ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ስምዓ ጽድቅ

‹‹አንገቱ ላይ ማዕተብ ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም››

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1161
  • ሪፖርታዥ

ክፍል አንድ

ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ዘመን ጀምሮ በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች፤ወንጌልን ለዓለም ለማዳረስ  ብዙ ዋጋ ከፍላለች፡፡ በየዘመናቱ ለቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆነው በተነሱ ከግለሰብ እስከ ገሥታት ድረስ ላደረሱበቸው መከራና ስቃይ አገልጋዮቹ ገፈት ቀማሽ ሆነው ኖረዋል። ቤተ ክርስቲያን፣  ንዋያት ቅዱሳት ሳይቀሩ ተቃጥለው ሲወድሙ ኖረዋል። ዛሬም በአምልኮቷ፣ በእምነቷ፣ በስርዓቷ እየመጡ ተከታዮቿንና እሷን ሲጎዱ ኖረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሀገርን ባቆመች፣ ዳር ድንበርን ባስከበረች፤ በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ቅርሶቿ ሀገርን በዓለም አደባባይ ባስወቀች ውለታዋን መመለስ ሲገባ ሆን ተብሎ በችግር ውስጥ እንድታልፍ ሲደረግ ኖሯል። ለበርካታ ዘመናት ቤተክርስቲያንና ምእመናንዋ ተመርጠው የጥቃት ዒላማ ሲሆኑ ኖረዋል፡፡  አግዚአብሔር እንዳይመለክ፣ ምዕመናን ወደቤተ ክርስቲያን እንዳይሄዱ የተደረጉባቸው ሁነቶች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ናቸው፡፡ አሁን አሁን እየገዘፈ እና እየበረታ የመጣው ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የአንድ ሃይማኖት የበላይነትን ለማስፋፋት የሚመኙት የተስፈኞች ሴራ ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን ለምን በየጊዜው የጥቃት ኢላማ ይሆናሉ ለሚለው በቂ መልስ ነው፡፡

እነዚህ ተስፈኞች ሳር ቅጠሉ ሁሉ የእነርሱን ሃይማኖት ብቻ እንዲከተል የሚመኙ፤ ከፍ  ሲልም ከእነርሱ ሃይማኖት ውጪ የሆነ የሰውን ልጅ  ሁሉ ማረድ፣ ሀብት ንብረቱን መዝረፍ፣ ማቃጠል እንዲሁም እንዲሰደድ በማድረግ ቀን ከለሊት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይ የኦርቶዶክሳውያንን ደም ካላፈሰሱ የሚረኩ አይደሉም፡፡ ተስፍኛውና አክራሪው ቡድን  ኦርቶዶክሳውያንን በጭካኔ ለመግደልና ሀብት ንብረታቸውን ለማውደም በአብዛኛው በሀገር ውስጥ የሚፈጠር ሁከትና ግርግርን ይመርጣል፡፡ በዚህ ወቅት የኦርቶዶክሳውያንን የአንገት ማዕተብ አስገድዶ ይበጥሳል፤ አስገድዶም ልብን ሳይሆን አካልን ያሰልማል፡፡ የዚህ አክራሪ ጽንፈኛ ኃይል የሃይማኖቴ ትርጓሜ “ሰላም” ነው ይበል እንጂ ከቃል ያልዘለለውን ፕሮፖጋንዳ ሽፋን አድርጎ የብዙ ንጹሓን ኦርቶዶክሳውያንን ሰላም ያናጋል፡፡ የያዝነውን ዓመት ጨምሮ ያለፉት ሁለት ተከታተይ ዓመታት ለዚህ ጽንፈኛ አክራሪ ቡድን የሽብር ወንጀሉን  ለመፈጸም ምቹ የመጫወቻ ሜዳ ሆነውለታል፡፡

Read more: ‹‹አንገቱ ላይ ማዕተብ ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም››

ዓይን የላቸውም ዓይን ያለንን ግን ይመሩናል፣እጅ የላቸውም ያሰሩናል . . .

Details
Written by: ከቆየ እትም የተወሰደ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1096
  • ቤተ አብርሃም

ክፍል አንድ

በዚህ ዓምድ በሕይወታቸው፣ በአገልግሎታቸው፣ በዕውቀታቸውና በሙያቸ ሊያስተምሩ የሚችሉ እንግዶች እንዲሁም ስለ ቤተክርስቲያን ተቋማትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ነው፡፡  እንደ ጥንቱ የአብርሃም ቤት እንግዶች የሚስተናገዱበት በመሆኑም ይህን ስያሜውን አግኝቷል፡፡

እስከ ፲፱፻፶፰ ዓ.ም ድረስ በላስታ አውራጃ በዋልድቢት ማርያም ገዳም ይኖሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ የጀመራቸው የሥጋ ደዌ በሽታ ስለተባባሰባቸው ለሕክምና ወደ ደሴ ከተማ መጥተው ከ፲፱፻፶፰-፲፱፻፷፫ ዓ.ም ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆዩ፡፡ ይህ ሕመም ሳይሻላቸውም ዓይናቸው ታመመ፡፡ ከዚያም ለከፍተኛ ሕክምና ወደሻሸመኔ ኩየራ ሔዱ፡፡ ሻሸመኔ ሲደርሱ ግን ሐኪሙ ወደሌላ ቦታ በመሔዳቸው ሳይታከሙ ቀሩ፡፡  

ከሻሸመኔ ወደ አገራቸው ለመመለስ የነበራቸው ገንዘብ በቂ አልነበረምና ሌላ መፍትሔ ያፈላልጉ ጀመር፡፡ የታመመ ሐኪም መፈለጉን አይተውምና በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም ‹‹ሐኪም አለ›› መባልን ሰምተው ወደ አዋሳ ሄዱ፡፡ ከአዋሳ ይርጋዓለም እየተመላለሱ ይታከሙ ጀመር፡፡ መኖሪያቸውም በዚያው ሆነ፡፡ በመጨረሻም ሕመሙ በከፍተኛ ሁኔታ በመባባሱ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም አዲስ አበባ አለርት ሆስፒታል ሁለት እግሮቻቸው ተቆረጡ፡፡ የዚህ ታሪክ ባለቤት አባ ዜና ገብርኤል ይባላሉ፡፡ 

Read more: ዓይን የላቸውም ዓይን ያለንን ግን ይመሩናል፣እጅ የላቸውም ያሰሩናል . . .

 “የተደራጀ አክራሪ ኃይል ቤተክርስቲያንን እያጠቃት እንደሆነ በተደጋጋሚ ለመንግሥት አሳውቀናል”

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1167
  • ፍሬ ከናፍር
 “የተደራጀ አክራሪ ኃይል ቤተክርስቲያንን እያጠቃት እንደሆነ በተደጋጋሚ ለመንግሥት አሳውቀናል”

ክፍል አንድ 

 

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ምዕመናን ላይ እየደረሰ  ያለው ግድያ እና ጥፋት እየተበራከተ መጥቶአል። በዚህ ዓመት ብቻ እንኳ በሻሸመኔ፣ በባሌ ፣ በአርሲ በጅማ እና  በሀረር እንዲሁም በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች  በተደራጁ ፅንፈኛ ኃይሎች ቤተክርስቲያን ላይ  የደረሰው ጉዳት ቀላል አይደለም ፡፡ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣  የቤተ ክርስቲያኒቷ ተከታይ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ታርደዋል ፣ እጅና እግራቸው እየተቆረጠ በክርስቲያን ወግ የቀብር ስርዓት እንኳ ሳያገኙ በየሜዳው እና በየጫካው ተጥለዋል። ከዚህ አሰቃቂ እልቂት የተረፉት ከተወለዱበት ፣ ከኖሩበት እና  ሀብት ንብረት ካፈሩበት ቀዬ ተፈናቅለው በየአብያተ ክርስቲያናቱ ተጠልለው ይገኛሉ። በአንድ ወቅት ራሳቸውን እና ብዙዎችን የሚረዱ ሰዎች ተረጂ  እጃቸውን ለሌሎች የሚዘረጉ የምዕመናን እጆች ከሌሎች  ምጽዋትን ለመቀበል ተገደዋል። 

ሰኔ 2012 ዓም. በአርቲስ ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ውስጥ በተነሳው አመፅ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ተከታዮቿ ናቸው። የአርቲስቱን ሞት ሽፋን በማድረግ በተጠና እና በተደራጀ መልኩ ፅንፈኛ የሆኑ አክራሪ ሙስሊሞች ያደረሱትን እና እያደረሱ ያሉትን እጅግ ዘግናኝ ውድመት አስመልክቶ  በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ እንዲሰጡን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ሰብሳቢ እና የኮቪድ-19 ተስፋ ልዑክ ግብረ ኃይል ፀሐፊ ከሆኑት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ጋር እንደሚከተለው ቆይታ አድርገናል።

ስምዐ ጽድቅ፡- የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ሞት ሽፋን በማድረግ በተለያዩ የኦሮሚያና በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች በምእመናንና በንብረታቸው ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት ደርሷል፡፡ ምክንያቱ ምንድነው?

Read more: “የተደራጀ አክራሪ ኃይል ቤተክርስቲያንን እያጠቃት እንደሆነ በተደጋጋሚ ለመንግሥት አሳውቀናል”

፲፪ ፲፪ ፲፪ አስፈሪው የጥፋት ኮድ

Details
Written by: ረቂቅ መቻል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1406
  • ትዝብት

ወሩ እንዴት ነበር? መቼም ከባለፈው  ወር ጋር እንደምታነጻጽሩት እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ፡፡ በቁስል ላይ ቁስል ሲጨመር ምን ያህል  እንደሚያም መገመት አያዳግትም? በዚህ ዓመት ሀገሬና  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሆነባቸውን ሁልጊዜ እየታዘብኩት ነው የማልፈው፡፡ 

ያሳለፍናቸው  ዓመታትና ወራት፣ አሁን ያለንበት የክረምት ወር በተፈጥሮ ዑደቱ ጥሩ መጥፎም አልነበረም፡፡ ተፈጥሮ የራሷን ሥራ በአግባቡ ታከናውናለች፡፡ የክረምቱ ዝናብ ይዘንባል ፣ ፀሐይና ጨረቃም እንደ ወትሮቸው  ባይሆኑም በተሰጣቸው የተፈጥሮ ሚዛን ላይ ሆነው  ብቅ ጥልቅ ማለታቸውን ቀጥለዋል ፡፡ እኔም ወደ ውጪ የሚላክ ዕቃ ለማድረስ ከቤቴ ወጥቻለሁ:: መንገዱ በተለየ ሁኔታ ፀጥ ረጭ ብሏል፤ አዲስ አበባን ወትሮ ለሚያውቃት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ አትመስልም፡፡ ደግሞ ዛሬ ምን ተከሥቶ ይሆን? ብዬ የተሳፈርኩበትን  የታክሲ  ሾፌር ፈራ ተባ እያልኩ ጠየኩት፡፡ አልሰማሽም እንዴ? ሲል በመኪናው የኋላ በስፖኪዮ  እያየኝ  ማውራት ጀመረ፡፡ 

ወይ ሀገሬ  ደግሞ ምን ሆነሽ  አደርሽ?  ባለፈው ሰኔ ፳፫ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ጽፈኞች ከተማችንን ሲያተራምሱ አደሩ ዛሬ ደግሞ ማን ሞተ  አልኩት? ማን ይሞታል ብለሽ ነው አክቲቪስት ጁዋር መሐመድ ትናንት ፍርድ ቤት  ቀጠሮ ነበረው እናም ዳኛውን  አሞኛልና  እባክህን በነፃ ልቀቀኝ ብሎ በለቅሶ ሲማጸን መዋሉን የሰሙ ተከታዮቹ እንደለመዱት  ሀገር ለማተራመስ ሰው ለማረድ፣ ንብረት ለማውደም የጥፋት አዋጁን ማስፈጸሚያ ያዘጋጀውን ቅጥር ፲፪/፲፪/፲፪ ብሎ በመሰየም የሰው ማረጃና ንብረት ማውደሚያ ኮድ  ያሴሩት ሴራ በፖሊስና በመከላከያ  ኃይል ከሽፎ አደረ:: በርግጥ በአንዳንድ የሀገራችን ከተሞች  ንቅናቄው ተካሄዷል፡፡ በተለይም በአወዳይ፣ ሻሸመኔ ፣ጊነር፣ አዳማና ባሌ መስመር  እያለ ተረከልኝ፡፡ 

Read more: ፲፪ ፲፪ ፲፪ አስፈሪው የጥፋት ኮድ

ልጅ መውለድ ባለመቻላችን  የትዳር ሕይወታችን እየተፈተነ ነው

Details
Written by: ረቂቅ መቻል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1330
  • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ

ክፍል አንድ

የተወደዳችሁ የስምዐ ጽድቅ ዝግጅት ክፍል እንደምን አላችሁ  በክርስትና ስሜ ዐምደ ሚካኤል እባላለሁ ዕድሜዬ ሠላሳዎቹ አጋማሽ ውስጥ ነው፡፡ የምኖረውም እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ላለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የሚወጡ መካሪና አስተማሪ ዐምዶችን እከታተላለሁ፡፡ ምሥጢሬን ላካፍላችሁ በሚባለው  የዝግጅት ዐምድ ላይ የሚወጡ ምሥጢራዊ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ደግሞ አስተማሪና መካሪ በመሆናቸው እንደሌሎች ሰዎች ብዙ የታፈኑ ምስጢሮቼን በሆዴ ብቻ እያብሰለሰልኩ ከምቀመጥ ከእናንተ መፍትሔ አገኝበታለሁ ብዬ ስለተማመንኩ  ምሥጢሬን አካፍላችሁ ዘንድ እንዲህ ጻፍኩላችሁ ፡፡

የእኔ ታሪክና ዛሬ ድረስ ውስጤን  ሲያብሰለስለኝ የኖረው የትዳር ሕይወት ችግሬ ሲሆን ይህንንም ወደ ፊትም እንዴት አድርጌ እንደማስወግደው የሚያስጨንቀኝ ጉዳይ  ሆኗል፡፡ እኔን የገጠመኝ የትዳር ቀውስ ከባድ ነው ፡፡ የማይቻል የማይታለፍ ነገር የለም ልትሉኝ ትችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እኔ ውስጥ የሚቻል የሚመስል ግን የማይቻል ነው፡፡ የትዳር መሠረታዊ ጣዕም የሚሰጠው ጉዳይ ግን ባዶ ነበር፡፡ ባለቤቴ የሩካቤ ስጋ ችግር አለባት በዚህ ምክንያት ይሁን በሌላ ልጅ እንድንወልድ እፈልግ ነበር አልቻልንም፡፡ በዚህ ላይ  ባለቤቴ አብዝታ የምትጨነቀው ስለምንበላው፣ ስለምንጠጣው፣ ስለምናሽከረክረው መኪናና ስለምንኖርበት ዘመናዊ ቤት ብቻ ነው፡፡  ለእኔ ግን የተሟላ ሕይወት አለኝ ለማለት አልደፍርም፡፡ ዘወትር የሚያስጨንቀኝን ጉዳይ ለቤተሰቦቼና ለባልንጀሮቼ ላማክር እፈልግና ሰዎችን ምን ይሉኛል የሚለው የባህላችን ተጽዕኖዎች አንቀው ይይዙኛል ፡፡ 

በተለይ እኔ   ያደግኩት ማኅበረሰብ  ደፍሮ መናገር ነውር የሆነበት በመሆኑ ችግሬን ደፍሬ ልናገር አልወደድኩም፡፡ እየዋለ እያደረ የቤታችን ሰላም እየተናጋ መጣ ፡፡ በቅርብ ሰዎች ዳኝነት ስንዳኝ ነገሩ እየባሰ መጣ ሥጋችን ብቻ ሳትሆን መንፈሳችንም ተፈተነች፡፡ 

Read more: ልጅ መውለድ ባለመቻላችን የትዳር ሕይወታችን እየተፈተነ ነው

መንግሥት ለምእመናን አፋጣኝ የደኅንነትና የኑሮ ዋስትና እንዲሰጥ ቤተክርስቲያን አሳሰበች

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1374
  • አጫጭር ዜናዎች
መንግሥት ለምእመናን አፋጣኝ የደኅንነትና የኑሮ ዋስትና እንዲሰጥ ቤተክርስቲያን አሳሰበች

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ሞት ሽፋን በማድርግ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ከተፈጸመባቸው ምእመናን የቀሩትን  መንግሥት አፋጣኝ የደኅንነትና የኑሮ ዋስትና ሊሰጣቸው እንደሚገባ  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ/ም ባወጣችው መግለጫ አሳሰበች፡፡ 

ተጎጂዎች በእምነታቸው ምክንያት ከደረሰባቸው የተቀናበረ ስልታዊ ጥቃት በኋላ የደኅንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ ቤተክርስቲያን ያረጋገጠች ሲሆን ምእመናኑ በአሁኑ ሰዓት ያሉበት ሁኔታም ለኮሮና ቫይረስ እና ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በሚያጋልጣቸው ሁኔታ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በመሆኑም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የፌደራል መንግሥት የኦርቶዶክሳውያንን በሕይወት የመኖር፤ ሀብትና ንብረት የማፍራት ፤ ሰብአዊ እና ዜጋዊ መብታቸውን እንዲሁም የደኅንነት እና የመኖር ዋስትናቸው በአፋጣኝ እንዲከበርላቸው ቤተክርስቲያን በመግለጫዋ ጠይቃለች፡፡

መንግሥት ጥቃቱን ያቀዱትን፤ የፈጸሙትንና ያስተባበሩትን ኃይሎች እንዲሁም የተጣለባቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት ወደጎን ትተው የተፈጸመውን ጥቃት በዝምታ የተመለከቱ በመንግሥት በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሹማምንቶችንና የፀጥታ አካላትን በሙሉ በቁጥጥር ሥር በማዋል እና በሕግ ተጠያቂ በማድረግ እስከመጨረሻው ድረስ በአካባቢው ፍትሕ እንዲሰፍን የማድረግ ተግባር  እንደሚጠበቅበትም አስገንዝባለች፡፡ 

በአሳዛኝ ሁኔታ በደልና ግፍ የተፈጸመባቸው ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሆነው እያለ፤ ነገር ግን በጥቃቱ ምንም ሱታፌ ሳይኖራቸው  የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በመሆናቸው ብቻ በእስር  እየተንገላቱ የሚገኙ ንጹሓን ምእመናን ጉዳያቸው በጥንቃቄ ታይቶ ከእስር እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ መንግሥትን አሳስባለች፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖለቲካ ፓርቲዎችም በግፍ በተገደሉ ምእመናን ላይ ከመሳለቅ እንዲቆጠቡና መንግሥትም ክትትል አድርጎ በእነዚህ አካላት ላይ አስፈላጊውን ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ ቤተ ክርስቲያን አጥብቃ ጠይቃለች፡፡ 

 

መንግሥት በዚህ ዓመት በጥቅምት፣ በጥር እንዲሁም በሰኔ ወራት በምእመናን ላይ ከተፈጸመ ግድያ፣ ዘረፋ እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ  ከደረሱ ጥቃቶች ጀርባ  ያሉትን አጥፊዎች አጣርቶ  ለፍርድ እንዲያቀርብ እና ውጤቱንም በይፋ ለሕዝብ እንዲገልጽ በመግለጫው አጽንኦት ሰጥታ አሳስባለች፡፡  

 

በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ጨምሯል ተባለ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1248
  • አጫጭር ዜናዎች
በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ጨምሯል ተባለ

ዓለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ወቅት በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃትና መገለል እየጨመረ መሆኑን ኦርቶዶክስ ታይመስ ዘግቧል፡፡ በተለይም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኘ በዓለም መከሠቱ ክርስቲያኖችን ለአካላዊና ሥነልቦናዊ ጥቃት እንዳጋለጣቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡ 

በታዳጊ ሀገራት የሚኖሩ ክርስቲያኖች በተለይም ምግብና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ቁሳቁስ እየተከለከሉ እንደሆነ የዩሲኤን ዘገባን ዋቢ አድርጎ ኦርቶዶክስ ታይምስ ዘግቧል፡፡  በተለይም በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች መጠለያና የተባበሩት መንግሥታትን ድጋፍ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት በአክራሪ ሃይማኖተኞች የሰፋ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ሲል ዘገባው አመላክቷል፡፡ 

የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ለፓኪስታንና ለግብጽ ክርስቲያኖች ሕይወት እንደከበደባቸው ያነሣው የኦርቶዶክስ ታይምስ ዘገባ በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች በከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ ብሏል፡፡ ክርስቲያኖቹ የዕለት ምግባቸውን ከማጣታቸው ባሻገር ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመጠበቅ የሚያግዟቸውን የፊት መሸፈኛ ጭንብልና የእጅ ንጽሕና መጠበቂያ ኬሚካል ጭምር በገንዘብ እጥረት ምክንያት እንዳላገኙ በዘገባው ተመልክቷል፡፡ 

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሠተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በክርስቲያኖች ላይ ለሚፈጸመው መገለልና ጥቃት አባባሽ እንደሆነ ከዘገባው የተገኘው መረጃ አመላካች ሲሆን በአንዳንድ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች እንደሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ እንደሆነም ታውቋል፡፡ የጥቃቱ ሰላባ እየሆኑ ያሉት ክርስቲያኖች ደግሞ ከእስልምና፤ ከሂንዱና ከቡዲሂስት እምነቶች የተመለሱ ናቸው ተብሏል፡፡ 

ክርስቲያኖች ከመንግሥታቸው ከሚያገኙት ሁለንተናዊ አገልግሎት በሃይማኖታቸው ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተገለሉ እንደሆነና እንደሁለተኛ ዜጋም እየተቆጠሩ እንደሆነ ያነሣው የኦርቶዶክስ ታይምስ ዘገባ የባንግላዲሽ፤ የማሌዥያ፤ የህንድ፣ የፍሊፕንስ፣ የናይጄሪያ እና የዓረቡ ዓለም ክርስቲያኖች ስለሚደርስባቸው መገለልና አካላዊ ጥቃት እንዲሁም ኢፍትሐዊ አያያዝ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አቤቱታ እንዳቀረቡ ከኦርቶዶክስ ታይምስ ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡    

 

ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ (ዘሌዋውያን. ፲፱፥ ፲፰)

Details
Written by: እንድርያስ ስንታየሁ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 1418
  • የሕፃናት ዓምድ

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? እግዚአብሔር ይመስገን አላችሁ? መልካም፤ እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን፡፡

ልጆች የእግዚአብሔር ቃል ነውና ሰው ራሱን እንደሚወድ ባልንጀራውን መውደድ እንዳለበት ዛሬ እንማራለን፡፡ ከዐሥርቱ ትእዛዛት ውስጥም ዐሥረኛው ባልንጀራህን ወይንም ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ ይላልና ነው፡፡ (ዘሌዋውያን. ፲፱፥ ፲፰)

ልጆች! እናንተ ወላጆቻችሁን ‹አባዬ እወድሃለሁ፤ እማዬ እወድሻለሁ› ትላላችሁ አይደል?  ሁሉም እናቱንና አባቱን ስለሚወድ ነው፡፡ ታዲያ የምንወዳቸው በአንደበታችን በመናገር ብቻ  መሆን የለበትም፡፡  መውደድ በተግባር መገለጽ አለበት፤ ይህም ማለት እነርሱ ሲያሳድጉን ትምህርት እያስተማሩ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ አሟልተው ነው፤ ማለትም ልብስ፣ ጫማ፣ ቦርሳ፣ ደብተር፣ እስክርቢቶ እና መጫወቻ ገዝተው በእንክብካቤ ያሳድጉናል፡፡  የእነርሱ መውደድ በተግባር ተገለጸ ማለት እንደዚህ ነው፡፡

እናንተ ደግሞ ባልንጀራችሁን በመውደድ ጥሩ ነገር ማድረግ አለባችሁ፡፡ ልጆች ባልንጀሮቻችሁ የወላጆጃችሁ ጓደኞች ልጆቻቸው፣ በትምህርት ቤት እና ከጎረቤት የምትተዋወቋቸው ሕፃናት ማለት ናቸው፡፡ እነርሱም የዕድሜ እኩዮቻችሁ በመሆናቸው አብረዋችሁ ይማራሉ፣ ያጠናሉ እንዲሁም ይጫወታሉ፡፡ በመሆኑም ልክ እንደራሳችሁ ልትወዷቸው ይገባል፡፡ ለእናንተ የተደረገላችሁ ነገር ለእነርሱም እንዲረግላቸው ማሰብ ይጠበቅባችኋል ማለት ነው፡፡ 

Read more: ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ (ዘሌዋውያን. ፲፱፥ ፲፰)

በሩሲያ ምሥጢራዊ መረጃ  በሚያወጡ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ ቅጣት ሊጣልባቸው ነው

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 04 September 2020
Hits: 720
  • አጫጭር ዜናዎች
በሩሲያ ምሥጢራዊ መረጃ  በሚያወጡ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ ቅጣት ሊጣልባቸው ነው

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቷን ምሥጢራዊ መረጃ አውጥተው ለሚዲያ ፍጆታ በሚያውሉ መነኰሳትና ቀሳውስት ላይ ጠንካራ ርምጃ እንደሚወስድ ኦርቶዶክስ ታይምስ ዘገበ፡፡ 

የቤተ ክርስቲያኒቷን ምሥጢራዊ መረጃ በሚያወጡ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ የማያዳግም የርምት ርምጃ እንደሚወስድ የጠቆመው ዘገባው ይህ የሆነበት ምክንያት ውስጣዊ የቤተክርስያኒቷ ምሥጥራዊ  መረጃ ለሦስተኛ ወገን ተጋላጭ እንዳይሆኑና አግባብ ላልሆነ የሚዲያ ፍጆታ እንዳይውሉ  ለመከላከል ነው ተብሏል፡፡ 

ድርጊቱን ፈጽመው በተገኙ ቀሳውስትና መነኰሳት ላይ ለአንድ ወይም ለሦስት ዓመታት ያህል ከሃይማኖታዊ አገልግሎት እንዲሚገለሉ ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመሆኑም መነኰሳቱም ሆኑ ቀሳውስቱ መረጃዎችን ይፋ ሊያደርጉ የሚችሉት ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከሊቃነ ጳጳሳት ፍቃድ ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ተመላክቷል፡፡ 

የየትኞቹን መረጃዎች ምሥጢራዊነት መጠበቅ እንደሚገባ ግራ የተጋቡት አንዳንድ የቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስቱና መነኰሳቱ የቀሳውስትን የግል ጉዳይ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷን የተመለከቱ ከፍተኛ የወንጀል ድርጊቶችን ምሥጢራዊነት መጠበቁ ያላስደሰታቸው  ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወሰነው ውሳኔ እንዴት ሥራ ላይ እንደሚውል፤ ጥቅሙንና ዓላማውን ጭምር ለመረዳት እንደሚፈልጉ ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡ 

 

አጋጣሚዎችን በመጠቀም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ይቁም!

Details
Written by: Gidey Gebre
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 26 August 2020
Hits: 1213
  • ርዕሰ አንቀጽ

አጋጣሚዎችን በመጠቀም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ይቁም!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች። በዚህም  ከመገፋት ያረፈችበት፣ ከጥቃት የተረፈችበት ጊዜ የለም። እንዲያውም መገፋት ግብሯ እስከሚመስል ድረስ የመከራ ዶፍ የሚወድባት ግፍ ተቀባይና ተገፊ እየሆነች ነው። በየዘመናቱ አያሌ ፈተናዎችን ተሻግራ ዛሬ ላይ ብትደርስም አሁንም  እንደጥንቱ ከውጪም ከውስጥም ብዙ መከራዎች እየተፈራረቁባት ይገኛሉ። በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ግንኙነት በሌላቸው ምክንያቶች ሁሉ በርካታ ጥቃቶች እየተፈጸሙባት ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ መለያየትና መከፋፈል ከሌለ ህልውናቸው የሚያከትም የሚመስላቸው አካላት መከፋታቸውና ቤተ ክርስቲያንን በጠላትነት መፈረጃቸው የማይቀር ነው። ለዚህም ነው በሰበብ አስባቡ ቤተ ክርስቲያንን ማጥቃት ግብራቸው አድርገው የተያያዙት። 

ፖለቲከኞች  እያራመዱት ያለው የዘውግ ፖለቲካና ርእዮተ ዓለም በታሪክ ስም በቤተ ክርስቲያን ላይ እየነዙት ያለው የሐሰት ትርክት ቤተ ክርስቲያንን በብዙኃኑ ዘንድ ጠላት አድርጎ በመፈረጅና ወዳጅ አልባ በማድረግ ለጥቃት እያመቻቿት  ነው። ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ሃይማኖታዊ  አመክንዮ  የሌላቸው በለውጥ ስም የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሁሉ የሚጠናቀቁት ቤተ ክርስቲያንን በማቃጠልና ኦርቶዶክሳውያንን በመግደል  ሆኗል። ሐምሌ ፳፻፲ ዓ.ም በሶማሌ ክልል በክልሉ መንግሥት የተደራጀውና ሂጎ የተሰኘው ቡድን በታቀደና በተጠና መንገድ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠለ፤ ካህናትንና ምእመናንን በአሠቃቂ ሁኔታ በማረድ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠለ፤ ነፍሰ ጡርና ሕፃናትን ጨምሮ ብዙ ሴት ኦርቶዶክሳውያን ተደፈሩ። ቤታቸውን አስቀድሞ ቀለም  በመቀባት በተቀናጀ መልኩ ሀብት ንብረታቸው በእሳት እንዲወድም አደረገ። በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ሪፖርት ሲደረግ እንደነበረው የክልሉ ርእሰ መስተዳደድር በነበረው ግለሰብ እና ግብረ አበሮቹ ላይ ክስ ቢመሠረትም ክስ ከተመሠረተባቸው በርካታ ተጠርጣሪዎች ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋሉ አሉ። ከደረሰውም ጥፋት አንጻር በአጥፊዎች ላይ የተወሰደው ርምጃ እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ ከዚያ በኋላ በተመሳሳይ መልኩ ጥፋት እያደረሱ ያሉ አካላትን ያበረታታ ይመስላል። 

Read more: አጋጣሚዎችን በመጠቀም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ይቁም!

የአብርሃም ቤት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 26 August 2020
Hits: 1317
  • ቤተ አብርሃም
የአብርሃም ቤት

በቤተ ክርስቲያናችን ካሉት አሳሳቢ ችግሮቹ አንዱ ለመገናኛ በማይመቹ አካባቢዎች ያሉ በዕድሜ ብዛት እና በእንክብካቤ እጦት በመፈራረስ ላይ የሚገኙት፣ በውስጣቸው ብዙ ንዋያተ ቅድሳትንና ብርቅና ድንቅ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዙት አብያተ ክርስቲያናት ችግር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የዛሬው እንግዳችን አባ ዜና ገብርኤል ያደረጉት እንቅስቃሴ አበረታችና አስተማሪ በመሆኑ ከአባታችን ልንማር ይገባል በሚል የወሩ የ‹‹የአብርሃም ቤት›› እንግዳችን ሆነዋል፡፡ አባ ዜና ገብርኤል የኖሩት በአዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤት ለእንግዳ…፡፡  

አባ ዜና ገብርኤል እስከ ፲፱፻፶፰ ዓ.ም ድረስ በላስታ አውራጃ በዋልድቢት ማርያም ገዳም ይኖሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ የጀመራቸው የሥጋ ደዌ በሽታ ስለተባባሰባቸው ለሕክምና ወደ ደሴ ከተማ መጥተው ከ፲፱፻፶፰-፲፱፻፷፫ ዓ.ም ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆዩ፡፡ ይህ ሕመም ሳይሻላቸውም ዓይናቸው ታመመ፡፡ ከዚያም ለከፍተኛ ሕክምና ወደሻሸመኔ ኩየራ ሔዱ፡፡ ሻሸመኔ ሲደርሱ ግን ሐኪሙ ወደሌላ ቦታ በመሔዳቸው ሳይታከሙ ቀሩ፡፡  

Read more: የአብርሃም ቤት

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

Details
Written by: Ayitenew
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 26 August 2020
Hits: 1376
  • አጫጭር ዜናዎች
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

ቀን፡- ነሐሴ 20/2012 ዓ.ም.

 

 

በስመ

አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

የልጃችን የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ እና ግድያውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ዞኖች ተቀነባብረው በተፈጸሙ ጥቃቶች የተጎዱ ኦርቶዶክሳውያንን መርዳትንና መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

“አማን አማን እብለክሙ ከመ ትበክዩ ወትላህዉ አንትሙ፤ ወዓለምሰ ይትፌሣሕ፤ ወአንትሙሰ ተኃዝኑ፤ ወኃዘንክሙ ፍሥሐ ይከውነክሙ = እውነት እውነት እላችኋለኹ፤ እናንተ ታለቅሳላችኹ፤ ሙሾም ታወጣላችኹ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችኹ፤ ነገር ግን ኃዘናችኹ ወደ ደስታ ይለወጣል፡፡” (ዮሐ.16፥20) ሃጫሉ ሁንዴሳ ስመ ጥምቀቱ ኃይለ ገብርኤል፣ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ መገደሉ ይታወሳል። ቤተ ክርስቲያን፥ በዚያ ድንገተኛ የልጇ ግድያ ከባድ ኃዘን ተሰምቷታል፡፡ ኾኖም፣ በግድያው የተሰማትን ኃዘን ለመወጣት ጊዜ ሳይሰጣት፣ ኃዘንተኛነቷ ተረስቶ እና እንደ ጠላት ተቆጥራ፣ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በክርስቲያን ልጆቿ ላይ ዘግናኝ ፍጅት እና መከራ ተፈጸመባቸው።

Read more: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

Page 18 of 19

  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት