
Written by: ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 4788
  • ትዝብት

ዝክር አንድን ቅዱስ የተወለደበትን፣ ያረፈበትን፣ ተአምራት የሠራበትን፣ መከራ የተቀበለበትን የክብር አክሊል የተቀዳጀበትን….ወዘተ በመሰባሰብ ወይም በተናጠል ማሰብ ማለት ነው። ኦርዶክሳውያን ቅዱሱን ከማሰብ ጀምሮ፣ በጸሎትና ምስጋና እንዲሁም በቅዳሴና በውዳሴ ይዘክሩታል። በቅዱሱ ስም ከሚጠራ ሩቅ ወይም ቅርብ ቤተ ክርስቲያን ወይም ገዳም ሄዶ በመሳለምም ይዘክራሉ። ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ከማጠጣት፣ ቆሎ ከማዘገን ጀምሮ ሰፋ ያለ ድግስ ደግሶ ነድያንን፣ ጎረቤትን ወዳጆችን ጠርቶ ‹‹ብሉልኝ ጠጡልኝ›› በማለትም ይዘክራሉ።….. 

ዛሬ ዛሬ ግን ነባሩን የዝክር መልክ የቀየሩ ክዋኔዎች እየመጡ ነው። በቅዱሱ/በቅድስቷ ስም ተጠራርተው ባልተቀደሱ መንገዶች እየሄዱ ብቻቸውን አብዝተው እየበሉ እየጠጡ ዝክር እንዳደረጉ የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ቆርሰው ለድሆች የማያጎርሱበት፣ ቀድተው ለምስኪኖች የማያጠጡበት ዝክር በርክቷል። ጥቂቶች ከመንደር ተጠራርተው ዛሬ ቅዱስ ‹‹እገሌ›› ነው ብለው በልተው ጠጥተው ከመለያየት በስተቀር ስመ አምላክ ሳይጠራ፣ ስለቅዱሱም ሳይወራ፣ ጸሎት ሳይደረግ፣ ሳይመሰገን በመብል ተጀምሮ በመብል የሚያልቅ ዝክር አለ። ለእነዚህ ወገኖች ዋናው አጀንዳ ተሰብስቦ መብላት ብቻ ነው። 

Read more: የዝክራችን መልክ

ከጋብቻ በፊት የሚኖር ግንኙነት ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር እንዴት ይታያል?

Details
Written by: ማኅበረ ቅዱሳን
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 3754
  • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ

ወደ ቤተክርስቲያን መጣ ሔድ በማለት በበዓል፣ በመንፈሳዊ ጉባኤያት፣ በዕለተ ሰንበት በመገኘት “ክርስቲያን ነኝ” ለማለት በማልደፍርበት አካሔድ እመጣለሁ (እመላለሳለሁ)። በወጣትነት የዕድሜ ክልል ላይ እገኛለሁ። በእግዚብሔር ቤት መኖር የምመኝ የመንግሥት መስሪያ ቤት ሠራተኛ ነኝ፤ እናም ለማግባት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ። ብዙ ወንዶች ለጋብቻ ይጠይቁኛል። ለብዙዎቹ ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› ብዬ እንዲጸልዩ እንዲተጉ ምክር እሰጣቸዋለሁ። አንድ ቀን ወደ መሥሪያ ቤት ስሔድ ታክሲ ውስጥ ከአንድ ወንድም ጋር ተዋወቅንና ስልክ ተለዋወጥን ከዚህ በኋላ እየተቀራረብን መጣን። ወደ ሥራ ቦታ ስንሄድም ሆነ ስንመለስ እየተጠባበቅን መሄድ ጀመርን በዚህ መሀል አንድ ቀን ወደ ሥራ እየሄድን ሳለ ስለትዳር ጉዳይ ተነስቶ እንድንጋባ ጠየቀኝ።  ጥያቄውን ከመመለሴ በፊት እርሱ በጋብቻ ላይ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ ጠየቅሁት  እርሱም ከጋብቻ በፊት ግንኙነት መፈጸም መልካም እንደሆነና ለጋብቻም ጥሩ መተዋወቅን እንደሚፈጥር፤ በአንጻሩ በምዕራባውያን ፺ ከመቶ  በላይ የሚሆኑት ሰዎች ጋብቻቸውን የሚያፈርሱት በግብረ ሥጋ ግንኙነት አለመጣጣም የተነሳ እንደሆነ አክሎ ነገረኝ። እኔም እግዚአብሔር ባቀበለኝ መንገድ ‹‹ምዕራባውያኑ በቅድመ ጋብቻ ውስጥ በመኖራቸው ለምን ፍቺን መቀነስ ብሎም ማጥፋት አልቻሉም? እኔ ቅድመ ጋብቻን ዝሙት እንደሆነ ነው የማስበው›› ብዬ በጊዜው መለስ  ሰጠሁት። ለመሆኑ ይህንን ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያን አስተምሮ አንጻር ምን ትሉኛላችሁ? 

