- Details
- Written by: በጋዜጠኛ ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 970
በሩሲያ መንግሥት ድጋፍ በሶሪያ መለስተኛ የሆነ አዲስ የሐግያ ሶፊያ ቤተመቅደስ ሊገነባ እንደሆነ ኦርቶዶከስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል፡፡
ቤተመቅደሱ የሚገነባው በርካታ የግሪክ ኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ክርስቲያን በሚኖሩባት አል ሱቋአያላቢያህ ሲሆን ግንባታውም በቅርቡ ተጀምሮ በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ዘገባው አመልክቷል፡፡
በቱርክ የሚገኝው ጥንታዊውና ታሪካዊው የሐግያ ሶፊያ ቤተመቅደስ ከርጅም ጊዜ በኋላ በቱርክ መንግሥት እምቢተኝነት የቤተመቅደሱ ይዘት በተወሰነ ደርጃ ተለውጦ በይፋ ወደ መስጅድነት ተቀይሮ ለሕዝበ ሙስሊሙ ማምለኪያነት እንደዋለም ዘገባው አስታውሷል፡፡
- Details
- Written by: እንድርያስ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 2218
ልጆች እንደምን ከረማችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን፤ ደኅና፡፡ ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ከዐሥርቱ ትእዛዛት መካከል አንዱ ስለሆነው ትእዛዝ እናትና አባትን ስለማክበር ነው፡፡ ልጆች! እናትና አባትን ማክበር ማለት የወለዱንን ወላጆቻችንን በሚገባ መታዛዝ ነው፡፡ ይህንንም ማድረግ ያለብን ለወላጆቻችን ብቻ ሳይሆን በሥጋ ባይወልዱንም በዕድሜያቸውና በዕውቀታቸው እኛን በጎ ምክር የሚመክሩን ሁሉ እናትና አባቶቻችን በመሆናቸው ለአዛውንቶችም ጭምር ነው፡፡
- Details
- Written by: ካሳሁን ለምለሙ
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1369
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት የአንድ ሀገር መንግሥት ሕዝቡ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በሚገባበት ወቅት ዜጎች ማድረግና መደረግ የሌለባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የሚያስቀምጥ ሲሆን ዜጎች ማድረግ እያለባቸው ሳያደርጉ ሲቀሩ ወይም ማድረግ የሌለባቸውን ሲያደርጉ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የአንድ ሀገር መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሊጥል የሚችለው ተፈጥሮአዊ አደጋ ሲከሰት፣ የእርስ በእርስ ግጭት ሲፈጠር፣ ረኀብና ድርቅ ሲከሰት እንዲሁም የማኅበረሰቡን ጤና የሚጎዳ ወረርሽ ሲከሰት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ መንግሥታት እንደተፈጠረው ሁኔታ ዜጎቻቸው እንዲጠነቀቁና የሕይወት ዘይቤአቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ አስቸኳይ የሆነ አዋጅን ያውጃሉ፡፡ በዘመናችን አንዳንድ ሀገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተመሳሳይ መልኩ በዜጎቻቸው ላይ ገደብ ወይም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲጥሉ ተስተውሏል፡፡ እነዚህ ሀገራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከጣሉበት ምክንያት ከላይ ከተዘረዘሩት ችግሮች መካከል አንዱ በመከሰቱ ነው፡፡ ይኽውም የሰውን ልጅ ጤና የሚያውክ እና ለሞት የሚዳርግ ኮሮና ቫይረስ (COVID -19) የተባለ ወረርሸኝ በመከሰቱ ነው፡፡ ታድያ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ የዓለማችን ሀገራት በዜጎቻቸው ላይ የተለያየ ገደብ በተለያየ ጊዜ ጥለዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስ (COVID -19) የዓለምን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ያናጋ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም የዚህ ገፈት ቀማሽ በመሆኗ እንደሌሎች የዓለም ሀገራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀች እነሆ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተጣለ ጊዜ ጀምሮ ታዲያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል፡፡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሌሎች እምነት ተቋማት በተለየ መልኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እጅግ ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን ፈጥሯል፡፡ አገልጋይ አባቶችን ለኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያንም ከምእመናን ታገኝ የነበረውን የገንዘብና የቁስ ድጋፍ አስቀርቶባታል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች በተጨማሪ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቤተክርስቲያን በፀጥታ ችግር እንድትቸገርና የተደራጁ አክራሪ ቡድኖችንና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሽፋን ያደረጉ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ምእመናንን ያለአግባብ እንዲደበድቡና በእስር እንዲያንገላቱ በር ከፍቶላቸዋል፡፡ መንግሥትና ሕዝብ ባለበት ሀገር ላይ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ለሚከተሉት ሃይማኖት ወግነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደሽፋን ተጠቅመው ምእመናንን ይደበድባሉ፣ ያስራሉ አለፍ ሲልም በኢኮኖሚ ለማዳከም የብር መቀጮ ይጠይቃሉ፡፡
- Details
- Written by: ረቂቅ መቻል
- Category: ስምዓ ጽድቅ
- Hits: 1336
የተከበራችሁ አንባብያን መቼም በዕለት ዕለት እንቅስቃሴያችን ልብ ብለን ካስተዋልን የሚደንቁ እና የሚያስገርሙ የሚያስደስቱና የሚያዝናኑ የሚያበሳጩ ነገሮችን በአግራሞት ተመልክተን ወይም ሰምተን ማለፋችን አይቀሬ ነው፡፡ አንዳንዴም አስተማሪ የሆኑ ትርኢቶችን ልናይ እንችላለን፡፡ እኔም በአንዲት ዕለት ካስተዋልኳቸው ትዝብቶቼ መካከል ለእናንተ ለማካፈል ወደድሁ፡፡
ወሩ ሰኔ ዕለቱ ዐርብ ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓቱ ደግሞ በግምት ከዐሥራ ሁለት ተኩል እስከ አንድ ሰዓት ባለው አካባቢ ይሆናል፡፡ ቦታው ስድስት ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ዕለት ዐይኖቼ ያዩትን በጆሮዬ የሰማሁትን እና በልቤ ያወጣሁ ያወረድሁትን እንዲሁም የተሰማኝን በትዝብት ቅኝቴ ውስጥ ላሳያችሁ ስወድ ከመንፈሳዊ ቅንዓት ተነሥቼ ነው ፡፡ ለትዝብት ቅኝቴ አትኩሮት እንድሰጥ ምክንያት የሆነኝ በክርስቲያን ወገኖቼ ዘንድ የዕለቱ በዓል ታላቅነት ሰፊ ስፍራ የሚሰጠው በመሆኑ ተከብሮ የሚውለውን የበዓሉን ምንነት በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል እግረ መንገዴን ታሪኩን እያወሳሁ የትዝብት ቅኝቴን ልገልጽላችሁ እወድዳለሁ፡፡ወቅቱ ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ኮቪድ ፲፱ ወረርሽኝን አስመልክቶ በሚወጡ የመንግሥት አዋጆች እና አተገባበራቸውን ስታዘብ በአብያተ ክርስቲያኖች ላይ አብዝቶ የሚደርሰው አሉታዊ ጫናና ግፍ ከዕለት ዕለት የሚያሳዝንና የሚያበሳጭ ሆኖ ስላየሁት ነው፡፡
በዚህ ቀን ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ ማልዶ በመነሣት ወደ ቅዱስ ሚካኤል ወዳለበት ቤተ ክርስቲያን ይተማል፡፡ ከባድ የሚባል ችግር ካልገጠመው በቀር ሁሉም በሚባል ደረጃ ደጁን ሳይረግጥ ቤተ ክርስቲያንን ሰላም ለኪ ብሎ በሮቿን ስሞ ቅዱስ ሚካኤልን አማልደኝ ርዳኝ ረድኤትህ በረከትህ ይደርብኝ ሳይል የሚውልና ወደ ተሰማራበት የዕለት ሥራ የማይሄድ ክርስቲያን የለም ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ዐይኖቼ ለሕዝብ ደኅንነት የተመደቡትን የፖሊስ አካላት ብቻ ሳይሆን በበጎ ምግባር ተሰማርተው ቤተክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያኑን በቅንነትና በማስተዋል ሲያገለግሉ የነበሩትን ወጣቶች በማየት ማድነቅ ጀመርኩ፡፡