ሐመረ ጽድቅ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ሐመር
    • የማኅበሩ መልእክት
    • ትምህርተ ሃይማኖት
    • እናስተዋውቃችሁ
    • የጥያቄዎቻችሁ መልስ
    • ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት
    • ኪነ ጥበብ
    • የነገዋ ቤተ ክርስቲያን
    • ከዓለም ማእዘናት
    • ዐውደ ስብከት
    • ዐቢይ ጉዳይ
  • ስምዓ ጽድቅ
    • ርእሰ አንቀጽ
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ሪፖርታዥ
    • ቤተ አብርሃም
    • ፍሬ ከናፍር
    • የሕፃናት ዓምድ
    • ትዝብት
    • ምሥጢሬን ላካፍላችሁ
  • ሙሉ ሕትመቶች
    • ሐመር በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • ሐመር በ ዓ.ም.
      • 1985
      • 1986
      • 1987
      • 1988
      • 1989
      • 1990
      • 1991
      • 1992
      • 1993
      • 1994
      • 1995
      • 1996
      • 1997
      • 1998
      • 1999
      • 2000
      • 2001
      • 2002
      • 2003
      • 2004
    • ሐመር በዓመት
      • 1ኛ ዓመት
      • 2ኛ ዓመት
      • 3ኛ ዓመት
      • 4ኛ ዓመት
      • 5ኛ ዓመት
      • 6ኛ ዓመት
      • 7ኛ ዓመት
      • 8ኛ ዓመት
      • 9ኛ ዓመት
      • 10ኛ ዓመት
      • 11ኛ ዓመት
      • 12ኛ ዓመት
      • 13ኛ ዓመት
      • 14ኛ ዓመት
      • 15ኛ ዓመት
      • 16ኛ ዓመት
      • 17ኛ ዓመት
      • 18ኛ ዓመት
      • 19ኛ ዓመት
      • 20ኛ ዓመት
    • ስምዓ ጽድቅ በወር
      • መስከረም
      • ጥቅምት
      • ህዳር
      • ታህሣሥ
      • ጥር
      • የካቲት
      • መጋቢት
      • ሚያዝያ
      • ግንቦት
      • ሰኔ
      • ሐምሌ
      • ነሐሴ
    • አዳዲስ ሙሉ ሕትመቶች
      • አዲስ ሐመር
      • አዲስ ስምዐ ጽድቅ
  • ያግኙን

ስምዓ ጽድቅ

ማኅበረ ቅዱሳን የስድስት ወር የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

Details
Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 28 April 2021
Hits: 1135
  • አጫጭር ዜናዎች
ማኅበረ ቅዱሳን የስድስት ወር የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የስድስት ወር የሥራ አመራር ጉባኤውን ከሚያዚያ ፩ እስከ ሚያዚያ ፫  ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም አካሄደ።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር የተወከሉ የማዕከላት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኝተዋል። በጉባኤውም የሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ፣ የኤዲቶሪያል ቦርድ ማስተባበሪያ፣ የኦዲት አገልግሎት ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የስድስት ወር የሥራ አመራር ቃለ ጉባኤም ጸድቋል። 

በቀጣይ ቀናትም የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ አገልግሎት ተግዳሮትና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ ስልታዊ ዕቅድ ማሻሻያ፣ የተቋማዊ  ለውጥ መነሻ ሐሳቦች እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መነሻ ሐሳብ  የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተነሥተው  ውይይት ተደርጎባቸዋል። 

ማኅበሩ ስልታዊ ዕቅድ ከጀመረ አራተኛ ዓመት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የማኅበሩ ዋና ጸሓፊ አቶ ውብሸት ኦቶሮ የስልታዊ ዕቅዱ አጠቃላይ ይዘት ስድስት ወሳኝ ጉዳዮችን፣ ፳፱ ግቦችን ፪፻፳፫ ስልቶችና አመላካቾች የተካተቱበት እደሆነ፤ የስልታዊ ዕቅዱ ዋና እሳቤም ከአጋር እና ከተባባሪ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ እንዲሁም የሰው ኃይል ልማት ላይ እንደሚያተኩርም ገልጸዋል።  

በጉባኤው መዝጊያም የማኅበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ  በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ችግሩ እጅግ እየተወሳሰበ መምጣቱን ገልጸዋል። አክለውም የማኅበሩ አባላት ከወትሮ በተለየ መልኩ ሱባኤ ገብተው ጸሎት በማድረግ እንዲሁም በማስተማር እና በመምከር ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ የምስጋና ደብዳቤ ላኩ

Details
Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 28 April 2021
Hits: 1088
  • አጫጭር ዜናዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ የምስጋና ደብዳቤ ላኩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳስ ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ሃይማኖትን መሠረት የደረጉ ጥቃቶች ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ላደረጉት ጸሎት እና ድጋፍ ለሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል ሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም  የምስጋና ደብዳቤ መላካቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ፔጅ ዘግቧል።

ቅዱስነታቸው የምስጋና ደብዳቤውን የላኩት የሞስኮና የመላው ሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ምእመናን መገደላቸውን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኀዘን መግለጫ እንዲሁም የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድጋፍ እንደሚያደርጉ የሚገልጽ ደብዳቤ መላካቸውን ተከትሎ ነው።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉት ጥቃቶች በዋነኝነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን በምስጋና ደብዳቤያቸው ላይ አክለው ገልጸዋል።

የሞስኮና የመላው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል በየካቲት ወር ፳፻፲፫ ዓ.ም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኀዘን መግለጫ ደብዳቤ መላካቸውን አስመልክቶ መዘገባችን ይታወሳል።

 

የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ . ከቁሳዊ ድጋፍ በተጨማሪ መንፈሳዊ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተገለጸ

Details
Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 28 April 2021
Hits: 1016
  • አጫጭር ዜናዎች
የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች የመቄዶንያ  የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ                                                             .  ከቁሳዊ ድጋፍ በተጨማሪ መንፈሳዊ ድጋፍ  ሊደረግላቸው እንደሚገባ  ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም መቄዶንያ የአረጋውያንና  የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን በመጎብኘት የመቊረቢያ አልባሳትንና የጸሎት መጻሕፍትን ለገሱ።   

የጉብኝት ጉዞው አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግሩም አሥራት ‹‹የታመሙትን መጠየቅ፣ የተቸገሩትንም መርዳት ግዴታችን ነውና ለአረጋውያኑና ለአእምሮ ሕሙማኑ ከቁሳዊ ድጋፍ ባሻገር መንፈሳዊ ድጋፍ ልናደርግላቸውው ይገባል››  ብለዋል። አስተባባሪው አክለውም ‹‹በቃል የምናስተምረውን በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል›› ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም የቀሩትን  የማኅበረ ቅዱሳንን አባላት በማሳተፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በማዕከሉ የተገኙት የማኅበሩ መደበኛ አገልጋይ ቀሲስ ይግዛው መኮንን በበኩላቸው ‹‹መስማት ማየትን አይተካውም የምንሰማውና የምናየው የተለያየ ነው ፤ እኔ እስከዛሬ ስለ ማዕከሉ ሳልሰማ ቀርቼ አይደለም  ፤ ነገር ግን በፊት ከነበረኝ አመለካከት ዛሬ ብዙ ነገር ተምሬአለሁ ፤ መማር ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገር ለማድረግ ወስኛለሁ፤ ስዚህ ሌሎቻችንም በአካል መጥተን ማዕከሉን አልናይ ይገባል።›› ብለዋል። 

አረጋውያኑም የማኅበሩ አገልጋዮች ማዕከሉ ድረስ በመሄድ ስላደረጉላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን የማዕከሉ መሥራች  ክቡር ዶክተር ብንያም በለጠም ‹‹አረጋውያኑን እና የአእምሮ ሕሙማኑን ስለጠየቃችኋቸው፣ ድጋፍም ስላደረጋችሁላቸው ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ›› ያሉ ሲሆን በመቀጠልም ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶች መጥተው እንዲረዱን እንዲሁም  ፹፩ ፷፩ ላይ OK ብለው በእጅ ስልካቸው ላይ በመላክ እና አንድ ብር በመስጠት ጎዳና ላይ የወደቁ  ወገኖቻችንን እናነሳ ዘንድ በእናንተ በኩል አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉል›› ሲሉ መልእክታቸውን አስተላለፈዋል። 

“ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም” - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ክፍል ሁለት

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 28 April 2021
Hits: 1525
  • ፍሬ ከናፍር
“ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን   የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም”                                           - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ  (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)                 ክፍል ሁለት

የተወደዳችሁ አንባብያን የዚህን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ባለፈው እትማችን ላይ ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ እትማችን ደግሞ ክፍል ሁለትን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ትከታተሉ ዘንድ ግብዣችን ነው።

ስምዐ ጽድቅ፡- በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሚኙት ‹‹የቅባት እምነት›› አራማጆች በርስዎ ሀገረ ስብከት ላይ ያደረሱት ተፅእኖ ካለ ቢገልጹልን?

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፡- ሀገረ ስብከታችን ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ቀሳጥያኙ በተለይም በደጋ ዳሞት በኩል እየገቡ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሊከፋፍሉና ባዕድ አስተምህሯቸውን ሊያስፋፉ ሲሞክሩ ጥብቅ ቁጥጥርና ክልከላ በማድረግ በአካባቢው እንዳይንቀሳቀሱ ስናደርግ ቆይተናል። የአካባቢው ምእመናንም ሆኑ ካህናቱ ችግሩን በደንብ የተረዱ፣ እምነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸውና ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና በመገመት በሀገረ ስብከታችን ከሙከራ የዘለለ የተጠናከረ እንቅስቃሴ አያድርጉም። በሀገረ ስብከታችን ውስጥ ሰርገው በሚገቡበት ወቅት በተቆጡ ምእመናንና አገልጋዮች አማካይነት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ እኔም ምእመናንና ካህናትን በመሰብሰብ ችግር ሳይፈጠር በዓይነ ቁራኛ ብቻ ተከታትለው በሰላም እንዲወጡ የማድረግ ሥራ ብቻ እንዲሠሩ እነግራቸዋለሁ። አልፎ አልፎ ወደ ሀገረ ስብከታችን በሚመጡበት ወቅት በምእመናን በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት አፍረውና ተሸማቅው ይመለሳሉ። 

Read more: “ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም” - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ...

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በአጣዬና አካባቢው ለተፈናቀሉ ምእመናን ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 28 April 2021
Hits: 1015
  • አጫጭር ዜናዎች
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በአጣዬና አካባቢው ለተፈናቀሉ ምእመናን ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በተፈጸመ ጥቃት  ለተፈናቀሉ የአጣዬ ከተማና አካባቢው ምእመናን የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቃዐጥበብ አባቡ አስታወቁ፡፡ 

በቅርቡ በአጣዬ ከተማና አካባቢው የጥፋት ኃይሎች በፈጸሙት ዘርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ አስከፊ ጉዳት እንደደረሰ ሥራ አስኪያጁ ገልጠዋል፡፡ በተፈጸመው ጥቃት ሀብት ንብረት እንደወደመና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ሕይወት እንደጠፋ ያስረዱት ሥራ አስኪያጁ በጥቃቱም እስካሁን ድረስ ከሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ በላይ ምእመናን ተፈናቅለው በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያዎች እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ 

ከጥቃቱ የተረፉ ምእመናን በደብረ ብርሃን፤ በደብረ ሲናና በመሐል ሜዳ ከተሞች ጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ የገለጡት ሥራ አስኪያጅ ሀገረ ስብከቱም አቅም የፈቀደውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአጣዬ ከተማና አካባቢው አክራሪዎች ባደረሱት ጥቃት ምክንያት በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዘገበ ሲሆን ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚሠራው ሥራ ላይ ሀገረ ስብከታቸው በቀጣይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡ 

ሀገረ ስብከቱ በተለይ በመሐል ሜዳ ተፈናቅለው ለሚገኙ ምእመናን አስቸኳይ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ያስረዳው ዘገባው ድጋፍ የተደረገላቸው ምእመናንም ለተደረገላቸው ድጋፍ ማመስገናቸውን አስረድቷል፡፡ 

ሰሞኑን በሚከበረው የትንሣኤ በዓል ወቅት ምእመናን በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ምእመናን ጋር በጋራ በማክበር ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል፡፡

በአካባቢው ተመሳሳይ ችግር ድጋሚ እንዳይከሰት ሀገረ ስብከታቸው ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መሆኑንን ብፁዕነታቸው አንስተው በሌሎች አካባቢዎች በጊዜያዊ መጠለያ ላሉ ምእመናን ጭምር አስቸኳይ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውንም ዘገባው  አስረድቷል፡፡ 

 

በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የምእመናን ተሳትፎ

Details
Written by: በጋዜጣው ሪፖርተር
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1067
  • ርዕሰ አንቀጽ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ  ክርስቲያን ሀገርን በሚመለከት ማንኛውም ጉዳይ ላይ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች። ተደጋግሞ እንደሚጠቀሰው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የማስታወቂያ ሚንስቴር፣ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሆና ሀገርን እና ሕዝብን ስታገለግል ኖራለች። ኦርቶዶክሳውያን ልጆቿም ከቤተ መንግሥት ጀምሮ እስከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ድረስ በሀገራችን በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት፣ በአማካሪነት እንዲሁም በዲፕሎማትነት ሲያገለግሉ ኖረዋል። እነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ላይ ለነበራት ከፍተኛ ሥፍራ እና ተሰሚነት ማሳያዎች ናቸው።

በሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ተቋማትም ሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የኋላ ታሪካቸው ሲታይ የቤተ ክርስቲያን አሻራ ያረፈባቸው ናቸው። በእምነት ተከታዮቿ ብዛት የሀገራችን ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሸፍን ምእመን ያላት ክርስቶሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ክብርና  ተሰሚነት የነበራት፣ ታላቅ ቦታም የሚሰጣት  ተቋም ነበረች። እንደዛሬው ሳይሆን በዚህ ወቅት በታላቁ የጾመ ሁዳዴ የመገናኛ ብዙኃኑ ሳይቀር ስለመንፈሳዊ ነገር የሚሰብኩ፣ በዘፈን ፈንታ የበገና መዝሙር የሚሰማባቸው ነበሩ። 

Read more: በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የምእመናን ተሳትፎ

ፍትሕን የተጠሙ ነፍሳት…

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 988
  • ሪፖርታዥ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ መጠነ ሰፊ የሆነ የአካል፣የንብረት፣የሥነ ልቡናና የኢኮኖሚ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ጥቃቱን በአብዛኛው የሚፈጽሙት በሃይማኖት ስም የተደራጁ አክራሪ ቡድኖች ናቸው። በተለይም በአንዳንድ የኦሮምያ ክልል ከተሞች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የማያቋርጥ ውድመትና ጭፍጨፋ ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ አሁንም እያደረሱ ይገኛሉ። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ጽንፈኛ አክራሪ ኃይሎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጭምር ሳይቀር የስንቅና ትጥቅ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። 

ለአክራሪ ጽንፈኛ ኃይሎች የስንቅና ትጥቅ የሚያቀርቡትም ሆነ የአክራሪዎቹ ዋና ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ማዳክም ሕዝበ ክርስቲያኑን ደግሞ ቢችሉ እነርሱ ወደሚፈልጉት እምነት መውሰድ ካልሆነ ደግሞ መግደል፣መዝረፍ ማፈናቀል እንዲሁም ሕይወታቸውን በስጋትና በሰቀቀን እንዲገፉ ማድረግ ነው። የመጨረሻ ሕልማቸውም ወድቃ የማትወድቀውን ቤተ ክርስቲያንን ገፍተው መጣል ነው። ይህንን ተግባር ላለፉት አርባና ኀምሳ ዓመታት ይፈጽሙት እንደነበረ ቢታወቅም በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ መልኩንና ዓይነቱን እየለዋወጡ በቤተ ክርስቲያንና በምእመና ላይ ዘመን የማይሽረው ትውልድ የማይረሳው በደል ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ አሁንም እያደረሱ ይገኛሉ።  

Read more: ፍትሕን የተጠሙ ነፍሳት…

‹‹ምእመናን በእምነታቸው እንዲጸኑ እኛ ካህናት ትጉህ እረኛ ልንሆን ይገባል›› - ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን

Details
Written by: መጽሐፈ ሲራክ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1296
  • ቤተ አብርሃም
‹‹ምእመናን በእምነታቸው እንዲጸኑ እኛ ካህናት ትጉህ እረኛ ልንሆን ይገባል››                                   - ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን

የተወደዳችሁ አንባብያን በዛሬው የቤተ አብርሃም ዐምድ ዝግጅታችን ይዘንላችሁ የቀረብነው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አገልጋይ ካህን የሆኑትን ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንንን ነው። ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን  በ ፲፱፻፷፰ ዓ.ም ወደ ካቴድራሉ መጥተው ማገልገል ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ሲሰጡ ቆይተዋል አሁንም እየሰጡ ነው። ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ምእመናን እንዲበዙ ወደ ተለያየ ቦታ በመዘዋወር  ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸዋል፤ አሳድሰዋል። በተቀጠሩበት ደብር በቅስና፣ የሰበካ ጉባኤ አባል በመሆን፣ እንዲሁም ለመንፈሳዊ ሥራ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በመግባት አገልግለዋል። 

በሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ስም ሲሠራ የነበረውን አደባባይ የተለያዩ ምእመናንን በማስተባበር አሠርተዋል። በካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ናቸው። ዛሬም ድረስ  ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን የሚጠቅም ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ። 

Read more: ‹‹ምእመናን በእምነታቸው እንዲጸኑ እኛ ካህናት ትጉህ እረኛ ልንሆን ይገባል›› - ሊቀ ትጉሃን ደሴ መኮንን

“ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም” - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1060
  • ፍሬ ከናፍር
“ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን   የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም”                        - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ  (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ ከካቶሊክ እስከ ፕሮቴስታንት ከተሐድሶ እስከ ቅባትና ጸጋ እንዲሁም ሌሎች ለዘመናት ጥረት ሲደርጉ ቆይተዋል። እነዚህ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን በውጭ ካሉ ሀገራት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚደረግላቸው ድጋፍ በከፍተኛ የሰው ኃይልና ገንዘብ ታግዘው ለዘመናት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ሲሸረሽሩ ምእመናንን ሲያወዛግቡና ሲከፋፍሉ ቆይተዋል። ቤተ ክርስቲያንም ኃይለ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርጋ ከቅጥሯ ውጭ ያሉትን ቀሳጥያን ከቅጥሯ ስታርቃቸው በውስጧ የነበሩ የእናት ጡት ነካሾችን ደግሞ በመምከር፣በማስተማር፣ንስሐ በመስጠት በዚህ ሁሉ አልፈው የማይመለሱትን ደግሞ በማውገዝ ከዐውደ ምሕረቷ እንዳይቆሙ ከቅጥሯ እንዳይደርሱ በማድረግ አስተምህሮዋን ከብረዛ ምእመኖቿን ደግሞ ከነጠቃ ስትታደግ ቆይታለች። እነዚህ የበግ ለምድ የለበሱ ነጣቂ ተኩላዎች ለጊዜው የተሳካላቸው ቢመስላቸውም  የቤተ ክርስቲያንን አሸናፊነትና መለኮታዊ ኃይል መቋቋም ሳይችሉ ቆይተዋል። የነጣቂ ተኵላዎች ጥረትም ከንቱ ሆኖ ቤተ ክርስቲያን በቻለችው መጠን ከሐዋርያዊ ጉዞዋ ሳትገታ ለዓለም ብርሃን መሆኗን ቀጥላለች። 

Read more: “ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመበረዝ በተነሡ ቡድኖች ላይ እስካሁን የተወሰደ ተጨባጭ ርምጃ የለም” - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ (የምዕራብ ጎጃም ሀገረ...

ዐቢይ ጾም (ጾመ ሁዳዴ)

Details
Written by: በእህተ ሚካኤል
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1217
  • የሕፃናት ዓምድ

ልጆች! ባለፈው እትማችን በዐቢይ ጾም (በጾመ ሁዳዴ) ውስጥ ከሚገኙ ሳምንታት እና መጠሪያዎቻቸው ውስጥ ‹‹ምኲራብ›› እና ‹‹መጻዕጉ››ን ስያሜያቸውንና ታሪካቸውን ነግረናችሁ ነበር። መቼም እንዳልረሳችሁት ተስፋ እንዳርጋለን። እነሆ በዚህ ዝግጅት ደግሞ ስለ ‹‹ደብረ ዘይት›› እና ስለ ‹‹ገብርኄር›› ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉን። 

5. ደብረ ዘይት 

ልጆች! አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹‹ደብረ ዘይት›› በመባል ይጠራል። ይህ ቀን  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ወደዚህች ምድር ዳግመኛ ስለመምጣቱ ፣ስለ ዓለም ፍጻሜ እንዲሁም ስለ ትንሣኤ ሙታን ያስተማረበት ነው። 

Read more: ዐቢይ ጾም (ጾመ ሁዳዴ)

የሀብታምና እና የድሀ ሥርዓተ ቀብር

Details
Written by: ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1265
  • ትዝብት

ሰው የተፈጠረው ሕያውና መልካም የሆነው የአምላኩ የእግዚአብሔር የክብሩ ወራሽ እና የስሙ ቀዳሽ ሆኖ እንዲኖር ነው። በምድርም ላይ ክቡር፣ ትሁት፣ ባለጸጋ፣ ንጉሥ፣ ጠቢብ ሆኖ እንዲመላለስ ፈቅዶለታል። ሰው ግን ክቡርና ሕያው ሆኖ መኖር የሚችለው ፈጣሪው ያዘዘውን የሚፈጽም ለእርሱም በትሕትና የሚገዛ መሆን ሲችል ነበር። ይህንንም ‹‹መልካምንና  ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ›› ዘፍ ፪፥፲፯ ብሎ አምላኩ ትእዛዝን ሰጠው። ይህን የመገዛቱ ማሳያ የሆነ ትእዛዝ አክብሮ ቢገኝ ሕያው ሆኖ በሥጋውም በነፍሱም መኖር በተቻለው ነበር። ካልታዘዘ ግን የሞት ሞትን እንደሚሞት ታውቋል። ሰው ግን በሰይጣን ምክር ተነሣሥቶ ይሄህን ትእዛዝ ስለጣሰ፤ ‹‹አትብላ›› ከተባለውም ወስዶ ስለበላ  በሥጋም በነፍስም ሞት መጣበት። ከሞት ጋርም መራቆት፣ ሐዘን፣ ትካዜ፣ ሰቆቃ፣ መለየት፣ ውርደት፣ ስደት ደረሰበት። 

ቸር የሆነው እግዚአብሔር የሰውን መጸጸት ተመልክቶ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ የድንግል ማርያምን ሥጋ ተዋሕዶ በተገለጸው በአንድ ልጁ ቤዛነት ሰውን ከሞተ ነፍስ አዳነው። ከነፍስ ሞት ታደገን በትንሣኤው በትንሣኤ ዘጉባኤ ለሚሆነው ለሥጋ  ትንሣኤያችን ተስፋ ሰጠን።  

Read more: የሀብታምና እና የድሀ ሥርዓተ ቀብር

ምእመናን ፍትሕን የሚያሰፍን የፖለቲካ ድርጅት እንዲመርጡ ማኅበሩ አሳሰበ

Details
Written by: ካሳሁን ለምለሙ
Category: ስምዓ ጽድቅ
Published: 08 April 2021
Hits: 1445
  • አጫጭር ዜናዎች
ምእመናን ፍትሕን የሚያሰፍን የፖለቲካ ድርጅት እንዲመርጡ ማኅበሩ አሳሰበ

ምእመናን በሀገራችን ኢትዮጵያ ፍትሕ ርትዕን የሚያሰፍን የፖለቲካ ድርጅት ሊመርጡ እንደሚገባ በኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሓፊ አቶ ውብሸት ኦቶሮ አሳሰቡ። 

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በሀገራቸው ፍትሕ ርትዕን የሚያመጣ የፖለቲካ ድርጅት እንዲመርጡ ማኅበረ ቅዱሳን የድርሻውን እንደሚወጣ ያስታወቁት ዋና ጸሐፊው ምርጫ ላይ ባለመሳተፋቸው በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመጣ የሚችለውን ጫና እንዲረዱ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ፖለቲካ ላይ በበቂ ሁኔታ ባለመወከሏ ላለፉት በርካታ ዓመታት ግፍ ሲፈጸምባት እንደኖረች አክለዋል። 

Read more: ምእመናን ፍትሕን የሚያሰፍን የፖለቲካ ድርጅት እንዲመርጡ ማኅበሩ አሳሰበ

Page 6 of 19

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10

የቅጅ መብት © ማኅበረ ቅዱሳን 2012 ዓ.ም.

ዋናው ማዕከል | Afaan Oromoo | English |አሜሪካ ማዕከል | አውሮፓ ማዕከል | ካናዳ ማዕከል | ትሩፋት
MK Facebook MK Telegram MK Youtube
አጫጭር ዜናዎች የሕፃናት ዓምድ ትዝብት ሪፖርታዥ ቤተ አብርሃም ፍሬ ከናፍር ምሥጢሬን ላካፍላችሁ ርዕሰ አንቀጽ Oct ኪነ ጥበብ June ዐውደ ስብከት sept እናስተዋውቃችሁ ትምህርተ ሃይማኖት Nov Mar Apr ዐቢይ ጉዳይ ክርስትና በማኅበራዊ ሕይወት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የጥያቄያዎቻችሁ መልስ July የማኅበሩ መልእክት Jan Aug May 1997 13 ከዓለም ማእዘናት