ወለተ ማርያም 

Read more: ከጋብቻ በፊት የሚኖር ግንኙነት ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር እንዴት ይታያል?

የማንቂያ ደወል የሆነው የኮሚሽኑ ሪፖርት

Details
Written by: ዲ/ን አሻግሬ አምጤ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 11 January 2021
Hits: 1084
  • ሪፖርታዥ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ባለ ፷፬ ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ከኮሚሽኑ ሪፖርት መረዳት የሚቻለው የተፈጸመው ጥቃት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ነው። ሕይወታቸውን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጥበቃ ቢተርፉ እንኳ የሚበሉት እንዳይኖራቸው ንብረታቸውን መዝረፍ፣ ማቃጠል፣ አፈናቅሎ በማሳደድ በችግር ሲሠቃዩ እንዲኖሩ ማድረግ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የኮሚሽኑ ሪፖርት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስታሳስበው የከረመችውን የሚያጠናክር በአንጻሩ መንግሥት ጥቃቱ አጋጣሚ የፈጠረው እንጂ በተጠና መልኩ የተፈጸመ አይደለም በማለት ሲያስተባብል የከረመውን የሚያጋልጥ ሪፖርት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የወጣ ጠንከር ያለ ሪፖርት መሆኑን አንብቦ መረዳት ይቻላል።

እንዲህ ዓይነት ሪፖርቶች እውነት ተዳፍና የምትቀር እነርሱም ከተጠያቂነት እንድናለን እየመሰላቸው በወንጀል ላይ ወልጀል፣ በኃጢአት ላይ ኃጢአት የሚደርቡ ወገኖች ሊደርስባቸው የሚችለውን አደጋ አስበው እጃቸውን ከጥፋት እንዲሰበስቡ ያደርጋል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት ወር ፳፻፲፫ ዓ.ም “የመንግሥት የበታች ባለሥልጣናት ለጥፋተኞች ከሚያደርጉት ከለላ እጃቸውን እንዲሰበስቡ”ያሳሰበችው በመዋቅር ክርስቲያኖች ሲገደሉ፣ ሲሳደዱ፣ ሀብት ንብረታቸው እየተዘረፈ ቀሪው ሲቃጠል ብዙዎቹ የክልሉ መንግሥት የጸጥታ አካላት ቆመው ያዩ ስለነበር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንዳይገባ ከመከልከል ጀምሮ የተሳሳተ መረጃ ይሰጡ እንደነበር የሚያሳየው ኮሚሽኑ መረጃ  ባንክ ለመጠበቅ ብቻ ለግዳጅ እንዲሰማሩ መደረጉ መንግሥት የራሱን መቅር መመርመር ያለበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።

Read more: የማንቂያ ደወል የሆነው የኮሚሽኑ ሪፖርት

Page 11 of 19

  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት